አዎን ኦሮሚያ የኦሮሞ ናት

February 10, 2016 | By Jawar Mohammed (Political analyst and Activist)

ወዳጄ አበበ ገላው ( Abebe Gellaw) ሰሞኑን በአፋን ኦሮሞ የጸፍኳትን አንድ ንባብ ወደ እንግሊዚኛ አስተርጉሞ በመለጠፉ ከልብ አምሰግናለሁ (የትርጉም ግድፈቶቹ እንዳለ ሆኖ)። ያቺ ጽሁፍ ይህን ያህል ተወዳጅ ከሆነች እነሆ እኔም ሃሳቧን ሰብሰብ አድርጌ በአማርኛ አቅርቤላችኋለሁ። ባጠቃላይ በ G7 ሰብሰባ ላይ የተንጸባርቁት ሀሳቦች ቢያን አራቱ ተቀባይነት እንደሌላቸው ነው ጽሁፏ የምትተነትነው።
1)"አሮሚያ የኦሮሞዎች ነች የሚለው ሀሳብ ትክክል አይደደልም" እዝህ ጋር ሊሰመርበት የሚገባ ነገር ቢኖር ይህ ድርጅት ስብሰበውን የጠራው ወይም ያከሄደው በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ንቅናቄ መሰረት በማድረግ በመወያየት ድጋፍ ለመድረግ በሚል የታሰበ ነው። ይሁንና በአንድ በኩል በህዝባዊ ንቅናቄው ውስጥ በቀጥታ በመሳተፍ ጉዳት የደረሰባቸውን ታጋዮች ከልብ እንደግፋለን እያሉ ከንፈር በመምጠጥ በሌላ መልኩ ደግሞ ታጋዮቹ አንግበው የተነሱተን መፈክር በመኮንን፣ ድጋፉም ሆነ ከንፈር መጠጣው የውሸት እንደሆና ያሳያል። ሁሉም ሰው ሊገነዘበው የሚገባው ጉዳይ "ኦሮሚያ የኦሮሞ ነች" የሚለው መሪ ሀሳብ በአሁኑ ወቅት በትግሉ ውስጥ ያለን የኦሮሞ ወጣቶች ያመጣነው ወቅታዊ መፈክር ሳይሆን የዛሬ አመሳ አመት ገደማ የኦሮሞ ተጋዮች ለነፃነታቸውና ለእኩልነት ትግል ሲጀምሩ የትግሉ ዋና መሰረት በማድረግ አንግበውት የተነሱት የሀገር በለቤትነት (mirga abbaa biyyummaa) ጥያቄ ነው። ኦሮሚያ የኦሮሞ ነች ስንል ኦሮሚያ የኦሮሞ ህዝብ ሀገር ነች ( Oromia is homeland of the Oromo people) ማለት ነው:: ይህንን መሰረታዊ ሀሳብ መቃወም ማለት የኦሮሞን ህዝብ መሰረታዊ የመብት ጥያቄ መካድ ብቻ ሳይሆን ንብረቱንና ሀገሩን ለመዝረፍ አላማ አንደላቸው አመላካች ነው። ኦሮሚያ የአሮሞ ካልሆነች ከወያኔ ጋር የአሮሞ ህዝብ ሰጣ ገበ እና ጥል ውስጥ ለመግባት ባልቻልን ነበር። የአፋር ክልል የአፋሮች፣ ሲዳማ የሲዳማዎች ስለመሆኑ ለመቀበል የሚያደግተው ቡደን መሬት ላይ ያሉትን እውነታዎች የማይቀበል በመሆኑ ከወቅቱ ጋር ለመራድ የይምሮውን software update ማድረግ ተገቢነት ያለው ይመስለኛል። ኦሮሚያ የኦሮሞ ነች ማለት ኬኒያ የኬኒያኖች፣ ኢትዮጲያኖች እንደ ማለት ነው። ይህ ማለት ኬኒያ ወይም ኦሮሚያ ውስጥ ሌላ ሰው መኖር ዜጋ መሆን አይችልም ማለት አይደለም። በሚገባ ይችላለ። የማይቻለው ሀገሬው ተገፍቶ የሀር ባለቤትነት መብቱን ተነጥቆ ሌላው ሊንደላቀቅበት ማሰቡ ነው። እናም ኦሮሚያ የኦሮሞ ነች የሚለውን መፈክር ልናፍርበት ሳይሆን በደማችን እውን ለማድረግ እየታገልንለት ያለ ህያው አላማችን ነው። ይህን አላማችንን የሚቃወም ካለ ከኦሮሞ ጋር መስራት አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን ፀረ-ኦሮሞ በመሆኑ አጥብቀን አንታገለዋለን። ( Note: ኦሮሚያ የኦሮሞ ነች ማለት እና ኦሮሚያ ለኦሮሞውች ማለት ለየቅል ነው። የአበበ ገላው ተርጓሚ 'የ'ን በ 'ለ' በመተካት ስህተት ውይም ቅጥፈት ፈጽሟል)
2. "የማንነተን ፖለቲካ መሰረት የደረገ ትግል አፍራሽና ለዲመክራሳዊ ስርዐት የማያመች" ነው የሚለው የተለመደው አጣጣይ የሆነ ሀሳብ ነው። በኢትዮጲያ ፖሊተካ ንትርክ ሂደት ውስጥ የማንነት፣ የብሄር፣ የጎሳ ወይም የዘውግ ፖለቲካ ተብለው የሚነሱ አተካሮዎች በኦሮሞ ፖሊቲካ ሂደት ላይ የነጣጠሩ የማንቋሸሽ አባባሎች ስለመሆናቸው ከማንም የተሰወረ አይደልም። የኦሮሞ ህዝብ በብሄር ተደራጅቶ ከተንቀሳቀሰ ከጥቅሙ ይልቅ ለሌላው ማህበረሰብ አደጋ አለው ወይም ጎጂ ነው በሚል ማስፈራሪያ የሚደረደረው ፕሮፓጋዳ ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ አንዳልሆነ የኦሮሞ ተማሪዎችና እርሶ አደሮች በቅርቡ ባደረጉት አንቅስቃሴ አስመስክረዋል። ብዙ ከተማዎችንና አካባቢዎቸን ነጻ በወጡበት ወቅት በሌላው ብሄረሰብ ጉዳት አለማድረስ ብቻ ሳይሆን ድህንነታቸውን ከመጠበቅ አንፃር ያሳዩት ስነምግባር ቁልጭ ብሎ እየታየ "ብሄር ፖለቲካ ጉዳት አለው" በማላት መሰረት የሌለው የማጥላላት ወሬ ላይ የተጠመዱ ቡድኖች የሀሳባቸውን ታአማኒነት ማጣት እና ፉርሽነት የሚያመላክት ነው። ይህን ሀሳባቸውን አሁንም ደጋግሞ ማንሳት ለኦሮሞ ህዝብ ያላቸው መሰረተ ቢስ ፍራቻ እና ጥላቻ (Oromophobia) ጨፍግጎ ይዞ አንዳልቀቃቸው ያሳያል። ማንም ተቀበለ አልተቀበለው የኦሮሞ ህዝብ በብሄራዊ ማንነቱ ይኮራል፣ ይደራጃል፤ የጋራ ጥቅሙን ለምስከበርም በአንድነት ይታገላል። ይህንን የትግላችን መሰረት የማይቀበሉ ብሎም ለማጥቃት ከሚቋምጡ ሀይሎች ጋር መስራት ይቅርና መነጋገር አንችልም። (በነገራችን ላይ "ትግሬ ሀገር ወረረ፣ ዘረፈ፣ ወታደሩን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩት" እያሉ ሲለፍፉ ወይም ደግሞ "አማራው ከጉራ ፈርዳ ተፈናቀለ፣ ወልቃይት ከአማራ ተቆርጦ ለትግራይ ተሰጠ" ብለው ሲከሱ 'በዘውገ' ላይ የተመሰረት ፖሊቲካ እያራማዱ መሆናቸውን የሚያስተውሉ አይመስልም። "ኦሮሞ የሚለው ቃል ሲጨመርበት ብቻ ነው እንዴ ፖሊቲካ የብሄር የሚሆነው?)
3. "ለዘብተኛ እና አከራሪ አሮሞ" ይህ ኦሮሞን በተለያዩ ተፃራሪ ጎራዎች ከፋፍሎ በሂደቱ ለመጠቀም መሞከር ያረጀ አና ያፈጀ ስልት መሆንን የተሰወረበት ሰው ያለ አይመስለኝም። በሀይለስላሴ አና በድርግ የአገዛዝ ዘመን "ሀገር ወዳድ ኦሮሞና ወንበዴ ኦሮሞ" በመለስ ዘመን ደግሞ "ጠባብ ብሄረተኛ እና ዲሞክራሳዊ ብሄረተኛ" ብለው አንዱን ወደራሳቸው በማቅረብ ሌላውን በመግፋት ሲገዙ ነበር። አሁንም ቢሆን የነዚያ አምባገነን ጨቋኞች ተተኪ ለመሆን ሚገመዡ ግለሰቦች እና ቡድኖች አንዱን ኦሮሞ ለዘብተኛ ነህ በማለት በማቅረብ ሊጠቀሙበት፤ ሌላውን ደግሞ አክራሪ በማለት ፈርጆ ላማውደም መመኘታቸው የህልማቸውን አደገኛነት አመላካች ነው። የኦሮሞ ወጣቶችና ገበሬዎች ለብሄራዊ መብታቸው ሲዋደቁ እና ሲታገሉ አንተ ለዘብተኛ ነህ አንተኛው ደግሞ አክራሪ ነህ የሚለወን ያረጀ የከፋፍል ፈሊጥ አሽቀንጥረው በመጣል ሁላችንም ኦሮሞ ነን በማለት በመላው ኦሮሚያ ግዛት በአንድነት መስዋዕት ሆነዋል። የኦሮሞን ብሄርዊ አንድነት የሚጠራጠሩ ወይንም የትግል አንድነቱን ለማፍረስ የሚጎመዡ ሀይሎች የሀሳባቸውን ፉርሽነት ለመረዳት ባለፉት ሶስት ወራት የተደረጉት እንቅስቃሴዎች በቂ ናቸው። ከሀርርጌ በረሃ እስከ ደጋማው አርሲ ከቦርና ጠረፍ እስከ ወለጋ ድንበር ኦሮሞ በአንድ ድምጽ ከሸዋ ገበሬ ለተዘረፈው መሬት መታገሉ ለብሄረተኝነቱ ስፋት እና መሰረት በቂ ማሳያ ነው።
4."ሰዎችን በማስጮህ፣ በስሜት በመቀስቀስ መንግስት አይወድቅም" ይህ አባባል መለሰ ዜናዊ "መንግስት የዛፍ ፍሬ አይደለም በድንጋይ አይረግፍም" ካለው የተኮረጀ ሲሆን ባለፉት ሶስት ወራት ወያኔን ያንቀጠቀጠውን የኦሮሞ ትግል ለማንኳሰስ ታስቦ የተባለ ነው። ባለፉት ሶስት ወራት የተካሄደው ተቃውሞ ያላንዳች ፕላን፣ ስትራተጂ እና አመራር ዝም ብሎ በደመ ነብስ የተካሄደ 'ሁከት እና ጫጫታ' እንደሆነ ለመፈረጅ የተዳዳ ነው። ግን ለምን? መልሱ ከመቼውም በላይ ተጠናክሮ የወጣውን የኦሮሞ ንቅናቄ ለማዳከም የህዝቡን ሞራል ለማኮላሸት ታልሞ ስለመሆኑ አያጠያይቅም። መሪ የለህም፣ በስትራቴጂ አትመራም ዝም ብለህ ነው የምታልቀው ከተባለ የኦሮሞ ህዝብ በትግሉ ተስፋ ቆርጦ ወደ ሗላ ሊያፈገፍግ ይችላል የሚል ቅዠት መስል ህሳቤ እና መሰረተ ቢስ ተስፋ ነው። የኦሮሞ ወጣቶች ከምንግዜውም በላይ የወያኔን አገዛዝ አንዲህ በሚያርበደብዱበት ወቅት በወያኔ ተቃዋሚ ጎራ የተሰለፈው አካል ይህንን መሰል ሀሳብ እና ተግባር ለምን ይዞ ብቅ አለ? መልሱ አሁንም ግልፅ ነው። "የኦሮሞ ወጣቶች ወያኔን ሲያነቀጠቅጡት አንናተ እስከ አፍንጭችን ታጥቀናል የምትሉት የት ናችሁ?" እያለ እያፋጠጣቸው ላለው ህዝባቸው ሆነው በመገኘት ተግባራዊ መልስ መስተጥ ስላልቻሉ "አይ ኦሮሞዎቹም እኮ ያለ መሪ እና ስትራተጂ ስለሚንቀሳቀሱ ብዙም ከኛ አይሻሉም፣ ርቀውም አይሄዱም አትፍሯቸው" በማለት ማበረታቻ በመስጠት ጊዜ ለመግዛት የሚያደረጉት ተግባር ነው።
በነገራችን ላይ ለስምንት አመታት ፎክሮ፣ ጮሆ ኢትዮጲያ ውስጥ አንድ ወፍ እንኳን ከዛፍ ላይ ማስበርገግና ማንሳት ያቃተው ቡድን የወያኔን ጉልበት አካብዶ መገመቱ የሚገርም ጉዳይ አይሆነም። የሚገርመው ነገር አለምን በማስደመም ጉድ ያስባለውን በኢትዮጲያም ሆነ በአፍሪካ ታይቶ የማይተወቅ ህዝባዊ ነቅናቄን ለማንኳሰስ መሞከሩ፤ ብሎም ደግሞ ጀግነናታቸውን በተጫባጭ ያስመሰከሩ መሪዎችንና ተሳታፊዎቸን ለማናናቅ ማሰቡ ነው። በቀለ ገርባ እኮ እንደነሱ በአጭር የሁለት አመታት እስራት ወኔው ተፈቶ ወያኔን ይቅርታ ጠይቆ ሸሽቶ ውጪ የተመሸገ ሳይሆን የተፈረደበትን ፍርደገምድል የእስር ግዜ ጨርሶ ከወጣ በኋላ በክብር ውጪ አገር ተጋብዞ፤ እዚሁ እንዲቆይ ስንት ነገር ተመቻችቶለት "እምቢ ሞትም ሆነ እስር ከህዝቤ ጋር" ብሎ ተመልሶ ሄዶ ታግሎ አታግሎ ከታጋዮቹ ጋር ዳግም የታሰረ የጀግኖች ጀግና መሆኑ መዘንጋት አልነበረባቸውም። ዶ/ር መረራ ጉዲና ከወያኔ መሪዎች እስከ ተራው ካድሬ ቀንና ሌሊት የዛቻ ውርጅብኝ አየደረሰበት፣ እየዘለፉት፣ ከሚወደው ስራው አባረው እያሰቃዩትም "ሞትም ሆነ ችግር በሀገሬ እና ህዝቤ መሃል ብሎ" ታግሎ እየታገለ ያለ ግዜ ያማይለውጠው ቆራጥ መሪ ነው። የኦሮሞ ትግል በነዚህ ጀግኖች ነው እየተመራ ያለው፤ እነዚህ ናቸው ሚሊዮን ጀግኖችን ለትግል አሰልፈው ወያኔን ያርበደበዱት። እናም የራስን ደካማ ማንነት በኛ መሪዎች ላይ ለማንጸባረቅ ለሚሞክሩት እዛው በጠበላችሁ ማለቱ አስፈላጊ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኦሮሞ ህዝብ ብቻውን መብቱን ማስከበር አይችልም የሚል አመለካከትም ይንጸባረቃል። የኦሮሞ ህዝብ አጋር ቢያገኝ ጥሩ ነው። ነገር ግን አጋር ጠፋ ብሎ እጁን ጠቅልሎ አይቀመጥም። ማንንም "አረ በፈጠራችሁ እርዱኝ" ብሎም አይለምንም። እንዲሁም ለድጋፍ ሲጠሩ ያለማጭድ ባዶ እጃቸውን አንጠልጥለው በመምጣት የባለቤቱን ነዶ ሰርቀው መሄድ የሚፈልጉትንም እርሻው እንዳይገቡ ይከላከላል።
ሌላው ESAT በአፋን ኦሮሞ መጀመሩ አላማው ምን እንደሆነ ገና ከጅምሩ ስላስመሰከረ ብዙ ማለት አያስፈልግም። ስርጭት በጀመረ በመጀመሪያው ሳምንት ዮሮሞዎችን ሰልፍ ሲዘግብ የኦሮሞን ባንዲራ ኤዲት አርጎ ካወጣ፣ ከኦሮሞ የትግል ሙዚቃ ውስጥ የአኖሌ እና ጨለንቆን ሀውልቶች ቆርጦ ካወጣ የፕሮግራሙ አላማ ምን አነድሆነ ፍንትው ብሎ ይታያል።
በመጨረሻም ተገቢውን መስመር ይዞ፣ በሚያመቸው መልኩ ተደራጅቶ እየሄደ ያለውን የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከመተናኮስ እና ለማንኳሰስ ከመሞከር ይልቅ እንታገልለታልን የምትሉትን ትግል በተጨባጭ ምንም ያልተደራጀውን ማህበረሰባችሁን በማደራጀት ለማታገል ብትሰሩ የተሻለ ነው ነሚል ምክር ልለግስ አወዳለሁ። ወያኔ የአማርውን ለም መሬት ለባዕድ ሲሸጥ ጩኸቱን እንኳን ከፍ አድርጋችሁ ማሰማት ከተሳናችሁ፤ የጎንደርን ህዝብ ከፋፍለው እርስ በርሱ ሲያባሉትና ሲያጨፋጨፉት ልትደርሱለት ሳትችሉ እና የጉዳቱ ሰላባዎች ቁጥር እንኳን በበቂ ሁኔታ ማወቅ ሳትችሉ ስለኦሮሚያ መለፈፍ ምን ዋጋ አለው? መሰረታችን ነው ብላችሁ ለምተኮፈሱት የከተማ ህዝብ እንኳ በኑሮ ውድነት ሲሰቃይ ችግሩን ፍንትው አድርጋችሁ አውጥታችሁ ቀስቅሳችሁ ማታገል ተስኗችኋል። እናም የኛን የቤት ስራ ለማረም ጣታችሁን ከመቀሰር ይልቅ የራሳችሁ ላይ ብታተኩሩ ፈተናችሁን ለማለፍ ይበጃችኋል በማለት ሀሳቤን ልቋጭ እወዳለሁ።

No comments:

Post a Comment