Pages

የሀይንሪኽ በል ድርጅት ከኢትዮጵያ የመውጣት ውሳኔ

Deutsche Welle | 13 November 2012

መንግሥታዊ ያልሆነው የጀርመናውያኑ የሀይንሪኽ በል ድርጅት ኢትዮጵያን ለቆ እንደሚወጣ እና በአዲስ አበባ የሚገኘውን ጽሕፈት ቤቱንም እስከ ፊታችን ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚዘጋ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ከሚሰሩት ትልቆቹ መንግሥታዊ ያልሆኑት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ይኸው ድርጅት የኢትዮጵያ መንግሥት ከሦስት ዓመት በፊት ያወጣው የበጎ አድርጎት ተቋማት ሕግ ሀሳብን በነፃ የመግለጽን እና የፖለቲካ ውይይትን የሚገድብ ሆኖ ስላገኘው እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱን በኢትዮጵያ የድርጅቱ ኃላፊ ፓትሪክ ቤርግ ትናንት በበርሊን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስረድተዋል። ሕጉ በስድሳ ሀገራት የሚንቀሳቀሰውን የሀይንሪኽ በል ድርጅት ከአካባቢ አጋሮቹ ጋ ዴሞክራሲን ለማስፋፋት፡ የፆታ እኩልነትን ለማራመድ እና ዘላቂ ልማት ለማስገኘት የጀመረውን ስራውን ለመስራት እንዳላስቻለው ቤርግ አክለው ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment