Pages

ይድረስ ለወጣቱ ለጉብል ነፍጠኛው

July 20, 2013

ይህ ግጥም ተሕሳስ ፬ ፲፱፻፷፰ /1968 (Dec 14. 1975) ተጻፈ፥፥  ነገሮች ተለወጡ ብለን ስናስብ ተመልሰው አዛው በነበሩበት ይንደፋደፋሉ የሚለውን የፈረንጆች ኣባባል ኣስታውሰን  ሰሞኑን አየተስተዋለ ያለዉን ኣስተሳሳብ ከቀድሞው ብዙም ርቆ አንዳልሄደ ያሳይ ይሆን ብለን ይህን ግጥም ለ አንባዎቻችን አቅርበናል፥፥ የጽሁፉን ይዘት አንዳለ ለመረዳት ኦሪጂናሉን ወደ ኮምፑተር ከመለውጥ በስተቀር ምንም የቃላት ለውጥ ሳናደርግ ለማቅረብ ወደናል፥፥ግጣሚው በወቅቱ ቶኪቻው በሚል የሚስጥር ስም ተጠቅሞ  የጻፈው ሲሆን ኣሁን ማንነቱ ያ አውቁ የኦሮሞ ደራሲ አብዱረሺድ መሀመድ ( አባ ኡርጂ) መሆኑን ማወቅ ተችሉዋል፥፥ ደራሲው ብዙ የግጥም፤ የታሪክ አና የለብወለድ መሃፍትን ለህዝብ ያቀረበ ሲሆን፤ በዚሁ ኣመት አራሱ RAAMMISOO ብሎ የሰየመውን  ታሪካዊ ልብወለድ ኣሳትሙዋል፥፥ 
=================================================================

ይድረስ ለወጣቱ ለጉብል ነፍጠኛው
ዱሮ ……………. ዱሮ
ሳንተዋውቅ እንደ ዘንድሮ
ጮርቃ ሆነን
ህጻን ሳለን
ብለው ብለው ባዳምጠው አትኩሬ
ቋንቋህ ሳይገባኝ ሳይጋባህ ቋንቋዬ
ማን አመጣው ሳልል ቀኤያችን
መንደራችን… አገራችን
በእጅ ስንነጋገር
በመላ ስንተባበር
ሳንወድ ተስማምተን
በግድ ተግባብተን
ደስታህ ደስታዬ ነው ተባብለን
ሃዘንህ ሃዘኔ ብለን ተማምለን
ቀስ በቀስ ተዋደን
እንደ ድር ተዋህደን
ባንድ ማእድ በልተን
አንድ አንሶላ ተከናንበን
ከአጐቴ ልጅ አንተን መርጬ
ቋንቋህን ወደድኩ የነን ትቼ።
ሀ… ሁ… ብለን
ፊደል ቆጥረን
አቡግዳን ጨርሰን ዳዊትን ደግመን
ትምርትን ገፋን እድሜንም ጨምረን።
ልጅነት ሀዶ መጥቶ ጉርምስና
ለሰፊው ህዝብ ተቆርቋሪ ሆንና
«በአፄ ተድሮስ እንዲያ የነበረች
በሃይለ ስላሰ ወደሗላ ቀረች»
ብለን ጎን ለጎን ተሰልፈን
ትግል ጀመርን ተራማጅ ሆነን።
መሬት ላራሹ! ስልጣን ለሰፊው ህዝብ!
ስጥ ድሞክራሲ ለሁሉም ያለ ገደብ!
ብለን አብረን
ስረአቱን ተቃውመን
ትምህርት ቤቱን
ስናወጣ እንክትክቱን
አብዮት የመጣው ለሰፊው ህዝብ ብዬ
ንቃ ኦሮሞ! አልኩኝ ለወገነ አዝኜ።
ይህን ስትሰማ ጭንቅላትህ ዞረ
ግንባርህ ኮስትሮ ደም ስርህ ተወጠረ
ድምጽህ ተቀይሮ ከንፈሪህ ደረቀ
የያዝከው ሰሌዳ ከእጅህ ወደቀ።
የስንት ዘመኑ ማደጋችን አብሮ
በአንዲት ቃሌ ወዲያው ተሰባብሮ
ኦሮሞ ኦሮሞ! ማለትህን አቁም
ይሄ መፈክርህ ለኢትዮጵያ አይበጅም
አስተሳሰቡም በጎ አይሆንም ላንተ
ደምህን ደመ ከልብ ያረገዋል በጄ
ብለህ ድፍረህ ማስፋራርያ ዛቻ
ጻፍክልኝ ቆይ ብቻ! ቆይ ብቻ!
ወይኔ! ወይኔ ቅሉ
ጅሉ ጅላንጅሉ
ማን እንደሆነ ዘንግቶ ረስቶ
ከአጋም የተጠጋ ወገኑን ትቶ።
አንተ ምን አጠፋህ ለአገር ታጋዳዩ
የነፍጠኛ ልጅ ያባት ፋኖ ተከታዩ
ቋንቋዬን ትቼ ባህሌን ንቄ
አንተን ለመሆን የመረጥኩ እኔ።
እኔ ነኝ እንጅ ጥፋተኛው
ሆደ ቡቡ ሆደ ባሻው
እንደ ሰገራ እያደር የምጋማ
ተብሎ ስስደብ ፊጽሞ ያልሰማ
የጨለንቆን ደም የወገኑን ካሳ
በቀሉን ያልወጣ ቂሙን የረሳ
ጋላ ጋልነቱን
ቆዳ መንጋጋቱን
ዘውትር እያልከኝ
አብሬህ የኖርኩኝ።
ዛሬ ማንነቴን ባዋጣ ይፋ
ነቅቼ ብነሳ ባሕሌን ላስፋፋ
የብሔሬን መብት ትግል ባስተጋባ
ጭቆናውን ብገልጽ ምሬቱን ባወጋ
ታዲያ አንተ ተጋዳዩ
ያባት ፋኖ ተከታዩ
ጉብል ነፍጠኛው ወጣቱ
ሐገር ያቀናለት አያቱ
ማንነቴ ቸግሮህ ኦሮሞነቴ ሽብሮህ
እንደ አባትህ ዘራፍነት ከጅሎህ
የፈሪ መላ ማስፈራሪያ ዛቻ
ትበልኝ ቆይ ብቻ! ቆይ ብቻ!

አንተን ብሎ ታጋይ
የሰው መብት ተከላካይ
የውሽት ታሪክ ደረቱን የወጠረ
የወገኔን ደም ሲጠጣ የኖረ
ትብዕታም እብሪተኛ መዥገር
የስወ አገር ባይተዋር።
አዳምጠኝ በደምብ አትኩረህ ስማ
ላልሰማው ዘመድህ በሙሉ አሰማ
ከአሁን ጀምሮ ከዛሬ ወድያ
መሬት ከፍ ቢል ዝቅ ቢል ሰማይ
እኔ! እኔ ቶክቻው
አንድዬ የዚያ የጋላው
ቤሔሬ ኦሮሞ! አገረ ኦሮሚያ
ገደል ትግባ ያንተ እትዮጵያ።
ቶክቻው
ተሕሳስ ፬ ፲፱፻፷፰ (1968)
Abbaa Urjii
Dec. 14, 1975

No comments:

Post a Comment