Pages

በዲሲ እና አከባቢዋ የሚኖሩ የኦሮሞ ማህበረሰብ ለደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ያላቸዉን አድናቆት ገለጹ

October 22, 2013 |Gadaa.com

ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ታዋቂ ደራሲ እና ጋዜጠኛ ሲሆን ቀልብን በሚስቡ የሥነ- ጽሁፍ ችሎታው ብዙ መጽፍትን ጽፎ ለአንባቢያን አቅርቧል የኦሮሞን ህዝብ ፖለቲካዊ ታርካዊ ማህበራዊ ባህላዊ እና ሁለንተናዊ ማንነቱን የሚገለጹ ጽሁፎችን በማቅረብ ይታወቃል ለምሣሌ የቡርቃ ዝምታ የጋዜጠኛዉ ማስታወሻ እና የስደተኛዉ ማስታወሻ የተሰኙት መጽፎቹ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ስለ ኦሮሞ ህዝብ ያትታሉ በተለይም በቅርብ ጊዜ ለንባብ የበቃዉ የስደተኛዉ ማስታወሻ የተሰኘዉ መጽሃፉን ለማሳተም ነፃነት አሳታሚ ከሚባል ድርጅት ጋር ከተነጋገረ በኋላ ይሄዉ ድርጅት “ጫልቱ እንደ ሄለን” የተኘዉን አንዱን ምዕራፍ በማስቀረት መጽሃፉን እንደገና አሻሽልሎ እንዲጽፍ በተስፋዬ ላይ ጫና ፈጥሮ መጽሃፉ እንደማይታተም ቢያስፈራራም ተስፋዬ ጥያቄዉን ባለመቀበል ኪሳራዉን በጸጋ ተቀብሎ መጽሃፉ በነፃ ለአንባቢዉ እንዲደርስ ያደረገ ጀግና ነዉ::


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራሳቸዉን ብቸኛዉ የኢትዮዽያ አንድነት ጠባቂ እና አስጠባቂ አድርገዉ የሾሙ ፀረ-አንድነት የሆኑ የዲያስፖራ አባላት በኦሮሞነት እና በኦሮሞ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲሰነዝሩ ይስተዋላሉ ከወራት በፊት ታዋቂዉ ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ ጀዋር መሐመድ ኦሮሞነቱን በአለም አቀፍ ምዲያ ላይ በመግለጹ ብቻ ከፍተኛ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ (Character Assassination) ሰለባ መሆኑ ይታወቃል ይሄዉ የስም ማጥፋት ዘመቻ ዛሬ በተጠናከረ ሁኔታ አድማሱን በማስፋት ቀጥሏል በዚሁ መሰረት ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብን “በሻዕቢያ ሰላይነት” አስፈርጆታል ለዚሁም እንደ ማስረጃ ያቀረቡበት እርስ በእርሱ የሚምታታ እና ምንም ተአማኒነት የለሌዉ የተለመደ ዉንጀላ ነዉ::

በዚሁ ምክንያት በደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ላይ ሊደርስ የሚችለዉን ቁሳዊና ሞራላዊ ኪሳራ ከግምት ዉስጥ በማስገባት በዲሲ እና አከባቢዋ የሚኖሩ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት ለደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ያላቸዉን ልዩ አድናቆት እና ክብር ገልጸዋል በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ዉይይቶች የተደረጉ ሲሆን አንዳንድ ሰዎች በኢትዮዽያ እምፓየር ዉስጥ በኦሮሞነታቸዉ ቢቻ የደረሰባቸዉን ግፍ እና መከራ ለታዳሚዉ በማቅርረብ ከዚህ አንጻር ሲታይ ደራሲ ተስፋዬ በጽሁፉ ያቀረበዉ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተፈጸመዉ የግፍ ታሪክ ዉቂያኖስን በማንኪያ እንደ መጭለፍ ያክል ነዉ ብለዋል በመጨረሻም እነዚህ የኢትዮዽያ አንድነት የሚል የማስመሰያ ጭምብል በማጥለቅ የብሄር ብሄረሰቦችን የግፍ ታሪክ ለማፈን የማይቦዝኑ ሃይሎችን እንደ ተስፋዬ ያሉ ጀግኖችን በመደገፍ ልንታገላቸዉ ይገባል ብለዋል::

ምስጋና ለደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ

No comments:

Post a Comment