Pages

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ገበታው ላይ እያለ በወያኔ ታጣቂዎች በግፍ የተገደለው ወንድማችን ግድያ አጥብቀን እናወግዛለን !!

የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ወጣቶች ላይ በተደጋጋሚ እየፈፀመ ያለው የግፍ ግድያ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የከፈተው የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካል ነው !!

ወጣት አንተነህ አስፋው ለገሰ በ1983 ዓ.ም በዲላ ዞን፣ ፍሰሀ ገነት ወረዳ፣ ቀበሌ 02 ተወለደ፡፡ ይህ ወጣት ተማሪ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የማርኬቲንግ ክፍል /department/ ተማሪ ሲሆን ወደ ዩኒቨርሲቲ በ2004 ዓ.ም የገባና በ2006 ዓ.ም ይመረቅ የነበረ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ህዳረ 24/2006 ዓ.ም ቁጥራቸው ከ60 በላይ ከሚሆኑ ከክፍሉ ተማሪዎች ጋር በመሆን ዳሽን ቢራ በተባለ ቦታ የግብዣ ፕሮግራም አድርገው ነበር፡፡ ከግብዣው ፕሮግራም በኋላ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ወደ ዩንቨርሲቲው ቅጥር ግቢ እየተመለሰ ሳለ የኦሮሞ ተማሪዎች ለብቻቸው ተነጥለው የትግል ዘፈኖችን እየዘፈኑ ይሄዱ ነበር፡፡ የሀበሻ ልጆችም አካባቢውን በጩኸት በመበጥበጥ በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ሰው ሁሉ ሲደበድቡ ነበር፡፡ የኦሮ ልጆች በወቅቱ የትግል ዘፈኖችን ከመዝፈን ውጪ ያነሱት ሁከት አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን ከዳሽን አለፍ ብለው “ቀሀ” የተባለውን ወንዝ ተሻግረው 18 ቀበሌ ሲደርሱ የሀበሻ ልጆች መንገዱ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የወያኔ ታጣቂዎች ላይ ድንጋይ መወርወር ጀመሩ፡፡ የወያኔ ታጣቂዎችም እየረበሹ ያሉትን የሀበሻ ልጆች ትተው ትኩረታቸውን የኦሮሞ ልጆች ላይ በማድረግ እናንተ ኦነግን ታወድሳላችሁ በማለት ተኩስ ከፈቱባቸው፡፡ በወቅቱ በግንባር ቀደምትነት የትግል ዘፈኖች እየዘፈነ የነበረው አንተነህ አስፋው ሲሆን እሱን ጀርባው ላይ በመምታት ሌሎቹን በተኗቸው፡፡ ይህ ልጅ የተመታው ከምሽቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ሲሆን ወዲያውኑ ወደ ዩኒቨርስቲው ሆስፒታል የተወሰደ ቢሆንም የደረሰበት ጉዳት ከባድ በመሆኑ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል እንደተወሰደ እያለ ሂወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡

 ከልጁ ሞት ጋር በማያያዘ ህዳር 25/2013 ከ3,000 – 4,000 የሚሆኑ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በተለይ የኦሮሞ ልጆች ወደ ሆስፒታሉ በሚወስደው መንገድ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት “we need freedom”  ”ነፃነት እንፈልጋለን”  በማለት ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲውን ንብረት ያወደሙ ሲሆን እስካሁን ድረስ በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ የሚገኘው የኦሮሞ ተማሪ፣ አስተማሪና ሌሎች ሰራተኞች ትምህርትና ስራቸውን አቋርጠዋል፡፡ የሀበሻ ልጆች ግን ወደ ትምህርታቸው ተመልሰው  እየተማሩ ናቸው፡፡ ወያኔ ይህን ስልት የተጠቀመው  የኦሮሞ ልጆችን ለመጨረስ ነው ሲል የሪፖርቱ ምንጭ ይገልፃል፡፡ “በጥይት ተመትቶ ህይወቱ ያለፈውን ወገናችንን ደም ሳንበቀል አንቀመጥም ትምርቱም ይቅርብን” ብለው በርካታ ቁጥር ያላቸው የኦሮሞ ልጆች ትምህርታቸውን አቋርጠው እንደሚገኙ ሪፖርቱ ይገልፃል፡፡
ድል ለኦሮሞ ህዝብ !!
ገዳው የነፃነት ነው !!

No comments:

Post a Comment