Pages

የ2014 አዲስ አመት ከወጣቶች ነፃነት ንቅናቄ (QEERRO) የተላለፈ የነፃነት ትግል ጥሪ

ለመላው የኦሮሞ ሕዝብና በሁሉም አካባቢ ለምትገኙ የኦሮሞ ታጋዮች እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ፡፡
የኦሮሞ ሕዝብ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ በባርነት አገዛዝ ሲደርስበት የነበረው ግፍና በደል ወደር የለውም፡፡ በዚህም የተነሳ ሕዝባችን የፀረ-ባርነት ትግል በማድረግ ያልከፈለው መስዋትነት የለም፡፡ ታጋዮችና ሀገር ወዳዶች የባርነት ስርአትን በመታገል እስከዛሬ በከፈሉት የህይወትና የገንዘብ መስዋእትነት ዛሬ ላለንበት ሊያደርሱን ችለዋል፡፡
ታጋዮቻችን መስዋእት የሆኑለትንና የተደራጁለትን አላማ ከግብ ለማድረስ ሁሉም የኦሮሞ ሕዝብ በተለይ በአገር ውስጥና በውጭ ለነፃነት እየታገለ የሚገኘው ወጣት /ቄሮ/ በ2014 የፀረ-ባርነት ትግሉን በአንድነትና በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል ድልን የምንጎናፀፍበትና ስኬታማ የምንሆንበት አመት እንዲሆን መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

በ2013 እ.አ.አ የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሲያደርሰው ከነበረ በደልና ጭቆና በተጨማሪ ከዚህ በፊት የኦሮሞን ሕዝብ ጨለማ ውስጥ ለማስገባት በነፍጠኛ ስረአት ሲደረግ የነበረው ዘመቻ አሁንም እየታየ ነው፡፡ በተለይ በቅርብ ወራት ውስጥ ሲፈፅሙት የነበረው ድርጊት ፀረ የኦሮሞ ሕዝብ ነው፡፡ የሚኒሊክ መንግስት ስረአትን በመያዝ ለኦሮሞ ሕዝብ ያላቸውን ጥላቻና ንቀት እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ ይህ ሁኔታ የኦሮሞ ሕዝብ በደልን የሚያባብስ ስለሆነ በ2014 ከዚህ ድርጊት ፊት እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የወጣቶች ነፃነት ንቅናቄ ቄሮ የወያኔ መንግስትና የነፍጠኛ ስረአትን ይዘው በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በደል የሚፈፅሙትን ድርጊታቸውን በሁሉም አቅጣጫ ለመከላከል የነፃነት ትግል በመፈፀም ኦሮሚያንና ሕዝቧን ለመጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ መልኩ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡
አዲሱ አመት የነፃነትና የብልፅግና ይሁንልን፡፡
ድል ለኦሮሞ ሕዝብ!
የወጣቶች ነፃነት ንቅናቄ /ቄሮ/
ፊንፊኔ ኦሮሚያ
ታህሳስ 31/20013

No comments:

Post a Comment