Pages

"ከሕዝባችን ነጻነት የቀደማ አንዳችም ጉዳይ የለም!"- ቄሮ የኦሮሞ ወጣቶች ለነጻነት ንቅናቄ ወቅታዊ አቋም

 October 03, 2014 | ቄሮ የኦሮሞ ወጣቶች ለነጻነት ንቅናቄ
ከሕዝባችን ነጻነት የቀደማ አንዳችም ጉዳይ የለም!
የትግላችን ጅማሬዉና ፊጻሜዉ ፣ መነሻዉና መድረሻዉ ፣ዉጥኑናግቡ - ሁለነገሩ የሕዝባችንን ነጻነት ማረጋገጥ ነዉ።ይህ የሕዝባችን ነጻነት ሺዎች የተሰዉለት፣ሚሊዮኖች የሚዋደቁለት፣ኣእላፍ የታሰሩላትና የሚሰቃዩለት አሁንም ሚሊዮኖች ለገቢራዊነቱ የሚሻሙበት ታላቅ ዓላማ ነዉና ከሕዝባችን የነጻነት አጀንዳ የቀደማ ኣንዳች ጉዳይ የለንም -የሕዝባችን ነጻነት ከምንምና ከማንም የላቃ ብቸኛ ጉዳያችን ሆኖ እስከፊጻሜዉ ይቀጥላል።

የኦሮም ሕዝብ ከተወራራሽ ወራሪ ኃይሎች አገዛዝ ተላቆ ብሔራዊ ነጻነቱና ሰብዓዊ ክብሩ እስክረጋገጥ ድረስ ፤እንድሁም የኦሮሞ ነጻነትና የኦሮሚያ ሉዓላዊነት ዕዉን ሆኖ ብሔራዊ ሰንደቁ በዓለም ለይ ተገቢዉን ስፍራ እስከሚይዝ ድረስ ከተያያዝነዉ የፀረ ባርነት ፊልሚያ መስመር ለኣፍታም እንኳ ቢሆን የሚያዘናጋን አንዳች ገደድ (concern) አይኖረንም። መታሰራችን መገደላችን መሰደዳችን ኣልያም ብረት አንስተን ለነጻነት ፊልሚያ መዉጣታችን ለዚህ ክቡር ሰአብኣዊ ተልዕኮ ነዉና ምንጊዜም በኩራት እናስበዋለን።


የጭቆና መንበሩን የተቆጣጠሩ የዘመኑ ወራሪዎችም ሆኑ የቀድሞ ዐሃዳዊ መንግስት ናፋቂዎች በሕዝቦች የጸረ ባርነት ትግል የተናወጠዉን የአገዛዝ መንበራቸዉን ለማጥበቅ አልያም የፈረሰዉን የዐፄ ዙፋናቸዉን መልሶ ለማጽናት በመሻኮት ላይ ስለመሆናቸዉ በዉል እንረዳለን። ለዚህ ዓላማቸዉ ስኬት ደግሞ የሕዝባችንን የነጻነት ጥያቄ ለማደናቀፍ ኣሊያም ከተቻላ ደግሞ ለማምከን በገሃድም ሆነ በስዉር ፣ በተናጠልም ሆነ በጋራ ያልተቋረጠ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ለመረዳት የየዕለት እንቅስቃሴያቸዉን ከማጤን ያለፈ ሌላ ተዓማኒ መረጃ መፈለግ ኣያሻም።በመሠረቱ የኦሮም ሕዝብ የነጻነት ትግል ማንም ልገዳደረዉ የማይችል ደረጃ ላይ ስለመሆኑ ከነዚህ ኃይሎች ግንዛቤና ዕይታ የተሰወረ ነዉ ቢሎ ማሰብ ኣይቻልም። ሆኖም ግን መሠረታዊ አፈጣጠራቸዉም ሆነ የሚከተሉት የድንቁሪና መንገድ በተጨማሪ አስተዋይነት የራቀዉ የትምክህት አስተሳሰባቸዉ ዛሬም ራሳቸዉን ከነባራዊ ዕዉነታ ጋር ኣስታርቀዉ፣የሕዝቦችን መብትና ፍላጎት ተረድተዉ ኢምፓዬርቷን እያናጣት ላለዉ ሕዝባዊ ጥያቄ ዓለም አቃፋዊ ድንጋጌዎችን በተከተላ ስልጡን አካሄድ ኣዎንታዊ ምላሽ ለመስጠት ኣላስቻላቸዉም።ስለሆነም አሳፋሪና ወራዳ አካሄዳቸዉን የሙጥኝ ብለዉታል። ይህን በማድራጋቸው ያተረፉት ነገር ቢኖር የሕዝቦችን ሁለንተናዊ ሕይዋት ማቃወስና ኢምፓዬሪቷን መዉጫ ወደማይኖረዉ አደገኛ ቀዉስ ማምራት ብቻ ይሆናል።

ያምሆነ ይህ የሕዝባችንን የነጻነት ጥያቄ የሚጻረር ማንኛዉም አካል በኃይልም ሆነ ዬትኛዉንም አግባባዊ የአጸፋ እርምጃን በመጠቀም የማስቆም ኃላፊነት ይኖርብናል። በመሆኑም ይህንን ብሔራዊ ግዴታችንን ዕዉን ለማድረግ የሚጠበቅብንን ማንኛዉንም ዋጋ ለመክፋል ያለነዉ ጽኑ አቋም በጠመንጃ አፈሙዝም ሆነ እየታያ ባለዉ አስገዳጅ ስልጠና ኣሊያም በማንኛዉም የማሰናከያ ስልትፈጽሞ የማይታወክ መሆኑን በጥብቅ እናስገነዝባለን።ከንግዲህ በኋላ በህዝባችን ላይ የሚደርሰዉን ማንኛዉም ዓይነት ማሸማቀቅና ዉርደት ለማስቆም የቆረጣ ትዉልድ ስለመሆናችን የሚናረጋግጠዉ በተጠናከረ ተግባራዊ ድርጊት ጭምር ይሆናል።

የኦሮሞ ሕዝብ በተያያዘዉ ትግሉ ነጻ ይወጣል እንጂ መብቱን ከማንኛዉም አካል በችሮታ አይጠብቅም። የሕዝባችንን የትግል ፍሬን ስናስብ፣ በተለይ ደግሞ የትዉልዱን ብሔራዊ መነቃቃትን ስናስተውል የዚህ ትግል ግንባር ቀደም ተሰላፊዎች መሆናችን በእጅጉ ያኮራናል። ለዚህ ክቡር ተልዕኮ ስኬት የሚጠበቅብንን ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን ለወዳጅም ሆነ ለጠላት ስንግልጽ አሁንም ታላቅ ብሔራዊ ኩራት ይሰማነል። በመሆኑም ሕዝባችን በጋራ ክንዱ የጋራ ጠላቶቹን ድልነስቶ ለሁለንተናዊ ነጻነቱ እንዲበቃ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናደርጋለን። ነጻነት የመራራ ትግል ፍሬ ናትና!

ቄሮ የኦሮሞ ወጣቶች ለነጻነት ንቅናቄ
ድል ለኦሮሞ ሕዝብ!!
September 29, 2014

No comments:

Post a Comment