Pages

በባህር ዳር ከተማ አንድ ኢንግሊዛዊ ቱሪስት ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አለፈ

December 24, 2014 | Fana Broadcasting Corporate (TPLF's Propaganda Machine)

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በባህር ዳር ከተማ አንድ ኢንግሊዛዊ ቱሪስት ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አለፈ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ ድርጊቱ የተፈፀመው ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ነው።


በግድያው የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ የወንጀል ድርጊቱ እየተጣራ መሆኑንም ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው።

የሟቹም አስክሬን በሆስፒታል እንደሚገኝ ተመልክቷል።

በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት መንግስት የተሰማውን ሀዘን ለኢንግሊዝ መንግስትና ለሟች ቤተሰቦች ይገልፃል ብሏል።

ሁኔታውንም አጣርቶ የተደረሰበትን ውጤት መንግስት ይፋ እንደሚያደርግ ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው።

No comments:

Post a Comment