Pages

የቀድሞው የኦነግ መሪ ሌንጮ ለታ ODF'ን ይዘው ወደ አዲስ አበባ ለመግባት መዘጋጀታቸውን ገለጹ! የመንግስት ፈቃድ አግኝተው ይሆን?

January 28, 2015 | Voice Of Amercia Amharic (VOA)

የቀድሞ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር አባል የነበሩትና አሁን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር መሪ አቶ ሌንጮለታ፤ ትግላቸውን በሃገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለማከናወን ወደ አዲስ አበባ በቅርብ ጊዜ እንደሚጓዙ አስታወቁ።

ከዓመት በፊት ዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለውይይት ዝግጁ መሆናቸውን በደብዳቤ ያሳወቁት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር አመራር አባላት፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውይይት አድርገው ወደ ሀገር የመመለስ እቅድ ነበራቸው።

ከኢትዮጵያ መንግስት የተገኘው ውሳኔ ጊዜ በመውሰዱ፤ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ወደ አዲስ አበባ ለማምራት መወሰኑን የፓርቲው መሪ አቶ ሌንጮ ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment