Pages

ወያኔ ልክ መግባት ያለበት ትክክለኛዉ ጊዜ ኣሁን ነዉ!

February 15, 2015

ኣባይ ጸሃይዬ የተባለዉ የወያኔ ደፋር የኦሮሞ ህዝብ ላይ ያለዉን ንቀቱን ንዴትና ቁጣ በተቀላቀለበት የጋጠ-ወጥ ንግግሩ ኣጋልጧል። ከዚህ ንግግር ብዙ ነገር መረዳት ቢቻልም የማይካደዉ ነገር ግን የኦሮሞ ህዝብና ወያኔ ከምን ጊዜዉም የበለጠ የተፋጠጡበትና ለማያዳግም እልህ አስጨራሽ ግጭት የተጋለጡበት ወሳኝ ጊዜ ላይ መሆናቸዉ ነዉ።

ከፍንፍኔ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ወያኔ የገባበት ወጥመድ ተስፋ ኣስቆርጦት ኣንድ የመንግስት ኣካል ነኝ ሃገር እመራለሁ የሚል ባለስልጣን በስብሰባ መድረክ ላይ እንደ መንገድ ዳር ቦዛኔ ሲደነፋ መሰማቱ የዚህ ማረጋገጫ ልሆን ይችላል። "ልክ እናስገባቸዋለን" ብሎ የፍጥጫዉን መካረር ሲያበስር ዳግም የኦሮሞን ህዝብ በአንድነት እንዲነሳ የተዘጋጁ ይዋጣልናል ፉከራ ፎክሯል። የኦሮሞ ህዝብም ይህን ጥሪ ተቀብሎ ከወያኔ ጋር ላለበት የመጨረሻ ትግል መነሳት አለበት። "ዶሮ ጭራ ጭራ ታወጣለች ካራ ለሰዉ እንኳን አይደል ለራስዋ መከራ" እንዲሉ ወያኔ ባመጣዉ የኦሮሞን ሚስክን ኣርሶ ኣደር ኣፈናቅሎ ኣዲሲቱን ትግራይ በመሃል ኦሮሚያ ለመመስረት ባወጣዉ እቅድ ሰበብ የኦሮሞን ህዝብ በላዩ ላይ ኣስተባብሮ የራሱን ግብኣተ-መሬት ደግሷል።


ግድያ እስራት ጭቆና የኦሮሞን ህዝብ ወዲ ጸሃይዬ እንዳሉት ልክ አስገብቶ ባርነት አሜን ብሎ እንዲቀበል ቢያደርጉት ኑሮ የኦሮሞ ህዝብ እስከዛሬ ድረስ የተሰራበት ግፍ ኣንገቱስ ባስደፋዉና ልክ ባስገባዉ ነበር። ነገር ግን ግፉ እያበዛበት በሄደ ቁጥር የኦሮሞ ህዝብ በባርነት ከመኖር ይልቅ ለመብቱ እየታገለ መሞት መምረጡን ለማረጋገጥ ከኣፍ እስከ ገደፍ የታጠቀዉን አጋዚ ሰራዊት ያራዱት ብርቅዬ የኦሮሞ ተማሪዎች መስዋአትነት ኣብይ ማስረጃ ሊሆን በተገባ ነበር። በገደላችሁን ቁጥር እንጋፈጣችኋለን ባሰራችሁን ቁጥር እናርበደብዳችኋለን ባስፈራራችሁን ቁጥር እንደፍራችኋለን። ከደደቢት በረሃ ተነስተዉ የኦሮሚያን ማርና ወተት እንዲሁም ጮማ ኣልጠግብ ያሉ የወያኔ ቱባ ባለስልጣናት ከኛ ይበልጥ ማን ብለዉ በፈነጩት የኦሮሞ ህዝብ መካከል መዋረድ ያለባቸዉ ትክክለኛዉ ጊዜ ኣሁን እና አሁን ነዉ። በዚህ አጋጣሚ ለጌቶቻችሁ አሁንስ አንታዘዝም ብላች ሁ የወያኔን እቅድ ከማስፈጸም ታቅባች ሁ አባይ ጸሃይዬን ጸጉር ለማስነጨት ዳር ዳር ያላች ሁ የ ኦሮሚያ ከተማ ኣስተዳደር የኦህዴድ ባለስልጣናትም ጅምሩ ይበል ለሚያሰኝ ነዉና ኣትፍሩ እስከዛሬ በልታች ሁ ላስበላች ሁት ህዝባች ሁ የምትቆሙበት ታሪካዊ ግዜ ኣሁን መሆኑን ተረድ ታች ሁ ለህዝባዊ ትገል ተዘጋጁ።

የፍንፍኔ ጉዳይ የመሬት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ለኦሮሞ ህዝብ የማንነት የሀገር ባለቤትነት ጉዳይ ነዉና ትግሉ የሚጠይቀዉን መስዋእትነት ከፍሎ መብቱን የማስጠበቅ ግዴታ በኣሁኑ ትዉልድ ላይ የወደቀ የህልዉና ሃላፍነት ነዉ።

ትግሉ መራር ቢሆንም እዉነትን ይዞ የብርቅዬ ልጆቹን የማይተካ ህይወት እየበላ ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ የደረሰዉን የነጻነት ትግል ከግቡ ማድረስ ኣማራጫ የሌለዉ ጉዳይ መሆኑ መታወቅ ኣለበት። ስለዚህ የኦሮሞ ህዝብ በመካከሉ ያሉትን ማህበራው እና ፖለቲካዊ ልዩነቶች ወደጎን በመተዉ ራሱን የማዳን ትግል ላይ በተባበረ ሃይል መሰለፍ ያለበት ዛሬ ነዉ። ልክ ያጣዉን ወያኔ ልክ የማስገባት ትክክለኛዉ ጊዜ ኣሁን ነው።

ድል ለኦሮሞ ህዝብ

2 comments: