Pages

ኦሮሞነትን የፈራ ኢትዮጵያዊነት እንዴት የጋራ ማንነት ይገነባል?

October 30, 2015 | Oromedia

ይድረስ የአንድነት ደጋፊ ነን ባይ የጠባብ ኢትዮጵያዊነት ልክፍተኞች ስለአንድ ኢትዮጵያ ሰባኪዎች እኔ የብሄር ብሄረሰብ ጥላቻ የለብኝም። ከማንኛውም ብሄር ሀይማኖት ለሀገሩ ትልቅ መስዋዕት የከፈለ ለኔ ጀግና ነው።
ሆኖም ግን አንድ ግለሰብ የኦሮሞ መገለጫ የሆነን ነገር ሲጠቀም ስለምን ያወግዙትና የጥላቻ ስድቦች ይሰነዝሩበታል? ኦሮሞነትን የፈራ ኢትዮጵያዊነት እንዴት ነው የጋራ ማንነት የገነባች ሁሉም የእኔ እማማ ኢትዮጵያ ብሎ ዳር ድንበሯን አስከብሮ ህልውናዋ ተጠብቆ የምትዘልቀው ?

mahi
በብሄር አናምንም ይሉና ስለራሳቸው የወጡበት ብሄር ግን ታላቅነት ጀግንነት የታሪክ ሀፍታምነት ሲሰብኩን ይቆዩ እና ግና የኦሮሞ ልጅ ግና ኦሮሞ ሲል ይናደዳሉ። የኦሮሞ ስም ሲያዩ ስሙን እንዲቀይርላቸው ሁሉ በረዘመ ምላሳቸው ያንጓጥጣሉ ወይሥ ብሄርን መጥራት ለናንተ ብቻ ይፈቀዳል ?
እኔ የሌላውን ብሄር ሳልቃወም አክብሬ የራሴን ባህል ቋንቋ ታሪክ ብናገር በሚሴጅ በኮመንት ማንነቴን በተመለክተ በሥድብ አጠገቡኝ ዘረኛ ጠባብ የሚል ታርጋ ለጠፉብኝ አሜን ብዬ ተቀበልኩ ።
እውነት እንነጋገር እናንተ ድሮም,,,,,,,,,!ኦሮሞን የሚሠድቡና የሚያብጠለጥሉ ሰዎች ዝምብዬ ሣስባቸው በራሳቸው ትምክተኛ የዘረኝነት አንቡላ ሰክረው እብደት ውስጥ የገቡ ፣በኦሮሞ ማንነት የቅናት ዛር አናታቸው ላይ ወጥቶ የሚጋልባቸው ፣በቃ ምክንያታዊ ያልሆኑና በስማበለው ብቻ የሚነዱ በስጥ እንግዲ ተረት የእውቀት ማማ ላይ የደረሱ ከነሱ ውጭ ምንም አዋቂ ያለ የማይመስላቸው መውጫ መግቢያ አጥተው የሚኳትኑ ገልቱ ልበቢሶች ይመሥሉኛል!።
befeke
ያስተውሉ! የዛሬዋ ኢትዮጵያ ለትምክህተኝነት የሚን ጥግ የላትምና ከትምክህተኝነት ይፅዱ! ታሪክን ጠንቅቀው የሚያውቁ,,,,,,,,,! እውነትን አለምን የሚያጠኑ የተማሩና የተመራመሩ,,,,,,,”እንዲ”ያነሡታል በክብሩ በቁም ነገሩ! ኦሮሞነቴን ዝም ብዬ ሣሥበው ደስታ መላ አካላቴን ይወረዋል ኡፍ በቃ ሲያረካ!!!!!!!!!
ኦሮሞ አባቴ፤እናቴ፤አያት ቅድመ አያቴ,,,,,,,,,,!ዘር ሀረግ ማህፀን እትብቴ ኩራት ማንነቴ ከምንም የማላነፃፅረው,!ብልጫ ማንነቴ ደስታ ፍስሃዬ የሥከለት ሞቴ በቃ ኦሮሞነቴ ! ጠባብ ዘረኛ መባሌ ካልቀረ እደዚ እርፍ በሉ!

No comments:

Post a Comment