Pages

የግዢ እና ሽያጭ ማቆም አድማ ጥሪ ከጷግሜ 1- መስከረም 2፣ 2009

#OromoProtests የግዢ እና ሽያጭ ማቆም አድማ ጥሪ
ቀደም ብለን እንዳስታወቅነው ለቀጣዩ ዘመቻ የተመረጠው ሳምንት በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ነው። ስለሆነም ዘመቻው የስርዓቱን ኢኮኖሚ ከማድቀቅም አልፎ የኦሮሞ ህዝብ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ግንድ መሆኑን የሚያሳይበት ይሆናል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ ለጨቋኙ ስርዓት ያደሩ ነጋዴዎችንም ለመለየት ይጠቅማል ዘመቻው። በዚሁ መሰረት ከጳጉሜ አንድ እስከ መስከረም ሁለት 2009 ዓ.ም የሚቆይ በስርዓቱ ኢኮኖሚ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ይደረጋል። ዓላማውም የስርዓቱን ኢኮኖሚ በመምታት የጭቆና አቅሙን ማንኮታኮት ይሆናል። ወቅቱ የዘመን መለወጫና የኣረፋ በዓላት ወቅት ነው። ባሮጌው ዓመት የኦሮሞ ህዝብ ለነጻነቱ ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ ብዙ ልጆቹን ሰውቶ ሺዎችን ላይ ደግሞ የኣካል ጉዳት ደርሷል። በኣስር ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በስርዓቱ አስቃቂ እስር ቤቶች አሁንም እየተሰቃዩ ይገኛሉ።
ስለሆነም በዓሉ እነዚህን ጀግኖቻችንን እያሰብንና እነርሱ የተሰውለትን ዓላማ ለማሳካት በሚያስችል መልኩ ትግላችንን እየቀጠልን ነጻነታችንን የምናፋጥንበት እንጂ በጭፈራና በከበርቻቻ የምናሳልፈው አይሆንም። በዚሁ መሰረት የሚወሰዱት እርምጃዎች፥

1) አርሶ አደሮቻችን እህል፣ የእርድ ከብት፣ ዶሮ፣ እንቁላል፣ ቂቤ፣ ቅመማ ቅመሞች፣ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች የመሳሰሉትን በሳምቱ ለገብያ ባለማቅረብ (ጨው፣ ስኳር ፣ዘይትና ሌሎች መሰረታዊ የቤት ውስጥ ፍጆታዎችን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀድሞ ባሉት ቀናት በመግዛት)፤
2) ነጋዴዎቻችንም ከላይ የተጠቀሱትን የበዓል ፍጆታዎች ፊንፊኔን ጨምሮ ወደ ሌሎቹ ትልልቅ ከተሞች ከማቅረብ በመቆጠብ፤
3) ይሄን ዘመቻ ለማክሸፍ የሚንቀሳቀሱ ለስርዓቱ ያደሩ ነጋዴዎችንም መንገድ በመዝጋት ጨምሮ በተቻለው መንግድ ሁሉ በማደናቀፍ፤
4) በከተሞችም ሆነ በገጠር የሚኖረው ህዝባችን በነዚህ ቀናት ምንም ነገር ከመሸመት መቆጠም። ምግብ ቤቶች፣ መዝናኛ ቤቶች፣ ሻይ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች ወዘተ….ሁሉ ገብቶ ምንም ዓይነት ወጪ አለማውጣት። በቤት ውስጥ ከዘመድ ወዳጅ ጋር ተስብስቦ ሰማዕቶቻችንን ማሰብ። እነሱ የተሰውለትንም ትግል እንዴት በፊጥነት ወደፊት ማስቀጥል እንደሚቻል መወያየት። እንደየእምነታችን ወደ እምነት ቤቶች ሄደን ጸሎት ማድረግ። እዛም በጉዳዩ ላይ በጋራ ሆነን መወያየት።
ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው፣ ሳምንቱ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ወቅት ስለሆነ፣ እነዚህን እርምጃዎች በመውሰድ ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በማድረስ የጭቆና ጉልበቱን ማሽመድመድ ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ የኦሮሞን ህዝብ የኢኮኖሚ ዋልታነት ከማሳየትም አልፎ ለስርዓቱ ያደሩና የህዝብ ወገንተኘት ያላቸውን ነጋዴዎች ለመለየት ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል።
ስለሆነም በህዝባችን ላይ እየተካሄደ ያለውን የግፍ የጅምላ ግድያ እና እስራት የምትቃወሙ ሁሉ በዚህ ሰላምዊ ግን ውጤታማ የትግል ስልት እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጠይቃለን

No comments:

Post a Comment