Pages

ዘረኝነት—የሐይማኖት መሪዎች መለዮ!

ግንቦት 17, 2017 | በዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ*

በምድረ ኢትዮጵያ ዘረኝነት የሚሉት ወረርሽኝ ከምንም ጊዜ በላይ ስርጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱ የአደባባይ ምስጢር ነው። በተለይ በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ያለ ምንም በቂ ምክንያት አንድን ሕዝብ ወይም ብሔር አብዝተው የሚጠሉበት ሁኔታ በግልጽ እያየንና እየሰማን እንገኛለን። እንድህ ዓይነቱን ኃላ-ቀር እና የወረደ አስተሳሰብ አጥብቀን መዋጋት ይኖርብናል። ምላሱን አዳጠው መሰለኝ የሆነ ቀን አንድ ሰውዬ፡-
‹‹እነኝህ ለማኝ ትግሬዎች ችግር አለባቸው!›› ስል በገዛ ጆሮዬ ሰምቼ ኖሮ፤

‹‹ችግር ያለው ትግሬ፣ ካምባታ፣ ኪኩዩ፣ ኦሮሞ፣ ዶርዜ፣ አማራ፣ ሃድያ፣ ጉራጌ፣ ሉዎ፣ አሻንቲ….አይደለም! ችግር ያለው የሰው ልጅ ራሱ ነው፤ የሰው ልጅ ራሱ ለራሱ ጥያቄ ነው፤ ጭፍን ጥላቻ የበለጠ ያራርቀናል እንጅ የትም አያደርሰንም! የጥቂት ሰዎች ድርጊት የአንድ ብሔር ማንነት መገለጫ ሊሆን አይችልም፤ ለምሳሌ፡- አማራ—ነፍጠኛ፣ ኦሮሞ—ወራሪ፣ ጉራጌ—አጨበርባሪ…ወዘተ እያሉ ሕዝቡን ግራ የሚያጋቡ ሰዎች አሉ፤ አንድን ሕዝብ ስብናውን መወረፍ አግባብነት የለውም፤ እናም የቅድመ-ጥቅላሎት ሕፀፅ ፈጽመሃል…›› አልኩት!
እንዳለጌታ ከበደ ይህንን ጉዳይ እንድ ስል ነበር የታዘበው፡-
‹‹አንዳንዱ የዚህ ትውልድ አባል- ከአባቶቻችን ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው መሰረት ልበል?) የስድብ ሃብታም ነው፤ የሚተርበው ብሔር አያጣም፤ ሌላውን አሳንሶ አስጐንብሶ ካላሳየ እሱ ቀና ቢል እንኳን የሚታይ አይመስለውም፤ ልቡ በነቀፌታ የተሞላ ነው፤ አንዳች የስድብ መንፈስ-በየቤቱ- በየቤተመንግስቱ- በየቤተ ክርስትናውና በየቤተ እስልምናው ሰፍኗል፤ የሆነውን ብሔር ለይቶ፣ የሆነውን ወገን አግልሎ፤ ‹እኛ ካልተሳተፍንበት የልማት እስክስታው አይሰምርም፤ እኛ ካልደሰኮርንለት አምላክ ቸርነቱን አያዘንብም› ማለት የተለመደ እየሆነ ነው! ለመጪው ትውልድ ‹በደም› የሚመለስ የቤት ስራ እየተውን ያለ ይመስለኛል፤ የመጪው ትውልድ አባላት እኛ በመጣንበትም ሆነ አባቶቻችን በተመላለሱበት የመሰዳደብ መንገድ ባይሄድ እንመርጣለን፤ እኛ ፈትለንና ገምደን ያቆየነው፣ አለባብስን ያረስነው ነገር ነገ ከነገ ወዲያ ‹… ያልተዘጋ ፋይል አለ!› ብለው በጥይት ቋንቋ እንዲነጋገሩ መፍቀድ የለብንም- ሰርተን በቆየንላቸው መንገድ ደም እንዳያጐርፍበት፤ ሰርተን ባቆየንላቸው ተቋማት ስድብ እንዳይፈበረኩበት ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል፡፡ አዎን፤ ሁላችንም ስድቦች ወደ መጡበት የሚመልስና ወደሚመለከተው ክፍል የሚያዘዋውር ጽ/ቤት በየህሊናችን ልናቋቁም ይገባል፤ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ በብዙዎች ልቦና ላይ የማይታይ ቁስልና ሰንበር እንዲታተም አድርገናልና!››
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ግን የእግዝአብሔርን ሕዝብ እናገለግላለን የሚሉ የኀይማኖት አባቶች የችግሩ አካል በመሆን ‹ወንገልን› በ‹ወንጀል› ለውጦታል። እነኝህ ፈርሳዊያን እና የሕግ መምህራን ፓስታ እየበሉ ወይንም ቢራ እየተጐነጩ ይህንን ጉዳይ ፈጽሞ አይወያዩበትም ማለት አይቻልም፤ ጠንቅቀው ነው የሚያውቁት—የእኛ አድርባዮች! ነገር ግን፣ እስከ ዛሬ ድረስ ዘረኝነትን በግልጽ ለመተቸት አይደፍሩም። አንድ የኀይማኖት መሪ የወጣለት ዘረኛ ሆኖ እያሌ ዓይኑን በጨው ታጥቦ እንዴት ‹‹እግዝአብሔር ፍቅር ነው›› በማለት ይሰብካል? ያሳፍራል እኮ! አንድ ቄስ ወይም ፓስተር በአጠገቡ ካለው ወንድሙ ጋር ሠላም ሳይፈጥር ‹‹የእኛ እግዝአብሔር የሠላም አምላክ ነው!›› ብሎ ክላሽ ማንጣጣት ነውር አይደለም እንዴ!? የጥምቀት ውሃ ከሰው ልጅ ባህል ‹በላይ› መሆኑን ያልተቀበለ/ያላመነ አንድ አገልጋይ ‹‹ሁላችንም በምስጢረ ጥምቀት የእግዝአብሔር ልጆች ሆነናል›› ብሎ ቤተ-መቅደስን ማጣበብ ስበዛ ሌብነት፣ ሲያነስ ደግሞ ድንቁርና ነው! ሌብነት ይብቃን አቦ!
ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ በሃይመኖት ተቋማት ውስጥ ያለአግባብ መበልጽግ ባሕል ከሆነ ፤ የመልካም አስተዳደር እጦት ከተንሰራፋ ፤ የውሸት ባሕል ከነገሰ፤ አድሏዊነት፣ ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ ጨቋኝነት ሥር ከሰደደ፣ በገዳማት ውስጥ በሠላምና በፍቅር አንድ ላይ አብሮ መኖር ካልተቻለ፣ መደማመጥና መነጋገር ጠፍቶ መናናቅ ብቻ ከሆነ፣ የአብሮነት መንፈስ የሚባል ነገር ከጠፋ፣ ሥራ የሚከፋፈለው በዝምድና እና በዘር ከሆነ ቤተ-ክርስቲያንን የሌቦች ዋሻ ሆናለች ማለት ነው!
ስለዝህ፣ ዘረኝነት በግልጽ መተቸት ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል። ለምን ይዋሻል! ሕዝቡ ቆንጨራ እስከሚያነሳ መጠበቅ የለብንም! በሩዋንዳ ምድር በተደረገው የዘር ጭፍጨፋ የቄሶች (እኔ መቀሶች ነው ሚላቸው!) እጅ ነበረበት። በእርግጥ እነኝህ የኀይማኖት መሪዎች ትምህርት ቤት ተመላለሱ እንጅ አልተማሩም፤ መጽሐፍና ማንበብ የቻለ ሁሉ ‹ተምሯል› ማለት አይደለም! እንዴታ! የሰባት ዓመት የዩኒቨርስቲ ትምህርት የአንድን ሰው አስተሳሰብን ካልቀየረ እኮ የጭንቅላት ጥቅም ለ‹ቆብ› ብቻ ነው የሚሆነው! አርስጣጣልስ (Aristotle) ልክ ነበር— ‹‹ልብን ሳያስተምሩ ጭንቅላት ብቻ ማስተማር ዋጋ-ቢስ ነው!››
የሆነ ሆኖ አጐስቲን ካሬኬዝ (Augustine Karekezi) የሚባል አንድ ኢየሱሳዊ ቄስ (a Jesuit priest) የሩዋንዳውን አሳዛኝ ክስተት በምገርም ሁኔታ እንደሚከተለው አስፍሮ ነበር፡-
“My faith as a Christian has been affected seriousely, in the sense that I cannot realize that such evil could happen in a country where so many people are Christians and where there are so many Catholics, over sixty five perecent, with such influence in education. What have we been doing as Christians and as priests? How can we preach the love of God, the compassion of God, in this situation? All these questions derive from an experience of the deep mystery of evil, evil that is so consistent and so strong that its power is prevailing”
ስለዝህ፣ የሃይማኖት አባቶች ትልቅ ኋላፍነት አለባቸው! ሕዝቡ በቆንጨራ እየተጨራረሰ ዝም የሚትሉ ከሆነ፣ በፈጣሪና በሕግ ፊት ተጠያቅዎች ናችው። እምነትና ፀሎት ብቻ በቂ አይደለም። ሰይጣንም እኮ እግዚአብሔር የዘለዓለም ኗር መሆኑንና ታላቅ አምላክ መሆኑን ያምናል። ግን መልካም ሥራ የለውም፤ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው! የእግዝብሔር ቃልም የሚላችው ይህንኑ ነውና፤ “ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ ተጸይፌውማለሁ፤ የተቀደሰውም ጉባኤአችሁ ደስ አያሰኘኝም። የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለምስጋና መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም።የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመሰንቆህንም ዜማ አላደምጥም። ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ።” (አሞጽ 5፤ 22-24) ይህ ማለት፣ አንድም፣ የሚተሰብከውን ኑር እንጅ፣ ፈሪሳዊ አትሁን፤ ሁለትም፤ ‹‹ከመጠምጠም መልካም-ሥራ ይቅደም›› ማለት ነው። ‹‹ፂም በማሳደግ ቢሆን ፍየል ትሰብክ ነበር›› እኮ!!
አዎን! በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ውስጡን ዘረኝነት የሚሰብኩ ወይም የሚያቀነቅኑ ቀጣፊ ቄሶች አሉ፤ እንድ ዓይነቱን የአስተሳሰብ ሽርሙጥና ከወድው በቆራጥነት መዋጋት አለብን፤ አዎን! እነኝህ አስመሳይና አድርባይ ‹መቀሶች› እሳት ከሚተፋው የፍልስፍና ብእር ማምለጥ አይችሉም! እየተከታተልን እናጋልጣለን!
ሠላም፣ ፍቅርና አንድነት ለሀገራችን ኢትዮጵያ እያልኩኝ፣ በሃይለመለኮት መዋእል ግጥም ልሰናበታቸው!
ምን ጠቀመዉ ቃየል—የመሳሪያ ቋንቋሰጠመ ጠፋ እንጂ—ባቤል ደም አረንቋመኢኑም አባተ—ሰመረ መረሳኦቦንግ አብዱል ከሪም—ጋቸኖ ቶሎሳአብረኸት ምንትዋብ—ኛዳክም ጋዲሴበላህ በነብዩ—በሶስቱ ስላሴሰይፉም ዶማ ይሁን—ሞርተሩም አንካሴ
*Yoseph Mulugeta Baba (Ph.D.)

No comments:

Post a Comment