Pages
▼
መታሰቢያነቱ ለአምባገነኑ መሪ ዘመድ አዝማድ ወይም ጓደኛ ሳይሆኑ የኢትቪ ካሜራ ፍትለፍት ደረታቸዉን ለደቁ አስመሳዮች
በጌታቸዉ ካሳ
September 5/2012
ስትፀልይ አልነበር አድማ ስትመታ???
ተበደልኩ ብለህ በወሬ ሹክሹክታ!!!
መለስ እንዲወገድ ከሀገር እንዲወጣ!!!
ስታምፅ አልነበር በሰልፍ ስትወጣ?
መብረቁ እንዲወርድ የእግዚአብሔር ቁጣ??
አሁን እዉን ሆኖ ቁርጥ ቀን ሲመጣ!!
ደረት እየደቁ እዬዬ ኡኡታ!!
ባደባባይ ወጥቶ በለቅሶ ድንፋታ
ሾካካ ወረኛ አድር ባይ ወስላታ
የአበሻ ፀባይ ግን አባጣ ጎርባጣ
መሪ ባይኖረንስ ከዚህ ሁሉ ጣጣ
No comments:
Post a Comment