Pages

ዶክተር ሃይለማሪያም ላሬቦ ምርኮኛነት በአካል ብቻ ሳይሆን አምሮም ጭምር ነው። ክፍል 3

ከቃሉ ኩሳ

ያለፉትን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ክፍል አንድ እና ክፍል ሁለት
ክፍል 3: ዶክተር ሃይለማሪያም ላሬቦ ምርኮኛነት በአካል ብቻ ሳይሆን አምሮም ጭምር ነው።
አንባቢዎቼ እንዲረዱልኝ የምፈልገዉ በክፍል ሁለት የጠቃቀስኩት ታሪክ መሰረቱ የዐፄ ሚኒልክ ሰራዊት ሰለባ በመሆን ከምባታዉ ሓዲያዉ ሲዳማ ወላይታና ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች በሙሉ ከመሬታቸዉ ተፈናቅለዉ ገባር በመሆን ለሽያጭ ስደተኛ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን በሁለተኛ ዙር የኢጣሊያን ወረራ ጊዜ በአብዛኛዉ ህዝብ ወደ ይዞታዉ ተመልሶ ነበር። በመሆኑም በዐፄ ኃይለ ስላሴ ከእንግሊዝ መልስና የአገሪቱ አገዛዝ ጊዜ ወደ ይዞታቸዉ ተመልሰዉ የነበሩ የተጠቀሱት ብሔሮች በንጉሱ ሹመኞችና የሃበሻ ሰፋሪዎች በድጋሚ ከይዞታቸዉ ይነቀላሉ። ይህን ድርጊት ለንጉሰ ነገስቱ እንዲያመለክቱ የሀገር ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎቹን ከነ እጅ መንሻ ጭምር ወደ አዲስ ኣበባ ይልካሉ።

1 comment:

  1. የተዛቡ አስተያየቶችንና በቀደሙ ስርዓት የተሰሩ ህፀፆችን በመለየት አዲሱ ትውልድ በነፃነትና በእኩልነት ሊኖርባት የምትችል ሀገርን መገንባት በዚህ ትውልድ ላይ የወደቀ ሸክም ነው፡፡ አያቶቻችንና አባቶቻችን ከነስህተቶቻቸው የማንም ቅኝ ገዢና ባእድ ወራሪ ይሁንታ የሌለበት ነፃ አገር መስርተው አስረክበውናል፡፡ እኛም ይህችን ከነብዙ ችግሯ የተረከብናትን ሀገር ለእኛ በምትመች መልኩ ማዘጋጀት ሀላፊነት አለብን፡፡ ይህን ለማሳካትም በግልፅና በሰከነ አዕምሮ መወያየት ይኖርብናል፡፡ ነገር ግን እየሆነ ያለው የጋራ እሴቶቻችንን ሆን ብሎ ወደ ጎን በማድረግ ልዩነቶችን ማራገብና ጥፋቶችን ብቻ በማጉላት እርስ በርስ የማባላት እኩይ ምግባር ትኩረት ተሰጥቶበት እየተሰራ ነው፡፡ በዚህ ተጠቃሚ የሚሆኑት ደግሞ አያቶቻችን ያሸነፏቸው ባዕዳንና የእነሱን ፍርፋሪ ዶላር ለመቃረም የተዘጋጁ ባንዳዎች እንጅ ብዙሀን ህዝቦች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ይህንን ጉዳይ በጊዜ በመንቃት ልንታገለው ይገባል፡፡ ታሪክን ልንማርበት እንጅ ልንማረርበት አይገባም፡፡ ለዚህ ትውልድ የሚጠቅመው አሁን ያለው ጊዜ እንጅ ያለፈው ጊዜ አይደለም፡፡ ሆኖም የስልጣን ጥማት ያለባቸውና ያልተሳካላቸው የ “ያ ትውልድ “ አባላት የዚህን ትውልድ ጊዜ እየሰረቁና እያባከኑት ይገኛሉ፡፡ ይህ ትውልድ እንደ ቌጥኝ በከበደ ተደራራቢ ችግር ተተብትቦ በተያዘበት ወቅት ከ100 አመት በፊት የነበረን ሁኔታ አሁን ያለ ለማስመሰል ደፋ ቀና ማለት የትውልዱን ስቃይ ለማራዘም ካልሆነ በስተቀር ምን የሚፈይድለት ነገር አለ?
    የኦሮሞ ጀግኖች የአባታቸው ስም እንዲነሳ አልተደረገም የሚል ወቀሳ ማቅረብ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ካለመገንዘብ እንጅ ሆን ተብሎ ኦሮሞን ለመጉዳት የተፈፀመ አይደለም፡፡ ራስ አሉላ አባነጋ የአባታቸው ስም እዚህ ውስጥ የለም የሚጠሩትም በፈረሳቸው ስም ነው፤ ምክኒያቱም የወቅቱ አሰራር ይህ ስለሆነ፡፡ ራሳቸው ምኒልክስ ቢሆኑ አባ ዳኘውና እምየ በሚባሉ ተቀፅላዎች እንጅ መቸ ነው ምኒልክ ሀየለመለኮት ተብለው የተጠሩት ? የዛሬዎቹ ነፃ አውጪዎችስ የራሳቸውን ስም እንኳ ለመጠቀም ፍላጎት የላቸውም፤ ለመሆኑ ሌንጮ ለታ እውን ሌንጮ ነው ስማቸው? በወቅቱ የክብርና የሞገስ መገለጫ እንጅ እናንተ እንደምታስቡት ወይም እንዲሆን እንደምትፈልጉት አንድን የህብረተሰብ ክፍል ለይቶ ለመጉዳት የተደረገ አይደለም፡፡ ለነገሩ ይህን በማለታችሁ ትዝብት ውስጥ ከመውደቅ አንዳችም ትርፍ አታገኙም፡፡ ትውልዱ ብዙ የሚያስጨንቀው ጉዳይ አለው የእናንተን የነተበ ፖለቲካ የሚያዳምጥበት ጊዜ የለውም፡፡ ይህን በማለታችሁ የኦሮሞ ህዝብ የሰራውን ታሪክ ከማደብዘዝ ውጭ የምትፈይዱት ጉዳይ አይኖርም፡፡ ታሪክ እንዳለ ይቀመጥ፡፡ ከዚህ ውጭ እንዲህ ለማድረግ ተፈልጎ ነው እየተባለ መተርጎሙ ተጨማሪ ስቃይና መከራ ከመጫን ውጭ ለትውልዱ የሚጠቅም ጉዳይ የለውም፡፡
    እዚህ ጋ አንድ ግልፅ ጉዳይ አለ የመከፋፈልና ህዝብን በህዝብ ላይ የማነሳሳት ሴራ ከሽፏል፤ እነ አቶ መለስም ቢሆኑ ስልጣንና ሃብት አገኙ እንጅ የኢትዮጵያን ህዝብ ልብ ሳያገኙ ነው ይህችን ምድር የተሰናበቷት፡፡
    እባካቹ እንደ ዘመኑ፤ እንደ ትምህርት ደረጃችሁና አንደ እድሜያችሁ አስቡ፡፡

    ReplyDelete