በግርማ ታደሰ |ጥቅምት 2005|ኒያግራ ፎልስ ኒው ዮርክ
አንተ ጥቊር ድንጋይ እንቅፋቴ ሆነህ
ቢመስልህ ነው እንጂ መንገዴን የዘጋህ
ብታውቅማ ኑሮ የታመቀ ሃይሌን
ያመታት ቁጭቴን ያንደረደረኝን
ያያቶቼን ጅምር ለዚህ ያበቃኝን
ያባቶቼን ምሬት ያንገበገበኝን
የጓዶቼን ግፊት እረፍት የነሳኝን
ደካማው ትግልህ መድረሻዬን ላይገታ
ዘወር ትል ነበር ለቀህ ይሄን ቦታ
ግና አንተ ድንጋይ አቅሜን ያልተረዳህ
የነፃነት ጥማት ትርጉሙ ያልገባህ
ጉዞዬን ላታቆም መሃል ተደንቅረህ
ለሂደቴ ታሪክ ድምቀት ትሰጣለህ
No comments:
Post a Comment