Recording devices found hidden in PM Hailemariam Desalegn's bedroom and living room

26 December 2012  | By Minilik Salsawi

Remote listening devices were found inside Ethiopian Prime Minister Hailemariam's bedroom and living room by his daughter. The Hailemariam family is now in distress.

ከጠቅላይ ሚ/ር ሃይለማርያም መኝታ ቤት እና የቤተሰብ ሳሎን ውስጥ ምስጥራዊ የድምጽ መቅጃ ተገኙ !!!


ከቤተ መንግስት ታማኝ ምንጮች ዛሬ ባገኘሁት መረጃ መሰረት የአቶ ሃይለማርያም ትንሽዋ ልጅ እጹብ ባባትዋ መኝታ ቤት በረቀቀ መንገድ ከአልጋው ተያይዞ የተቀመጠ ምስጢራዊ የድምጽ መቅጃ በማግኘትዋ...ይህንን ተከትሎ በተደረገው ከፍተኛ ፍተሻ በቤተሰቡ ሳሎን ውስጥም ሌላ ተመሳሳይ መገኘቱን የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ተናግረዋል::

ቤተሰቡ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደገባ እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት ይህ መገኘቱ ለሌላ የስነልቦና ቀውስ እንዳይዳረጉ በመስጋት የሃዋርያ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከነተከታዮቻቸው ለጽሎት በጠ/ሚ መኖርያ ከትመዋል::

ምንጮቼ እንዳሉኝ በከፍተኛ አይነቁራኛ የሚጠበቁት ሃ/ማርያም እያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸው በየሰአቱ ለ ሕወሓት አመራሮች ወኪል ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ሪፖርት ይደረጋል:: ከጥቂት ቀናት በፊት ሶስና ለተባለች ልጃቸው ካልታወቀ ሰው... በሞባይል ቁጥርዋ በኢንተርኔት መስመር ተደውሎ "አባትሽ የስልጣን መልቀቂያ እንዲያቀርብ ግፊት አድርጉበት ..." የተባለች ሲሆን ይህንን ንግግር ሪኮርድ አድርጋ ለአባትዋ እንድታሰማ በታዘዘችው መሰረት አድርጋዋለች:: ይህንን ደሞ ሊያደርግ የሚችለው ሕወሓት ብቻ ነው ሲሉ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

የቤተሰቡ ምንጮች እንደሚሉት አቶ ሃ/ማርያም "...እነዚህ ሰዎች ሊያሰሩን አልቻሉም:: ከጌታ ሊያጣሉኝ ነው" ሲሉ ተሰምተዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከቀድሞው ወድጆቻቸው ጋር ተገናኝተው በነበረ ጊዜ ሕወሃት ሊያሰራቸው እንዳልቻለ PM Hailemariam Desalegn Expresses Frustration to Close Confidants  በማለት  Ethiopian Review ገልጿል።

የወታደሩን ክፍል እና ቢሮክራሲውን በተለየ የተቆጣተሩት ህወሃቶች አቶ ህ/ማርያም ምንም አይነት ዉሳኔ እንዳያደርጉ ተጽእኖ ፈጥረውባቸዋል ሲሉ አንድ ወዳጃቸው ተናግረዋል:: በደህንነት የተከበቡት እኚህ ምስኪን ሰው እንደ በላይ ተቆጣጣሪ ሃገራዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ሪፖርቶችን በወቅቱ እንደማያገኙ ተናግረዋል::


አቶ ሃይለማርያም ለፖለቲካ እስረኞች ምህረት ማድረግ እየፈለጉ በሕዋሓት ተጽእኖ ምንም ሊወስኑ አልቻሉም::

ከኤርትራ መንግስት ጋር ለአከባቢው ሰላም ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጠር ለመስራት ቢፈልጉም ህወሃት በዚህ ጉዳይ እንዳይገቡበት አስጠንቅቋቸዋል::

የአባይን ግድብ በተመለከት ሃይለማርያም የፖለቲካ መጭበርበር እንደተደረገባቸው እየተናገሩ ሲሆን መለስ ዜናዊ ካረፉ በኋላ ሕወሓት ፕሮጀክቱ እንዳይንቀሳቀስ እንቅፋት በመሆን የፕሮጀክቱ ገንዘብ እና ንብረት እንዲመዘበር አድርጉዋል... ሰራተኞች ክፍያቸዉን እንዳያገኙ ችግር ፈጥሩዋል ...እስከዛሬ የተሰበሰበው ገንዘብ እንዳይታወቅ እንቅፋት ሆነዋል ሕወሓቶች! እንዳሉት የቤተ መንግስት ምንጮች::

Source: Ethiopian Review

No comments:

Post a Comment