የወያኔ መንግስት የኦሮሞ ተማሪዎችን ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመሰብሰብ “የኢፌዲሪ መንግስት በአግባቡ እና በፍትሀዊነት የኦሮሞን ህዝብ እያገለገለ አይደለም እያላችሁ ህዝቡ በመንግስት ላይ እንዲያምፅ ለማድርግ አስተባብራችኋል ስለዚህ በአሸባሪነት ወንጀል ተጠያቂ ናችሁ” በማለት የከሰሳቸው ሲሆን ችሎት በማቋቋም በኦሮሞ ልጆች ላይ የረዥም እና የአጭር ጊዜ እስራት ብይን አስተላልፎባቸዋል፡፡ የመብት ጥያቄ ለመጠየቅና ሰልፍ ለመውጣት አስባችኋል በማለት ተማሪዎችን ማሰር እና ከትምህርት ገበታቸው ላይ ማባረር ለረጅም አመታት ሲፈፀም የቆየ ነው፡፡ “የኦሮሞ ህዝብ ሰልፍ ሊወጣ ነው ብላችኋል” በማለት ተማሪዎችን በህዝባዊ አመፅ አስተባባሪነት በመፈረጅ አሰቃቂ ድርጊት ከመፈፀሙም በላይ ኢ-ፍትሀዊ ውሳኔ ስለተላለፈባቸው ብሄራዊ የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ይህን ድርጊት በጥብቅ ያወግዘዋል፡፡ የወያኔ መንግስት የኦሮሞ ተማሪዎችን በማሰር እና የኦሮሞን ህዝብ ከመኖሪያ አካባቢው በማፈናቀል የፖለቲካ ችግሩን ለመፍታት መሞከሩ የህዝቡን የፀረ ባርነት ትግል መቀልበስ እንደማይችል እንገነዘባለን፡፡
የኦሮሞ ተማሪዎች በአንድ በኩል የፀረ ባርነት ትግሉን ለማቀናጀት አስባችኋል እየተባሉ እየተወነጀሉና እየታሰሩ የሚገኙ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ባልፈፀሙት ድርጊት አሸባሪ ተብሎ በመፈረጅ ትርጉም የሌለው ክስ ቀርቦባቸው የእስር ውሳኔ ከተሰጠባቸው መካከል፡-
- ተማሪ ደቻሳ ዊርቱ፡- ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ 8 ዓመት፣
- ተማሪ ኤቢሳ ራቴሳ፡- ከኦምቦ ዩኒቨርሲቲ 8 ዓመት፣
- ተማሪ አዳሙ ሽፈራው፡- ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 8 ዓመት፣
- አቶ በርሲሳ ለሚ፡- የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን 4 ዓመት፣
- መምህር ብርሃኑ እምሩ፡- የኮተቤ ኮሌጅ መምህር ሲሆን 4 ዓመት፣
- ተማሪ ጌቱ ሳቃታ፡- ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 3 ዓመት፣
- ተማሪ ሴና መረራ፡- ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 3 ዓመት፣
- ጋዜጠኛ አለሙ ተሾመ፡- የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን 3 ዓመት፣
- ተማሪ ዲሪብሳ ዳምጤ፡- ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 3 ዓመት፣
- ተማሪ ስለሺ ሶሪ፡- ከሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ 3 ዓመት፣
- ተማሪ አብዲሳ ጉደታ፡- ከመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ 3 ዓመት፣
- ተማሪ መሬሳ ኃ/ኢየሱስ፡- ከአዲስ አበባ የግል ኮሌጅ 3 ዓመት፣
- ተማሪ ደሜ ዘሪሁን፡- ከአዲስ አበባ የግል ኮሌጅ 3 ዓመት፣
- ተማሪ አብዲ ደረጀ፡- ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ 4 ዓመት፣
- ተማሪ አለማየሁ ራጋሳ፡- ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 3 ዓመት፣
- ተማሪ ደረጀ ጌቱ፡- 3 ዓመት፣
- ተማሪ ዳግም በቀለ፡- ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ 3 ዓመት፣
- ተማሪ ጌታቸው አበራ፡- ከሻምቡ 3 ዓመት፣
- ተማሪ ሻፊ ሰኢድ፡- ከጅማ ዩኒቨርሲቲ 3 ዓመት፣
- ጅሬኛ ደሳለኝ፡- 3 ዓመት ከ3 ወር፣
- አለማየሁ ረጋሳ፡- 3 ዓመት፣
- ሻሼ ሰኢድ፡- 3 ዓመት፣
- መምህር ለሚ፡- 4 ዓመት፣ እንዲሁም
- አለሙ ተሾመ፡- 3 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡
ብሄራዊ የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ የኢፌዲሪ መንግስት በኦሮሞ ላይ የሚፈፅመውን አረመኔያዊ ድርጊት እንዲያቆም በጥብቅ ያሳስባል፡፡
ትግሉ ይቀጥላል! የባርነት አገዛዝ ይወድቃል!
ድል ለኦሮሞ ህዝብ!
ብሄራዊ የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ
ነሀሴ 2013 አዲስ አበባ
No comments:
Post a Comment