ለአቶ ተክሌ የሻዉ ድንፋታ የተሰጠ መልስ: ክፍል ሶስት

ጃንዋሪ 17, 2014 ቃሉ ኩሽ

ክፍል አንድና ክፍል ሁለትን  ለማንበብ እዚህ ይጫኑ Part One and Part Two
 ክፍል ሶስት
አቶ ተክሌ የሻዉ ደጋግመዉ እንደነገሩን ከሆነ ኣማራዉ የሃገር ባለቤትና፥ ኦሮሞው ከህንድ ዉቅያኖስ ጠረፍ ተነስተዉ እንደወረሩዋቸዉና፥ ኣሁን ከኢትዮጲያቸዉ ኦሮሞችን ሊያባርሩ (ሊያስወጡ) ሃሳብ እንዳላቸዉ ነግሮናል። እንዲሁም ኦሮሞ የማንነት ችግር እንዳለዉና፥ ኣማራዉ ግን በማንነቱ እንደሚኮራ ገለጾልናል። የዉጭ ሃገር ዜጎች የሚጽፉት ኣማራዉ ኣማራዉ ወይም ሃበሾች የማንነት ችግር እንዳለባቸዉና ለኣፍሪካ መጤ ማህበረሰብ መሆናቸዉ ነዉ። የዚህ ምሳሌ የሚሆን ለሚኒልክ ወረራ እርዳታ ከመጡት የሩሲያ ዜጋ የሆነዉ ኮሎኔል አሌክሳንደር ቡላቶቭች እንድህ በማለት ማንነታቸዉን ገልጾታል።

"Amhara, or, as we have become accustomed to called them, "Abyssinians," constitute the latest, military and official population of these regions and are scattered among them rather uniformly. The origin of these people has still not been accurately established; and, with regard to this question, there are only hypotheses, often contradictory. Some authors call all three groups "Cushitic". Others, considering the first two cushitic, count the Abyssinians as of Semitic race. But to call Oromo and Sidamo descendants of Cush, the son of Ham doesn't mean anything at all. Why between the ones and the others is there such a huge difference with regard to culture and customs and language? where did the ones and the other come from?

I am too little acquainted with this question to take upon myself its resolution. But bringing my personal observations together with works I have read about this question, I believe the most probable explanation of the existing ethnographic grouping is as follows. 

Oromo, Somali and Adali (the latter two are steppe nomadic tribes who occupy the coast of the Red sea from the Ethiopian plateau) are all Cushites and occupied these places, it must be, in the time when the descendants of Mesraim occupied Egypt. They arrived here probably, by a dry route with their herds.

...The Finikiyane were driven toward The Mediterranean sea, and the other part toward the Arabian sea. This forced the migration of the latter to Africa across the the Bab-el-Mandeb Gulf. These immigrants occupied the Ethiopian plateau. They must have been culturally higher than the Oromo and drove the Oromo to the south.

From the fifteen century B.C, a vast movement Semites into Africa began. Between Ethiopia and the Arabian peninsula there were active trade dealings. They spread out on the plateau, but unevenly. In all probability, their port of entry, so to speak, the point for settlement of the plateau was Massawa. Therefore, we see the greatest concentration of Semites in northern Ethiopia: Felasha, Abyysinian Jews in the mountain of Semien, and Tigreans in Tigre. Southern Ethiopia was under the least influence of Semitism. From the Arabian peninsula, they brought with them the language belongs to the Hamitic root -- this is the present-day Geez language (literary). The Semites having mixed with the inhabitants of the country, changed their language and pronunciation and hence came about the present-day Amhara, or Abyysinian, or Amharic language. "Amhara" is the name that the Abyysinian gave themselves. The name "Abyysinian" accepted now in Europe, came about thus: Arabs call them "Habesha", which means "mixture" (confirmation of what we surmised that the Abyysinians are a mixed race.) The Portuguese changed the word "Habesha" to "Habeks", and German scholars "Habeks" made "Abessinen".

The Abyysinians, ruler of the country, call them selves "Amhara" in contrast to the inhabitants of Tigre. Through all the extents of my journey to the west, I didn't come across any areas that they had completely settled, but, on the other hand, in those most recently conquered, all the rulers and troops are Abyysinian. As said above, being a mixture of all the peoples who gradually occupied the country, they are not of one uniform type.

"History of Ethiopia- The name "Ethiopia," which the Abyysinians give to their country, is a Greek word and in translation means "Black face." Homer called all of central Africa "Ethiopia,"stretching from the Red sea and the Indian ocean to the Atlantic.  Diodor the Sicilian distinguished three Ethiopias: Western-- The Congo basin, High-- The present day of high-land Ethiopia, and Eastern- - Which included the lower, east coast of Africa."

ቡላቶቭች በመቀጠል ስለ ኦሮሞ ሲጽፍ እንዲህ ብሎ ነበር

"...The Oromo , The first mention of the name "Galla" in The Abyysinian History of The Kings ("Tarika Negest") is attributed to 1480 A.D. During the reign of Iskander, the Oromo made their first invasion into Abyysinian land and destroyed the monastery of Atones Maryam,"

The armaments of the Oromos consist of a metal spear (which has a different shapes among the various clans), a knife in his belt, and a large shield. Whether or not Oromo is a cavalryman depends on his place of residence. On the Plateau of Chalea, Wobo, Tikur, Shoa, and Leka, which are abundant in horses, all the Oromo are cavalrymen. In the mountains and forests of the west and south west regions adjacent to Kaffa, almost none are. The ambush, the night attack, the single combat-- those are the favorite tactics of the Oromo."

ይህ ከላይ የተጠቀሰዉ የኦሮሞ ጀግኖች ጋሻና ጦር በሩሲያኖቹ የሚኒልክ የጦር ኣማካሪዎቹ ተወስደዉ በተለያዩ የሩሲያ ሙዚየሞች ሲቀመጡ፥ በቮልጎግራድ (እስታሊን ግራድ)ሙዚየም ዉስጥ ያለዉን በ ፩፱፹ዎቹ እኔ ራሴ በዓይኔ ብሌን አይቻለሁ።

በሌላ በኩል የሚኒልክን የመቶ አመት የሙት ዝክር በማስመልከት ዶክተር አምባቸዉ ከበደ የሚባል የአሁኑ ዘመን ደብተራ የኮሎኔል አሌክሳንደር ቡላቶቭችን መጽሀፍ ወደ አማርኛ ተርጉሞታል። በጣም የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ትርጉም ነዉ የተደረገዉ። በአብዛኛዉ የመጽሃፉ ክፍል የያዘዉ የተርጓሚዉን የግል ድርሰት ነዉ። ስለ ኦሮሞ በቡላቶቭች መጽሀፍ ዉስጥ የሌለዉን እራሱ ዶክተር የተባለዉ ጠቅጥቆበታል። ለምሳሌ ቡላቶቭች ስለ ኦሮሞ በምስራቅ ኣፍሪካ በፈረሰኛ ጦር ሃበሾች ላይ የበላይነት እንዳለዉ ሲገልጽ፥ ደብተራዉ/ዶክተር አምባቸዉ ግን ኦሮሞን ስለፈረስ ያስተማረዉ ሃበሻ ነዉ ብሎ ጽፎታል።

እንድሁም የመሬት ስም እና የሰዎችን ስም አማርኛ ወይም ግዕዝ እንድመስሉ ኣድርጎታል። ለምሳሌ "Gura" ሆሎታ ኣካባቢ ያለዉ የቦታ ስም፣ በመደጋገም "ጉራዓ" ብሎ ጽፎታል። ይህ ጉራዓ የሚባል ስም በኤርትራ ዉስጥ አለ። ይህ ስም ደግሞ የሚያያዘዉ ከጉራጌ ብሔረሰብ ጋር ነዉ። ስለዚህ ዶክተሩ ይህንን ያደረገዉ የሚቀጥለዉ የሃበሻ ትዉልድ "ሸዋ" በሙሉ የጉራጌ ነዉ እንዲባልለት ነው። ልክ ቄስ ባሕሬ "ጋሞ" ብሎ ሲጽፍ፥ የኣሁኑ ደብተራዎች እንደነ ጌታቸዉ ሃይሌ ያሉ ደግሞ "ጋሙ ጎፋ" ብለዉ ኣረፉ። 

የሰዎቹ ስም ዉስጥ ደግሞ ቁሴ (ሀብተጊዮርጊስ) የአባት ስም ዲነግዴ የነበረዉን ቢነግዴ ብሎ በመጽፍ ተገላገለ። ዲነግዴ ማለት በእነሱ ሀብታሙ ማለት ነው። 

ሌላዉ ደግሞ ስለተፈጸመዉ የህዝብ ጭፍጨፋ፥ ስለ የሰዎች አጥንት በአዋሽ ሸለቆ ዉስጥ ተበትኖ መኖሩ በቡላቶቭች ሲገለጽ በአምባቸዉ ምንም የተጠቀሰ የለም። ከእንጦጦ እስከ ባሮ ያየዉን የተፈጥሮና፥ የኦሮሞ ሴቶች ቁንጅና በቡላቶቭች ሲገለጽ የነበረዉ፥ በዶክተሩ ምንም አልተባለም። ሁሉ ነገር ሙገሳና ፉከራዉ ስለሃበሻ ብቻ ነዉ። 

ሌላ እዚህ ላይ መጥቀስ የምፈልገዉ ነገር፥ በክፍል ሁለት ጽሁፌ ላይ ከአስተያየት ሰጪዎች ዉስጥ ጥያቄዎች ቀርበዉ ነበር። ይህም ባልቻ ሳፎ (ኣባንፍሶ) ማን ሰለበዉ? የሚል አንዱ ነዉ። 

በሚኒልክ ወረራ ግዜ ባልቻ ሳፎና ቁሴ ዲነግዴ በእዲሜ ከ15 በታች ነበሩ። በዚህ እድሜያቸዉ በጦርነት ዉስጥ ተሳተፉ። በወቅቱ የኦሮሞ ጦር፥ በጦር መሳርያ ተበልጦ ስለነበር የማታ-ማታ ባልቻና ቁሴ ለምርኮ ተዳረጉ። ባልቻ የተማረከዉ በበቾ ግንባር ቆራ በሚባል ቦታ ሲሆን፥ ማራኪዉ ደግሞ የኣማራ ጎሳ የጎበና ዳጬ ወታደር ነዉ። ይህም ወታደር ለግላጋዉን ወጣት ባልቻን የግሉ ምርኮ በማድረግ ወደ ቤቱ ወስዶ ሰለበዉ። ምክንያቱ ሃበሻ ጀግና ሰዉ ዘሩ እንዲበዛ ስለማይፈለጉ፥ ማኮላሸትና መስለብ ባሕላቸዉ ስለነበር ነዉ። 

ቁሴ ዲነግዴ (ሀብተጊዮርጊስ) የተማረከዉ በመጫ (Dandii Bishaanii) ዳንዲ ቢሻኒ በሚባል ቦታ ሲሆን፥ ማራኪዉ ደግሞ የኦሮሞ ጎሳ ከሆነዉ የጎባና ዳጬ ወታደር ነዉ። በመሆኑም እሱም እንደ ግል ምርኮ ወስዶ እቤቱ ኣስቀመጠ። በኋላ ላይ ቁሴ ብልጥና አስተዋይ መሆኑን በመገንዘብ ወስዶ ለሚኒልክ በተመንግስት አስረከበ። በኦሮሞ በመማረኩ ከስልብነት ኣመለጠ። 

ሌላዉ ስለስም መቀየር ወይም የአባት ስም ማስቀረትና የሰዉን ማንነት ለመደምሰስ የሃበሾች ቀዳሚ ተግባር ነዉ። ለምሳሌ የሊሴ ገበረማርያም የአባት ስም አይጠቀስም። ነገር ግን ደጃዝማች ገበረማርያም ጋሪ የሶዶ ኦሮሞ ነዉ። የሊሴ ገበረማርያም ትምህርት ቤት ዳይሬክተርም የገበረማርያምን የአባቱን ስም እንደማያዉቁ በኢትዮጲያ ቲቪ እና ሬዲዮ ገለጸዉ ነበር። 

ሌላዉ መገለጽ ያለበት ነገር ዛሬ ስለኣድዋ የሚወራዉ ሚኒልክ ብቻ ኣስደናቂ ኣመራር በመስጠት ነዉ በማለት የሚመጻደቁ ሃበሾች ታሪክን ማዛባት ኣመላቸዉ ስለሆነ ነዉ። የጦሩ መሪዎች ይብዛም ይነስም ወይም በአብዛኛዉ ኦሮሞ ናቸዉ። ከጣይቱ ቡጡሌ ወሌ (ወሎ ኦሮሞ)፥ ራስ መኮንን ወለደሚካኤል ጉዲሳ (አቢቹ) ገበዮ ፈሪሳ እና ባልቻ ሳፎ ሌሎችም። 
እኔም አንድ ጥያቄ ለሃበሾች ላቅርብላቸዉ፤
የማይጮ ጦርነት (የጣልያን ወረራ ጊዜ) የኢትዮጲያ የጦር መሪ የነበረዉ የራስ ሙሉጌታ የአባትና አያቱ ስም ማን ይባል ነበር?

መቼም በዚያን ጊዜ የኣማራዉ የምላስ ጀግና፣ ግማሹ ከኃይለስላሴ ጋር ወደ ዉጪ ሲፈረጥጡ፤ ግማሹ ባንዳ በመሆን ፋኖዎቹን የኦሮሞ ጀግኖችን ሲያስቸግሩ ነበር። ራስ አበበ ራጋ በቻራ፥ ሃይለማርያም ማሞ (ሻኖ)፥ በላይ ዘለቀ፥ የወሎ ቦረና ኦሮሞና ሌሎቹ ሲፋለሙ ራስ መንገሻ ስዩም እና ራስ ኃይሉ ከጎጃም ለኢጣሊያ ባንዳ በመሆን ሲያገለግሉ፥ የጀግኖቹን ኣካባቢ ቤት ንብረት ሲያቃጥሉ ቆይተዉ፤ ኃይለስላሴ በኢንጊልዝ ድጋፍ በሱዳን በኩል ሲመጣ ተሸቀዳድሞ ሄዶ እግሩ ላይ የወደቀ ራስ ኃይሉ ነበር። የዉስጥ ኣርበኛ ነበርኩ በማለት ነበር ተጨማሪ ስልጣን ከኃይለስላሴ (ተፈሪ) የተቀበለ። ነገር ግን የጠላት ቀሳፊ የነበሩና እና በላይ ዘለቀ ተይዘዉ በኣደባባይ ተሰቀሉ። ሌሎች ኣርበኛች ግዞትና እስር እጣ ፈንታቸዉ ሆነ።

ይቀጥላል

1 comment:

  1. ለምን አስተያየት መቀበል ትፈራላቹ??

    ReplyDelete