February 17, 2014 | በጨመዳ ሁንዴ*
ታሪክ በጥሩም በመጥፎም ጎኑ ይነሳል። ሁለቱም የሚነሱበት ዋና ምክንያት በትናትነዉ ዘመን ወይም ታሪክ ለመኖር ሳይሆን በጎ ድርግቶችን አዘምነን መጥፎ ፍፃሜዎችን ዳግመኛ እንደይከሰቱ (እንደይመለሱ) አዲሱ ትዉልድ እንድማርበት ነዉ። በአጠቃላይ አነጋገር ታሪክ ሲባል በተላያዩ መልኩ ትርጉም ሊሰጠዉ ይችላል። ታሪክ በድርግት ተፈፅሞ ወይም በአፋ ታሪክ ደረጃ ሊኖር ይችላል። ታሪክ እዉነተኛ የህዝቦችና የሀገርቱን ሁኔታ የሚገልፅ ሊሆን ይችላል። የዚህ ተቃረኒ ደግሞ የፈጠራና የመስመሰያ ታሪክ ሊሆን ይችላል።
ከዚህ አንፃር የአቢሲንያን (ኢትዮጵያን) ታሪክ ሲንመለከት የተለያዩ ሰዎች በተለያዩ መልኩ ሊመለከቱ ወይም ለያቀርቡ ይችላሉ። እስከሁን ድረስ የአቢሲንያን ታሪክ ሲንመለከት በወሰኝ መልኩ ሃቀኛ የህዝቦች ታሪክና ፍጻሜዎች ከመግለፅ ይልቅ፣ እዉነተኛ ታሪክን በማጠመም የፈጠራና ሃቅን ለመሸፈን የሚሞክሩ የቅብብሎሽ ታሪክ ነዉ። የፈጠራን ታሪክ የማይቀበሉት አዲሱ ትዉልድ ለረዥም አመታት የሚነገራዉን ድርቶ ታሪክ ከሥር መሰረቱ እንድለወጥ ወይም በሃቀኛ ታሪክ እንድተካ በአፅኖት ይፈልጋሉ። ይህ እዉነተኛ የህዝቦች ጥያቄ፣ ታሪክን በማጠመም መንገድ ለሳቱና ለሳቱ ቡድኖችና ግለሰቦች ላይዋጥ ይችላል። ለእነሱ መራራ ቢሆንም መቀበል ግድ ይላቸዋል።
አንድ ነገር ግን መዝላል የማይቻለዉ፣ በድርጊት የተፈፀመና የቅርብ ትዉልድ ዉጤት የሆነዉን ግን ማሰነስ፣ መከለስ፣ መስመሰል፣ ማጨበርበር፣ መከድና መወሻት ከቶ አይቻልም። ይህ ማድረግ መሞከር ዉጤቱ አደገኛ ይሆናል።
ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያን (አቢሲኒያን) ታሪክ የሩቁን ትተን የቅርብ ትዉልዶችን ሲነይ ሃቀኛ የህዝብ እና ፍፃሜዎች በጥሩም ሆነ በመጥፎ መልኩ የተከሰቱትን ለአዲሱ ትዉልድ ከማስተመርና ከማሰወቅ ይልቅ፣ መሸፋፈንን፣ ማጨበርበርን፣ መካድን፣ መስመሰልን፣ ታሪክ መቀመትን፣ እና የህዝብን ታሪክ በግለሰቦች ፋይዳ መለወጥን አስከትለዋል።
እዉነተኛ ታሪክ ሚዛን በሰተ መልኩ ለአመታት የኢትዮጵያ ገዥዎችና ደብተራዎች በማስተመራቸዉ ዛሬ ሃቁን መደበቅ ወደማይቻልበት ደረጃ ደርሰዋል። ምንጊዜም የፈጠራ ታሪክ እዉነተኛ የህዝቦች ታሪክን ማሸነፍ አይቻለዉም። ለጊዜ ግን መስመሰል ይቻል ይሆናል።
በኢትዮጵያ ዉስጥ የህዝቦችን ታሪክ በመከድ የወንጀለኛ ግለሰቦችንና ደብተራዎችን ታሪክ ጎልተዉ እንዲታይና ህዝቡ ራሱን እንዲራሳ በመደረጉ ጠባሰ ታሪክ ጥለዋል። ይህ ጉዳይ ለሌላ ጊዜ እንደሚመለስበት ለቀጠሮ ትቼ ወደ ርእሴ ሊመለስና “የወጋ ቢረሳም የተወጋ አይረሳም” እንደሚበላዉ የትላንቱ አልበቃም ብሎ አሁንም ቁስላችን የሚነካኩን ቡድኖችና የጥቁር ታሪክ ናፋቅ ነፍጠኞችን አንድ በሉ ለማለት ነዉ።
የኦሮሞ ህዝብ በታሪኩ ዉስጥ የማንንም ህዝቦች ታሪክ በማጠመም ወይም በማንቓሸሽ የሚገለፅበት አጋጣሚ የለም። ከዚህ በተቃራኒ የኦሮሞ ህዝብ ባሕሉና ታሪክ የሚነግረን፣ እንደግለሰብም ሆነ እንደቡድን የተቸገራዉን መርዳት፣ መንከበከብ፣ አብሮ መኖርና ከለላ መስጠትን የጎለበተ ኩሩ ህዝብ ነዉ። ይህ የሆነበት ምክንያት አለዉ። ከታሪክ እንደሚንረዳዉ የኦሮሞ ህዝብ የራሱ የነነር ዘይቤና የራሱን ስልጣኔ ከራሱና በራሱ ያመነጨ እንደመሆኑ መጠን የራስ መተማመን ስለሚሰመዉ የማንንም ታሪክ የመቀማት ወይም የመበደር ታሪክ የለዉም። ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑት ብዙና ብዙ ነገሮችን መጥቀስ ይቻላል። ከነዚህ ዉስጥ ሦስቱን መጥቀስ በቂ ነዉ።
አንደኛ የኦሮሞ ህዝብ ራሱን የሚያስተዳድርበት በጣም ዘመናዊና ዴሞክራሲያዉ የሆነ የገዳ ሥርዓት አለዉ። ይህ ገዳ ሥርዓት ከየትም የተቀዳና የተዋሰ ሳይሆን የጥንቱና የጥዋቱ የኦሮሞ የሥልጣኔ ዉጤት ነዉ። በኦሮሞ ታሪክ ዉስጥ ለሥልጣን ሲባል ልጅ አባቱን፥ አባት ልጁን አይገድለዉም። በኦሮሞ ባሕል ይህ ድርግት ኣስነዋር (haraamuu) ነዉ። ሥልጣን የተገደበና ወደሚቀጥለዉ አካል የሚተላለፍበት ግልፅ አሰራርና መመሪያ አለዉ።
ሁለተኛ የኦሮሞ ህዝብ የሥልጣኔ ዉጤት የሆነዉና የራስ መተማመን እንድኖራዉ ምክንያት የሆነዉ የራሱ ኃይማኖትና ሃቀኛ የጥቁሮችን ማንነት የሚገልፅ አለዉ። የኦሮሞና የኩሽ ዋቄፋና(waaqeffannaa) ኃይማኖት ከየትም አልተቀዳም። ከፈረንጁ ወይም ከአራቡም የተደበለቀ ወይም የተሰረቀና የተለጠፈበት ሳይሆን የጥቁር ህዝቦች የእምነት መሰረት ነዉ።
ሦስተኛ የኦሮሞ ህዝብ የዘር ግንዱና የታሪክ መሰረቱ ጥቁር አፍሪካና አፍሪካዊነትን መሰረት ያደረገ ነዉ። የኦሮሞ የዘር አመጣጥ ታሪክ በምንም መልኩ የፈጠራ ታሪክ ላይ አልተመሰረተም። በጥቁርነቱ የሚኮራ ህዝብ ነዉ። ስለዚህ እንደህዝብ የዘር ግንዳችን ላይ የማንነት ቀዉስ (identity crisis)የለንም።
ይህ በመሆኑም የኦሮሞ ህዝብ የራሱንም ሆነ የሌሎች ህዝቦች ታሪክ አያጣምም ወይም አይሰርቃዉም። የራስ መተማመኑ መሰረት የጥንቱና የጥዋቱ የጥቁሮች ሥልጣኔ ውጤት ነዉ።
ይህ ታሪክ ግን የአቢሲኒያ ደብተራዎችንና ገዥዎች በማጠመም በመደበቅ ወይም በመስረቅ እዉነተኛዉን የህዝቦችን ታሪክ ፍጻሜዎች ከመቅረብ ይልቅ የሌሎችን ህዝቦች ታሪክ በመካድና የራሳቸዉን የፈጠራ ታሪክ እንድቀበሉ መስገደድን እንደ ሥራ ወስዶታል። የኢትዮጵያ ገዥዎችና ደብተራዎች ከጥንት እስከ ዛሬ ያሉት እዉነተኛ የራሳቸዉን ታሪክና የህዝቦችን ታሪክ ደፍሮ መቀበልና ከስዕታተቸዉ ለመመር ዝግጁ አይደሉም። ይህ የሚሆንበት ዋነኛ ምክንያት ራሳቸዉን ወደ ሥልጣን የማጡበት ታሪክና የራሳቸዉን ታሪክ የሚገለፅበት ሁኔታ በሀሳትና በፈጠራ ላይ በመመስረቱ ነዉ።
ሃቅን ከመቀበል ይልቅ የራሳቸዉ ማንነት ክደዉ የሌሎችን ህዝቦች ማንነት ይክዳሉ። አንዳንዱም የፈጠራ ታሪካቸዉን በግድ ለሌሎች ብሔሮች እንድቀበሉ ይዳዳቸዋል። ከትናትና የታሪክ ስዕታተቸዉ ከመመር ይልቅ አሁንም በስዕታት ላይ ስዕታት ለመጨመር ሕልም ያልማሉ። የልተገነዘቡት ነገር ቢኖር አዲሱ ትዉልድ በፈጠራ ታሪክ የሚኖር አለመሆኑን አለመገንዘባቸዉ የሳዝናል።
የኦሮሞ ህዝብ ከሰሜን በመጡት ገዥዎች እስከ ዛሬ ድረስ እዉነተኛ ታሪኩን እንዳያዉቅ ተባብረዉ ይሰራሉ። ይህ ግን ከንቱ ጥረት መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል። ዛሬ ያለ ምንም አፍረት አረመኔ ሚኒሊክ፥ ቴዎድሮስ፥ ዮሐንስ….. ወዘተ እንደ ጀግናና ሀገር ገንቢ ሊነግሩን ይሞክራሉ። እነዚህ ወንጀለኛ ግለሰቦች በኦሮሞና በሌሎች ብሔር ብሄራሰቦች ዘንድ ጥቁር ታሪክ ያለባቸዉ ናቸዉ። ሚኒልክ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የፈፀማቸዉ ታሪክ አይረሰዉም።
በኦሮሞ ባሕልና ታሪክ ሴቶችና ሕፃናት በምንም መልኩ በጦርነት ዉስጥም ሆነ ከጦርነት ዉጭ አይገደሉም። ወንጀለኛዉን ሚኒልክ በሚናፍቁና ድርግቱን በጀግንነት የሚነግሩን ግን በሰዉ ፍጡር ላይ አስነዋር ድርግት የፈጸመ ግለሰብ ነዉ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኦሮሞ ሕጻናት፥ ነፍሰ ጡሮችን፥ ሽማግሌዎችን እና ሴቶችን ጡት፥ እጅ፥ እግር፥ አንገት የቆረጠ ፋሽስት ነዉ። ሚኒሊክ የኦሮሞን እናቶች ከሚጠባ ልጅ አላቆ ጡት የቆረጠ፥ ነፍሰ ጡር ሴት ከሆድዋ ሽል በሳንጃ የስወጣ በጅምላ የሰዉ ፍጡር የፈጀ ፈሪ ነዉ። የሚኒሊክ ጀግንነት የሚነግሩላት ሳይሆን የሚያፍሩበት ነዉ። እዉነተኛ ጀግና ሴት ልጅን ጡት አይቆርጥም። ስለዚህ ሚኒልክ የታሪክ ተወቃሽ እንጅ በምንም መልኩ ተወደሽ የሆነበት ትንሽ ነገር የለዉም።
ዛሬ አንዳንድ የአበሻ የፖላቲካ ድርጅቶችና ግለሰቦች እምዬ ሚኒልካቸዉን እንደ ጀግና ሊነግሩን የሚዳዱት ሊያፍሩበት ይገባቸዋል። የሚኒልክ ዘሮችና አቀንቃኞች የኦሮሞን ህዝብ በእፋ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸዉ። ይህን የማያደርጉ ከሆነ ከነሕልማቸዉ የሚኒሊክን መቃብር ይቀላቀላሉ።
ብዙ የሚዘከር የሚወደስ የሚዘፈንለት እዉነተኛ ጀግኖችና የህዝብ ታሪክ አለ። ለአረመኔና ለፋሽስት ሚኒልክ የጨፈርለት ሳይሆን የሚተፈሪበት ነዉ። የሚኒልክ ራዕ በ21ኛ ክ/ዘመን በምንም መልኩ በድርግትም ሆነ በፍላጎት ደረጃ የሚያስተነግድ ህዝብና ትዉልድ የለም።ከዚህ ይልቅ ሚኒልክ ለፈጸማቸዉ ፋሽስታዊና የፈሪ ድርግቱ የዘር ግንዳችን የሚሉት ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባቸዋል።
ዛሬም የሚኒልክ ሕልመኖች በብሔር መደራጀትና የብሔር ስም መጥራት እንደወንጀል የሚቆጥሩ በፖላቲካ ድርጅት መልኩ ተደጅተዉ እየሰሩ ነዉ። ኦሮሞን እንደ ኦሮሞነቱ መጥራትና ማክበር አዉንም የከበዳቸዉ የፖላቲካ ድርጅቶች በምንም መልኩ የሚኒልክ ራዕ በኦሮሞና በኦሮሚያ ምድር ላይ ቦታ እንደሌላቸዉ ሊያዉቁ ይገባል።
ይልቁንም የፈጠራ ታሪካቸዉንና ከማንነት ቀዉሳቸዉ ወጥተዉ ራሳቸዉ መሆን አለባቸዉ። የሰለሞን ዘር ነን ባዮች ራሳቸዉን ዝቅ አድርገዉ ከመገመት ይልቅ የጥቁር ዘር መሆናቸዉን ማመንና እዉነተኛ ታሪክን “ሀ” ብሎ መመር ይገባቸዋል። በሌላ በኩል አሁንም ሊረዱት የሚገባቸዉ በ21ኛ ክ/ዘመን በደብተራ የፈጠራ ታሪክ የሚመራ የሌለና የራሱ ታሪክ ጠንቅቆ የወቀ ትዉልድ ያለ መሆኑን ማወቅ አለባቸዉ። የሚኒልክን እርኩስ መንፈስ ይዞ መጮህና መጨፈር ይቻል ይሆናል። በምንም መልኩ በኦሮሞና በኦሮሚያ ምድር የሚኒልክ እርኩስ መንፈስ እንደ ከዚህ ቀደሙ መስፋፈት ከቶም አይቻልም። የሚኒልክ የዘር በጅምላ መፍጀት ምዕራፍ ለአንዴና ለሁሌም ተዘግትዋል። የኦሮሞ ህዝብ ትግል በድል የሚጠናቀቃዉም የሞተዉን የሚኒልክ አፅሚ በመዉቀስ ብቻ ሳይሆን የሚኒልክ እርኩስ መንፈስ ሕልመኞችንም ወደ መቀብር በመዉድ ይደመደመል።
* ጨመዳ ሁንዴ (Camadaa Hundee): camadaa@gmail.com
No comments:
Post a Comment