ይህ ትዉልድ የባርነትን ሠንሠለት ሰባብሮ ፍርሃትን ገድሎ ነጻነቱን ፍለጋ እስከ ወዲያኛዉ አድማስ ጥግ እንኳ ቢሆን ለመጓዝ ወስኖ የወጣ ጀግና ትዉልድ ነዉና “አልገዛም!” ካላ ቃሉ ጽኑ ነዉ!
ነጻነትን ያረገዛ ትውልድ ግፍና ጭፍጨፋ አላቆመዉም። የደቡብ አፍርካዉ የስዌቶ ጭፍጨፋ (the Soweto Massacre 1976 ) ፣ በኬንያ የታየዉ የሆላ ጭፍጨፋ “Hola massacre 1959” ወይም በሃሬሮና ነማ ሕዝቦች ላይ የተፈጸመዉ የነሚቢያዉ ጅኖሳይድ “Herero and Nama Genocide 1904” አልያም የ‘Robben Island’” እስር የትዉልዱን የነጻነት ጥያቄ እንዳልገታ ፤ የነጻነትን ብርሃን እንዳላጫለማ ታሪክ ምንጊዜም ህያዉ መስካር ነዉ።
ዛሬም ቢሆን ከማዕከላዊ እስከ ቃሊቲ፣ ከቅሊንጦ እስከ ዝዋይ የእስር ቤቱ ቁጥር ቢባዛም ፣ የማሰቃያ ዓይነቶች ቢበራከቱም ፣ ግዲያና ሽብር ቢፋፋምም ይህ ትዉልድ “ነጻነቴን!” ብሎ ወቷልና ፈጽሞ የሚያቆም አይሆንም። ነጻነትን የተጠማ ትዉልድ ለእዉነት በእዉነት የሚታገል ኀያል ኃይል (Super Power) ያለዉ ባለራዕይ የነጻነት ሠራዊት እንጂ በመንደርተኞች ኣሉባልታ የሚሳናከል እርባናብስ ስብስብ አይዴለምና!
በተደጋጋሚ እንደተገለጸዉም ሆነ በታግባር እንደተረጋገጠ የትዉልዱ መሠረታዊ ዓላማ (basic Objective) የኦሮሞ ሕዝብን ብሔራዊ ነጻነትን ማረጋገጥ ነዉ። ለዚህ ዓላማ ስኬት ሕዝባችን ዘማናትን ያስቆጠረ ዉድ ዋጋ ስከፍልበት ቆይቶ አሁን ለባርነት የመጨረሻ ስንብት የሚደረግበት ያታርክ ፊጻሜ ላይ አድርሰዉታል። ይህንን የትግል ምዕራፍ በኃላፊነት የተረከበዉ ትዉልድም ኃላፊነቱን ጠንቅቆ የሚያዉቅ ብቻ ሳይሆን ኃላፊንቱ የሚጠይቀዉን ዋጋም (responsibility) ጭምር ለመወጣት ዝግጁ ስለመሆኑ በአደባባይ አስመስክሯል። ነጻነት በነጻ አይገኝምና ሞትና እስራት ሳይገድበዉ ርቆ ተጉዟል።
ያለነጻነት መኖር ያዉም ደግሞ በአናሳ ቡድን ነጻነትን መነጠቅ በእጅጉ የስቆጣል። ሕመሙም ጥልቅ ነዉ። ይህንን ታሪካዊ ጥላሸት ለመንጻት እስከ አሁን የተከፈለዉን ዉድ ዋጋ እያሰብን ከእንግዲህ ወዲያ ይህ ታርክ የህዝባችን መታወቂያ ሆኖ እንዳይቀጥል ታሪካዊ ግዴታችንን ለመወጣት እነሆ በየፍልሚያ መስኮች ሁሉ ተሰልፈናል። ነጻነቱን የጠየቀ ሕዝብ ተሻግሮ ይሄዳል። ማሸጋጋሪያ ኃይሉ ደግሞ በዘመኑ ላይ የተገኘ ትዉልድ ነዉ። ለኦሮሞ ሕዝብ ያ ትዉልድ ተነስቷል። “እምብኝ ነጻነቴ!” ብሎ ታጥቆ የወጣ ትዉልድ ተንበርካኪ አሽከሮች (Bakar Shaalee, Warqinaa Gabayyoo, Abbaa Duulaa Gammadaa, Alamaayyoo Taganuu, Abdulqaadir Huseen, Geetuu Wayyeessaa, Mohammad Tusaa, Isheetuu Dassee…) በሚያሰሙት ጭንቀት ወለድ ሠሞነኛ ጩሃት ይቅርና የቅኝ ገዢዎችን በታሊዮን ሠራዊት እንኳን ቢሆን በትኖ የሚያልፍ ፣ ሞትን የደፈረ ፣ በደሙ ጎርፍ ሕያዉ ታርካዊ ዝክርን ጽፎ የሚያልፍ በዘማናት ዉስጥ አንዴ ብቻ የሚገኝ ፍርሃት ዓልባ ብርቅዬ ትውልድ ነዉ።
በመሆኑም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፣ ከዉስጥም ይሁን ከዉጭ ዛሬ የኦሮሞን የነጻነት ትግል ለማደናቀፍ ለሚትሹ ኃይሎች በሙሉ መልስ አለን። መልሳችን ኃይልን በኃይል ለማስቆም የደፈረ ትዉልድ መነሳቱ ነዉ። ይህ ትዉልድ የባርነትን ሠንሠለት ሰባብሮ ፍርሃትን ገድሎ ነጻነቱን ፍለጋ እስከ ወዲያኛዉ አድማስ ጥግ እንኳ ቢሆን ለመጓዝ ወስኖ የወጣ ጀግና ትዉልድ ነዉና “አልገዛም!” ካላ ቃሉ ጽኑ ነዉ!
ይህ የትዉልዱ ግልጽ አቋም ነዉ።
ሕይዋታችን ለነጻነታችን!!
No comments:
Post a Comment