መጀመሪያውኑ ማስተር ፕላን የሚባል ነገር የለም ማስተር ጥፋት እንጂ ባልፈው ፅሑፌም ደጋግሜ ያሰፈርኩት ማስተር ጥፋት በማለት ሲሆን እዚህ ፅሁፍ ውስጥም የምጠቀመው ማስተር ጥፋት የሚለውን ይሆናል።የዚህ የማስተር ጥፋት ተቁዋሞ ከተጀመረ ረጅም ግዜ ቢሆነውም በአዲስ መልክ እና በተጠናከረ መልኩ ከጀመረ ግን January 12 ድፍን 2 ወሩ አለፈ።ነገሩ በድጋሜ የተቀሰቀሰበት ምክንያት ደሞ ቀደም ብሎ በጨፌ ኦሮሚያ ኢናጉሬሽን ቀን ወያኔ በእጅ አዙር ያለምንም ውይይት ማስተር ጥፋቱ እንዲጸድቅ አደረገች።ይህ በእንዲህ እንዳለ ለትምህርት ቤት ኩዎስ ሜዳ ይውላል የተባልን ቦታ ያለምንም እፍረት የወያኔ ካድሬዎች ተከፋፈሉት ምን እሱ ብቻ ጨለመውን የሚያክል ደን ለአድ ግለሰብ ወያኔ ሸጠችው ለነገሩ በህይወት ያለ ሰው አንድ ጫካ ቢገዛ ምን ይደንቃል የመለስ ፓርክ የመለስ ፓርክ እተባለ አገር ምድሩን የሞተ ወሮት የለ እንዴ ሊያውም በነፃ ። ታዲያ ይህንን ቁጭ ብሎ ማየት ያቃተው የጊንጪ ህዝብ በቃኝ, መበዝበዝ በቃኝ, በሙት መንፈስ መገዛት በቃኝ, እየተንገፈገፉ ከመኖርስ መሞት ይሻላል ሲል ሰላማዊ ተቁዋሞ ሊያሰማ አደባባይ ወጣ። ሰላም የማይገባው የወያኔ መንግስት ግን ትክክለኛ መልስ ነው ብሎ ያስቀመጠው ጥይት ነበር እናም ንጹሀን ኦሮሞች ሰላማዊ ጥያቄን ስለጠየቁ በአደባባይ ተገደሉ። የንጹሀን ኦሮሞዎች በአደባባይ መሞት የኦሮሞን ህዝብ ከትግሉ ወደሗላ አላስኬደውም ይልቁንም ልክ ቤንዚን እንደተርከፈከፈበት ጭድ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምእራብ ትግሉን በተጋጋለ ሁኔታ አቀጣጠለው።
ይህ የህዝብ ትግል ያስፈራት ወያኔ የኦሮሞ ህዝብን በየአጣሚው መግደሉን ቀጠለች የሟቾች ቁጥር በረከተ ውሻ በበላበት ይጮሀል እንዲሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዘዳንት አቶ ሙክታር ከድርም እነኛ የሰባት አመት ሕጻን ልጅ ላይ ሳይቀር ቦንብ የሚጥሉ አረመኔ ገዳዮችን በአደባባይ አመሰገኑ። የኦሮሞ ህዝብ ግን አረመኔዎችን መፍራት ሳይሆን ከስልጣን ማስወገድ ነው ሲል ትግሉን ቀጠለ ወያኔም ትግሉን ፈጽሞ መግታት አቃታት። የዚህን ሰፊ ህዝብ ትግል ከመፍራት የተነሳ አሸባሪ, ጠባብ ዘረኞች ,ወንበዴዎች ,አጋንንት ,ጠንቁዋይ ,ከጀርባው አሸባሪ አለ, እከሌ አለ እያሉ ስም ሰጡት ተራና የወረደ ስድብም ተሳደቡ ። ይህ ውንጀላ ግን ትግሉን ወደፊት ከማጠናከር ይልቅ ቅንጣት ታህል ወደሗላ አልመለሰውም እነደውም ሁለት ወር አልፎት ሶስተኛ ወሩን ማስቆጠር ጀመረ። ይሄኔ ነው ታድያ ሕወሓት በኦህዴድ በኩል ማስተር ጥፋቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ቆሟል ሲሉ የማደናገሪያ ሀሳቡን ያስታወቁት።ወጉ ለምን ይቅርብን ያሉት ሆዳም ኦህዴዶች ልክ አጽድቁ ሲባሉ እንዳጸደቁት ሁሉ ዛሬ ደሞ ባለማፈር ማስተር ጥፋቱን አቁመነዋል አሉ ለነገሩ ሆዳም ምን አእምሮ አለውና ያፍራል። ይህ ከላ የጠቀስኩት ማስተር ጥፋቱን ከጥንስሱ ጀምሮ በቁርጥኝነት ሲከራከሩ የነበሩትን የኦህዴድ አባላትን አይመለከትም እነሱም ይህን በዚ መልኩ እንድሚርዱኝ እርግጠኛ ነኝ ምክያቱም እኔ ኦህዴድ የምለው ለሆዳቸው ያደሩትን ብቻ ንው።
በኦሮሞ ህዝብ በኩል ማስተር ጥፋቱ ቆሙዋል የሚለውን ሀሳብ እንደ አንድ ድል ቢወስደዉም ይህ ግን የሮሞ ህዝብ የሚጠብቀቀው የመጨረሻ ውጤት አይደለም ። ድል ያልንበት ምክያት በወያኔ የእድሜ ዘመን ለመጀመሪያ ግዜ ሽንፈትን ያመነበት በመሆኑ ነው። ከዘህ ቀጥሎ በሚጠቀሱት የተለያዩ ምክኛቶች ደሞ የሚጠበቀው የመጨረሻ ውጤት አይሆንም።
በኦሮሞ ህዝብ በኩል ማስተር ጥፋቱ ቆሙዋል የሚለውን ሀሳብ እንደ አንድ ድል ቢወስደዉም ይህ ግን የሮሞ ህዝብ የሚጠብቀቀው የመጨረሻ ውጤት አይደለም ። ድል ያልንበት ምክያት በወያኔ የእድሜ ዘመን ለመጀመሪያ ግዜ ሽንፈትን ያመነበት በመሆኑ ነው። ከዘህ ቀጥሎ በሚጠቀሱት የተለያዩ ምክኛቶች ደሞ የሚጠበቀው የመጨረሻ ውጤት አይሆንም።
1 ኛ ቆሞል የሚለው የማደናገሪያ ሀሳብ ሙሉ ለሙሉ ተሰርዙዋል ወይም ቀርቱዋል በሚለው ሀሳብ መተካት አለበት ምክንያቱም የቆመን ነገር ያቆመው አካል በፈለገው ሰአት መልሶ ማንቀሳቀስ ስለሚችል ለምሳሌ ይህ ማስተር ጥፋት ወያኔ አምናበት ባይሆንም በ 2014 የሰማኒያዎችን ሕይወት ከቀጠፈ በሗላ ቆሞ ነበር ታዲያ ይኸው ተመልሶ በ 2015 ደግሞ ተነሳ ስለዚህ ይህ ማስተር ጥፋት ጨርሶ መሰረዝ ነው ያለበት።
2 ኛ ይህ ማስተር ጥፋት ከተጀመረበት 2014 ጀምሮ በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም አደባባይ ወጥተው የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 200 አልፋል፣ ወደግፍና ማሰቃያ ቦታ የታጎሩ ኦሮሞች ቁጥር በበርካታ ሺዎይች ይቆጠራል (እዚጋ እስር ቤት አላልኩም ልብ በሉ የግፍና የስቃይ ቦታ ነው ያልኩት ምክንያቱም እስርቤት የሚለው ቃል ጥፋት አጥፍተው ወይም ወንጀል ሰርተው ለመታረም የሚገቡትን እጂ ለንጹሀን ዜጎችን ስለማይመጥን ነው) አያሌዎች በአጋዚ ጥይትና ቦምብ ቆስለዋል አያሌዎች ደሞ ተሰደዋል ስለዚህ መንግስት በቅድሚያ የዚህ ሁሉ ጥፋትን ሀላፊነት ወስዶ ተገቢውን ካሳ መክፈል አለባት።
3 ኛ መንግስት የህዝቡጥያቄ ተገቢና ልክ መሆኑን ስላመነ ኦሮሚያን የወረረው የአጋዚና የፌደራል ወታደርያለምንም ቅድመ ሁኔታ ኦሮሚያን ለቆ ወደ መጣበት መመለስ አለበት።
4 ኛ የኦሮሞ ህዝብን ጠንቁዋይ አጋንንት ጠባብ ጽንፈኛ እያሉ ልክ እናስገባዋል ብለው የፎከሩ የመንግስት ባለስልጣኖች በአደባባይ ወተው የኦሮሞ ህዝብን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው።
5 ኛ በመጀመሪያውኑ የረቀቀው ማስተር ጥፋት ለጨፌ ኦሮሚያ የተላከው እንዲወያዩበት ሳይሆን እንደነ ሙክታር ከድር ያሉ ለሆዳቸው ያደሩ ከዳተኞች እንዲያፀድቁት ሕወሓቶች የላኩት ነበር። ነገር ግን ኦሕዴድን ሕወሓቶች ባስቀመጡበት አላገኙትም በርከት ያሉ ለኦሮሞና ለኦሮሞ ሕዝብ ብቻ የሚሰሩ ውድ የኦርሞ ልጆች ተቀላቅለውበታል ስለዚህ ይህ ማስተር ጥፋት ገና ከእቅዱ እክል ገጥሞት ወደ አደባባይ ወጥቶ ለዚህ በቅቷል። ለኦህዴድ ይህን የጥፋት እቅድ አውጥቶ የሰጠው አካል ነው መሰረዝ ያለበት እንጂ ኦህዴድማ በምን አቅሙ።
6 ኛ ባለፈው
ጽሁፌ እንደጠቀስኩት የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ አድጎ ይህ መንግስት ዲክታተርና ጨካኝ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ሕዝብን ለማጥፋት በየግዜው የጥፋት እቅዶችን አቅዶ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ እኛ እራሳችን ይበጀናል የምንለውን መሪ መምረጥ እንፈልጋለን በመሆኑም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መንግስት ስልጣኑን ይልቀቅ። ወያኔ ከዚህ በሗላ በምንም መመዘኛ የኦሮሞ ሕዝብን የማስተዳደር ብቃት በፍፁም አይኖረውም።
ጽሁፌ እንደጠቀስኩት የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ አድጎ ይህ መንግስት ዲክታተርና ጨካኝ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ሕዝብን ለማጥፋት በየግዜው የጥፋት እቅዶችን አቅዶ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ እኛ እራሳችን ይበጀናል የምንለውን መሪ መምረጥ እንፈልጋለን በመሆኑም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መንግስት ስልጣኑን ይልቀቅ። ወያኔ ከዚህ በሗላ በምንም መመዘኛ የኦሮሞ ሕዝብን የማስተዳደር ብቃት በፍፁም አይኖረውም።
በትንሹ እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት 6 ነጥቦች በተግባር እስካልዋሉ ድረስ ሕዝባዊ አመፁ ይጨምር ይሆናል እንጂ አይቀንስም። ትግሉ በመሀል ቀዝቀዝ ሊል ይችላል ይህ ማለት ግን እራሱ የትግሉ ስልት እንጂ በምንም አይነት የወያኔ ወታደሮች ተቆጣጥረውት አይደለም። በመጨረሻ ማሰብ, መስማት, ማየትና ማስተዋል ለተሳናቸው የሕወሓት ሰዎች የምሰጣቸው ትንሽ ምክር ብጤ ቢኖር ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ ከዚህ የባሰ አደጋና ቁርሾ ሳይመጣ በመውረድ ሳይመሽባችሁ ሰላም መፍጠር ያዋጣችሗል እላለሁ። በተለይ ደሞ ወጣት የሕወሓት አባላት አቶ አባይ ፀሐዬ የሚደነፋው የቀረኝ እድሜ አጭር ነው ብሎ ነው እናተ ግን ዛሬ ሰላምን መፍጠር ካልቻላቹ የአባት እዳ ለልጅ የሚለው በእናንተ ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን አትጠራጠሩ።የኦሮሞ ሕዝብ ድልን እንደሚቀዳጅ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የለንም።
ድል ለህዝባችን
አዴው (አድ አዳማ) ከኖርወይ
No comments:
Post a Comment