የኦሮሞ ህዝብ በይፋ ከታወጀበት ጦርነት ራሱን የመከላከል ህጋዊ መብት አለው! ትዕግስትም ልክ አለውና!

May 02, 2016 |በደጀኔ ጉተማ


የአሮሞ  ህዝብ ላለፉት  25 ዓመታት በሕወሓት በይፋ  በታወጀበት  የዘር  (ማጥፋት) ጦርነት  ውስጥ ቆይቷል; አሁንምን ይገኛል።  ይህ በቀጥታ በኦሮሞ  ህዝብ ላይ  ነጣጠረው  ጦርነት  ሚዛኑን ያልጠበቀ  ስለመሆኑ  አጠያያቂ  አይደለም። ምክንያቱም ኦሮሞ  ባዶ  እጁን  ወራሪው ጠላት  ደግሞ እስከ አፍንጫው የታጠቀ በመሆኑ!  ያም ሆኖ ኦሮሞ  ራሱን ከጥፋት  ለመከላከል  የሕልውና  ትግሉን  ያቋረጠበት ጊዜ የለም።
የኦሮሞን ህዝብ  በዋና ጠላትነት   የፈረጀው ህወሐት  የስርአቱን ዕድሜ  ለማራዘም በኦሮሞ ህዝብ ላይ አጠቃላይ ጦርነት ማወጅ የግድ መሆኑን  ያመነው  ገና ከጅምሩ በትረሰልጣኑን እንደተቆናጠጠ ነበር።  እናም ይህን እምነቱን ላላፉት 25 ዓመታት  ተግባራዊ  ሲያደርግ  ቆይቷል፣ አሁንም  አጠናክሮ  ቀጥሎበታል።

እንደ አውሮፒያኖቹ ዘመን  አቆጣጠር  ከ2014 ዓም ጀምሮ በጀግኖቹ የኦሮሞ ወጣቶች  እየተመራ  ያለው ታላቅ  የፀረ  ጭቆና ሕዝባዊ  ንቅናቄ  የጭቃ ውስጥ እሾህ የሆነበት  ህወሓት  ይህን ህዝባዊ  መሠረትና አለማቀፍ  ድጋፍ ያገኘውን  አብዮታዊ ንቅናቄ  ለማኮላሸት  በጦር  ሠራዊቱና በፀጥታ  ኃይሎቹ በመታገዝ  በኦሮሞ  ህዝብ ላይ  ያወጀውን የዘር  ማጥፋት ዘመቻ ከምን ጊዜውም  በላይ አጠናክሮ  ቀጥሎበታል።
ወያኔ  በኦሮሞ  ህዝብ ላይ ያወጀው  ጦርነት  ዓላማው  አንድና አንድ ብቻ ነው ! የኦሮሞን  ህዝብ ከምድር ገፅ ማጥፋት አልያም  በወታደራዊ  ጡንቻ አስፈራርቶ  በባርነት  እስር ቤት ውስጥ ማቆየት!  መግደል፣ ከሀገር   ማሳደድ፣  ኦሮሞና ኦሮሚያን  በጠራራ ጸሐይ  መዘርፍ፣  ኦሮሞን በገዛ  ቄዬው ባይታወርና የበይ ተመልካች ማድረግ!
የወያኔ  መንግስት ከ10 አመት በፊት  የኦሮሚያን ዋና ከተማ  ከፍንፍኔ ወደ አዳማ  ማዛወርና በቅርቡ  ደግሞ  ማስተር ፕላን ከተባለው  የመሬት  ዘረፋ  ጋር  በተያያዙ  ሁኔታዎች የተነሱትን ሕዝባዊ  ተቃውሞ  ለማክሸፍ በተለይ የትኩረቱ  ኢላማ ያደረገው የነገ  አገር ተረካቢ  የሆኑ የኦሮሞ ወጣቶችን ነው።  ወያኔ  ምርጥና ታማኝ  ብሎ የሚመካበትን አጋዚ  የተባለውን  ነፍሰ ገዳይ  ጦር  ወደ ኦሮሚያ አዝምቶ በአጠቃላይ መላውን የኦሮሞ ዜጎች  በተለይ ደግሞ የነገ ኦሮሚያ ተረካቢ  ወጣቶችን  በጅምላ  በመግደል፣ በማሰርና በማሳደድ፣ በመረሸን ላይ ያተኮረው  ኦሮሞ  የተማረ  የሰው ኃይልና ጠንካራ መሪ እንዳይኖረው ነው።
ይህን የማይሳካ የቀን ህልምና ቅዠት  ለማሳካት በተለይ  በአሁኑ  ወቅት የኦሮሞ ወጣቶችንና የፖለቲካ  መሪዎችን አድኖ በማሰርና  በማሰቃየት  ላይ  ይገኛል። የኦሮሞ እስረኞችን አደንዛዥና  ገዳይ  መድኃኒቶችን እንደዲውጡ  በማስገደድ  ላይ ይገኛል።  የኦሮሞ ተማሪዎች  በሠላም እንዳይማሩ  እንቅፋት  ከመፍጠር  ጎን ለጎን ትምህርት  ቤቶች  በተለይ  ዩኒቨርስቲዎችን ሆን ብሎ ያቃጥላል።
ወጣቶች  ከሐገር ተሰደው  ባህር  ላይ እንዲያልቁና በአሸባሪዎች እንዲታረዱ እያደረገ  ነው።   የሀገርቷ የዳቦ ቅርጫት የነበረው  ኦሮሚያ  ሻጥር በአሻጥር ወደ ረሃብ  ቀጠናነት ለውጦ ሕዝባችንን  በረሃብ  እንዲረግፍ አድርጓል።
ከ25 ዓመት   በፊት የወያኔ  ወታደሮች  ተፈራርቀው በፈፀሙባት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል  ቆሯጧ የኦሮሞ  ውድ ልጅ (አይሻ) በምስራቅ  ኦሮሚያ  ህይወቷ ማለፉ ለኦሮሞዎች የእግር  ውስጥ እሳት ሆኖ ቆይቶ  እያለ ዛሬም እነሆ የኦሮሞ ሴቶች በጠራራ ጸሐይ  በወያኔ  ወታደሮች እየተደፈሩ ነው። በዚህም ምክንያት  ገሚሶቹ  ለሕልፈተ ሕይወት  ተዳርገዋል፣ ሌሎቹ  ለተላላፊ በሽታዎች( ኤዲስን ጨምሮ) ተጋልጠዋል።
በወያኔ  የፀጥታ  ሃይሎች  በየቀኑ  እየታደኑ የሚታሰሩ  የኦሮሞ  ዜጐች  ተደብድበው  አካለ ስንኩላን  መሆናቸው  ሳያንስ ወደ ሆስፒታሎች  ከተወሰዱ በኋላ  መሞታቸው  እንቆቅልሽ  ሆኗል።
በቅርቡ የአምቦ እስር  ቤት (ከርቸሌ)  ከተቃጠለ  በኋላ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ማምለጣቸው ያበገነው የወያኔ  መንግሥት  ወጣቱን  የኦሮሞ  ታጋይ  በአምቦ ከርቸሌ  አስሮ በድብደባ ገድሏል።  በአጠቃላይ  ወያኔ  ኦሮሞንና ኦሮሚያን  ለማጥፋት  ያልፈነቀለው ድንጋይ  የላም፣ ወደፊትም  አይኖርም።
ይህ የለየለት  አሸባሪ መንግሥት  የኦሮሞን  ህዝብ ህጋዊ የመብት ጥያቄ  አፍኖና ጨፍልቆ  የትግሉን የትኩረት  አቅጣጫ ለመቀየር  ሰይታክት መስራቱን  ቀጥሎበታል ።
በአንፃሩ  ግን  ከ6 አመት  ህፃናት እስከ  80 አመት  አዛውንቶችን  በአደባባይ  አጋዚ በተባለው ጦር  ጨፍጭፏል።  ልጇን ለማደን የሞከረች  እናት ከልጇ ጋር  የጥይት ሰለባ አድርጓል ።  ነፍሰ ጡር እናትን በጭካኔ   ገድሏል።  የኦሮሞ  አርሶአደሮችና አርብቶ  አደሮችን  ከአያት ቀድሞ አያታቸው መሬት አፈናቅሎ  ለልመና ዳርጓቸዋል ።
ላለፉት  5  ወራት የኦሮሞ  ወጣቶች  ፍጹም በሰለጠነ  ሁኔታ  ሰላማዊ  የመብት ትግል  እያካሄዱ  ቢሆንም  ከወያኔ  አጋዚ ግን  ምላሹ የጥይት ውርጅብኝ  ሆኖ ቀጥሏል።  የዚህ ዓይነቱ  ፋሽስታዊ የሽብር  ተግባር በምን መልኩ ተቀባይነት የለውም።
ኦሮሞ  ትዕግስትም ልክ አለው ብሎ  ወያኔን  በሚገባው ቋንቋ ለማነጋገር  ወስኖ  እየተንቀሳቀሰ ያለውም  ድርግቱ ከተራ ሽብርተኝነት ወደ ከፋ የዘር  ማጥራት  ወንጀል ከተሸጋግሮ ሕልውናውን  ስጋት  ላይ በመጣሉ ነው። እንግዲህ በመላው  ኦሮሚያ  እየተወሰዱ  ያሉት   ራስን የመከላከል እርምጃዎችም ይህንኑን  ያመላክታሉ።
በእርግጥም  ትዕግሥትም ልክ አለው። ኦሮሞ  በየቀኑ  በአጋዚ ጥይት የተገደሉበትን ዜጐች  መቅበርና ማንባት(ማልቀስ) አንገሽግሾታል።  የለቅሶና የስቃይ  ፅዋው ሞልቶ  ፈሷል። ልጆቹን  ድሮና አስተምሮ  ለወግ  ማዕረግ ማብቃት አልቻለም።  ኦሮሞዎችን በእስር ቤቶችና ከእስር  ቤቶች  ውጪ  በመድኃኒትና በድብደባ  መግደልና  አካለ ጎዶሎ  ማድረጉ  ከፍተኛ  ብሶት  ፈጥሯል።
በጥቅሉ  ደመኛው ጠላት  ሰላማዊውን  ጥያቄ  በሰላማዊ  መንገድ  ከመመለስ  ይልቅ  በኦሮሞ ላይ የዘር  ማጥፋት ዘመቻውን  ከምን ጊዜውም  በላይ  አጠናክሮ  ቀጥሏል። ሰላም ፈላጊ ለመምሰልም ካንገት  በላይ ያላለፈ ይቅርታ እየጠበቀ  በተግባር  ግን ንፁሃን ዜጎችን  ማሸነፉን ገፍቶበታል።  በቅጥፈትና በሽር በተሞሉ የሐሰት  ሽምግልናዎች የህዝቡን  አንድነት ሽርሽሮ የንቅናቄው  መሪዎች ያላቸውን  አድኖ  ማፈኑን ዕለታዊ  ተግባሩ  አድርጓል።

ስለሆነም  የዘር  ማጥፋት ዘመቻ  የተከፈተበትና  በይፋ  በታወጀበት  አጠቃላይ  ጦርነት  ውስጥ የሚገኘው  የኦሮሞ ህዝብ፣ ትዕግስትም ልክ አለው ብሎ፣  በተፈጥሮ ያለውን ህጋዊ  መብት ሁሉ  ተጠቅሞ  ራሱን ከጥፋት ለመከላካል  የተለያዩ  የትግል ስልቶችን (ሰላማዊና የትጥቅ ትግል)  አቀናጅቶ  ኃይልን በኃይል ፣ መሣሪያን በመሳሪያ፣ ጥይትን በጥይት ፣ ጦርነትን  በጦርነት  መመለስ  ይጠበቅበታል። ምክንያቱም የኦሮሞ ህዝብ የታወጀበትን ጦርነት  የመከላከል ህጋዊ መብት  አለውና!

1 comment:

  1. AnonymousMay 05, 2016

    Ummatnii Oromo waggaa bayyeedhaf sabootta gossa lammaan dabaredhaan darrarrama turuun issa nibeekama. Hata'uu malee ossoo namootnii dhalootan Oromoo ta'aan dinotta kanna gargaruu batanii Oromoon yero kam iyyuu hingarbomfamuu turee. Amma garuu yeroo yoom iyyuu challaatii ummatnii Oromoo tokoo ta'ee jirra. Garuu namootnii lakofsii ishee murassa tatee ammaas garaa isheetif jechaa Dinnaa jalla figuudhaan lolotootta Oromoo ummaatta Oromootiif lubuu issaanii wareeganii halkanii guyaa waraaqa jiran firra fakkattee nukeessa faccatee diinaaf nu saxilla jirtii.
    Jarii kun xiyeefanaa cimmatuu barbachissaa. Warootnii Oromoo osoo hintaiin nu kessaa jiratanii affaan kenyaa hassaan diinaa wajiin waligalanii osso lafa kenya irra jiratanii, horatanii jiranii diinaaf nusaxuluu barbaduun issanii diinna issa rassassan ummataa keenya akayaa jiruu callaatii illallamuu qabuu. Qabeenii issaan horataniis akka qabeenna dinnatii illallamu qaba. Hamma ille goftotiin kenyaa durrii nu midhuu hindhiisnee. Kanafuu nanoo keenya yeroo hunda iyuu illalluuf waan gonuus of egennandhaan hojechuun nimalla. Tokummaan Oromootta chimmee ittii fufuu malla. Tokumma keenyya argisiisufis alabba tokko jalatii akka waltiqabbamnetti itii fuffu qabnna. Hinjifanoon Kan Ummatta Orommotti. Jabbadhaa!!

    ReplyDelete