EPRDF’s Anti-Oromo Policy – የወያኔ ጸረ ኦሮሞ ሴራ ዳግመኛ ሲጋለጥ!

28 January 2013 | Gadaa.com

By Bekele* | በበቀለ*

በወያኔ ቡድን የሚመራው የኢትዮዽያ ገዢ መንግስት ገና ስልጣን በያዘ ማግስት ጀምሮ ጸረ የኦሮሞ ህዝብ ኣቋም ይዞ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲያካሄድ ቆይቷል ኣሁንም በማካሄድ ላይ ይገኛል። በወያኔ የሚመራው የኢህአዲግ መንግስት የኦሮሞን ብሄርተኞች ለማጥፋት ኣቅዶ የተነሳው ገና ስልጣን በያዘ ማግስት መሆኑን ቀጥሎ ከሚነበበው መረዳት ይቻላል።

Stated Government Policy

Oromo nationalism is perceived as the greatest threat to the ruling government party (the Ethiopian Peoples Revolutionary Democratic Front – EPRDF – an umbrella party, led and dominated by the Tigrean People’s Liberation Front – TPLF). According to the EPRDF party journal, Hizbaawi Adera [People’s Custodian], Tahsas 1989, Ethiopian Calendar [December 1996]:
“To defeat narrow nationalism … must be part of our struggle. In order to have a lasting solution to our problem … we have to break narrow nationalist tendencies in Oromia … we have to fight narrow nationalism to the bitter end … to smash it in a very decisive manner … fighting the higher intellectual and bourgeoisie classes in a very extensive and resolute manner … The standard bearers of narrow nationalism are the educated elite and the bourgeoisie. [W]e must be in a position to eradicate all narrow nationalists …” (quoted from Oromia Support Group’s report)
በዚሁ የጸረ ኦሮሞ ፖሊሲ መሰረት በሺዎች የሚቆጠሩትን ገድሏል፣ ህጻን፣ ሽማግሌ፣ ሴት ወንድ ሳይል በቤታቸው ውስጥ እንዳሉ በእሳት ኣቃጥሏል። በሺዎች የሚቆጠሩትን በጥይት ደብደቦ ገድሏል፣ በሺዎች የሚቆጠሩትን ከሃገራቸው እንዲሰደዱና በተለያዩ ሃገሮች ለከፍተኛ ሲቃይ እንዲዳረጉ ኣድርጓል።

በኣሁኑ ጊዜ ከሃያ ሺ በላይ የኦሮሞ ተወላጆች በዚሁ ኣስከፊ ስርኣት እስር ቤቶች ታጉረው በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ። የሃገሪቱ ህገመንግስት በሚፈቅደው መሰረት ተደራጅተው ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነትና ለፍትሕ የምታገሉ እንደ እነ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳና ሌሎች በርካቶች ያለ ምንም ወንጀል ለእስር ተዳርገው ይገኛሉ። እነ መስፍን ኣበበና ተስፋሁን ጨመዳ ኣስከፊውን ስርኣት ከሸሹበት ሃገር ከኬኒያ ተጠልፈው በወያኔ ጉዳይ ኣስፈጻሚ ፍርድ ቤት ተብዬው የሞትና የእድሜ ልክ እስር ተፈርዶባቸዋል። በግል ስራ ላይ ተሰማርተው ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር ይጥሩ የነበሩ እንደነ እሸቱ ኪትልና በቀለ ነገሪ ከየቤታቸው ተወስደው ያለ ምንም ጥፋት ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ በርካታ ኣመታት ተፈርዶባቸዋል። በሙያቸው ተቀጥረው በማገልገል ላይ የነበሩ እንደነ ከበደ ቦረና፣ ሃጅ ዋቤ የመሳሰሉት ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ ታስረዋል። ሌሎች ከትምህርት ቤታቸው ተይዘው እድሜኣቸውን በእስር እንዲጨርሱ እየተደረገ ያለው ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ እንጂ የሰሩት ወንጀል የለም። በተለይም በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተፈጸሙና እየተፈጸሙ ያሉ የማጥቃት ዘመቻዎች ከሁሉም ኣስከፊና ከዘር ማጥፋት ተለይቶ የማይታይ ድርጊት ነው። በማንኛውም ጨቋኝ መንግስትና በማንኛውም ሃገር ታይቶ የማይታወቅ በወያኔ መንግስት በ1993 በኣንድ ጊዜ ከኣምስት መቶ በላይ የዩኒቨርሲቲና ኮለጅ ተማሪዎች በኣንድ ላይ ተይዘው ወደ ኮልፌ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተወስደው ኢሰብኣዊ በሆነ ሁኔታ ተደብድበው ግማሹ ዳግመኛ ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዳይመለሱ ሲደረጉ ሌሎች ወደ እስር ቤት ተወርውረው የወጣትነት ጊዜያቸውን በእስር እንዲያሳልፉ ተደርገዋል። ይህ ኣድራጎት የኢህኣዲግ መንግስት ምን ያህል ኦሮሞን ያለ ተተኪ የተማረ ትውልድ ለማስቀረት እንዳቀደ ያመለክታል። ከላይ በተጠቀሰው ፖሊሲው ላይም በተለይ የተማረውን ክፍል ለማጥፋት ያቀደ በመሆኑም በተግባር ላይ እያዋለ ነው።

ከላይ ከተዘረዘሩት የጸረ ኦሮሞ ድርጊቶች በተጨማሪ በተፈጥሮ የላቀ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች በየጊዜው በየትምህርት ተቋማቱ በሰገሰጋቸው ቅጥረኛ ተማሪ ተብዬ ካድሬዎቹ የትንኮሳ ተግባራት እያስፈጸመ ተበዳዮቹን የኦሮሞ ተማሪዎችን ጥፋተኛ በማድረግ በመደብደብና በማሰር ከትምህርታቸው እንዲወገዱ በማድረግ የለየለት ወንጀል ሰርቷል ኣሁንም ኣጠናክሮ እየሰራ ይገኛል። ይህ ሰሞኑን በፊንፊኔ (ኣዲስ ኣበባ) ኣራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ የተፈጸመውም በትግራይ ነጻ ኣውጭ ግንባር የሚመራው የኢህአዲግ መንግስት ቀጣይ የኦሮሞን ትውልድ ለማዳከም ከላይ የተዘረጋ ፖሊሲ ቀጣይነት መሆኑን ለመረዳት ኣያዳግትም።

የወያኔን ጸረ የኦሮሞ ወጣቶች መሆን ሰሞኑን ኣቶ ተክለሚካኤል ኣበበ እና ዶክተር መረራ ጉዲና ከኣሜሪካ ረድዮ የኣማርኛ ፕሮግራም ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ በቂ ምስክር ከመሆኑም በላይ ከላይ የተጠቀሰውን ፖሊሲ ዳግም ያጋለጠ ነው። በተለይ ኣቶ ተክለሚካኤል በወቅቱ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት የነበሩ እንደገለጹት “በ1993 ከዩኒቨርሲቲ ተደብድበው በፖሊስ መኪና ተጭነው የተወሰዱት የኦሮሞ ተማሪዎች ያለ ምንም ጥፋት መታወቂያቸው ታይቶ ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ መሆኑን በዐይናቸዉ ማየታቸዉን ኣረጋግጠዋል። የትግራይ ተማሪዎች ከሆኑ ኣለመነካታቸው ከጉዳዩ በስተጀርባ ኣንድ ድጋፍ ሰጭ ተቋማዊ ሃይል መኖሩን ያመለክታል” ሲሉም ኣጋልጠዋል።

ዶክተር መረራም በተመሳሳይ መልኩ “መንግስት ኣንዱን ተማሪ ጠላት ኣድርጎ ሌላውን ወዳጅ የማድረግ ሁኔታዎች እንዳሉ ገልጸው ሰሞኑን በኣራት ኪሎ ግቢ በተከሰተው ግጭት ወቅትም የኦሮሞ ተማሪዎች ጉዳዩን ለሚመለከታቸው ለማመልከት በሄዱበት በፖሊስ ተደብድበው ወደ እስር ቤት መወሰዳቸው ገዥዉ ፓርቲ ኣንዱን ወዳጅ ሌላውን ጠላት ኣድርጎ የከፈፍልህ ግዛ ፖሊሲውን በተግባር እያሳየ መሆኑን ያመለክታል” ብለዋል። የወያኔ መሪዎች የኦሮሞን ህዝብ የመብት ትግል ያዳክምልኛ በሚል ኣጉል ተስፋ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ለወስዱኣቸው የማጥቃት እርምጃዎች የሚጠየቁበት ጊዜ ይመጣል። የዚህ የዘር ማጥፋት ራዕይ መሪ ዋጋቸውን ከሃያሉ ያገኙ ሲሆን ቀሪዎቹም እዚሁ በምድር ላይ ዋጋቸውን የሚያገኙበት ጊዜ እሩቅ ኣይሆንም።

በመጨረሻም የኣምባገነኑን የወያኔ መንግስት የኦሮሞን ተማሪዎች የማጥቃት ፖሊሲ ኣስፈጻሚ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ከድርጊታቸው ተቆጥበው እየሰሩ ያሉትን ቆም ብለው ማሰብ ኣለባቸው። የኢህአዲግ መንግስት መውደቁ ኣይቀረ ነው። እናንተ ግን ከኦሮሞም ሆነ ከሌሎች የኢትዮዽያ ህዝቦች ጋር ትቀራላችሁ። ምናልባት ጥቂት ተማሪዎች ከኢህአዲግ ፍርፋሪ እያገኙ ነገ የሚጠየቁበትን ወንጀል ይሰራሉ። ይህ ጊዜያዊ ነው እንጂ በምንም መልኩ ዘላቂ ልሆን ኣይችልም። ዘላቂ የሚሆነው የህዝቦች ወዳጅነት ነው። ስለዚህ ከዚህ ከማይበጃችው የትንኮሳ ስራችው ታቅባችሁ እስካሁን ለፈጸማችው የጥፋት ድርጊታችሁም ይቅርታ መጠየቅ ይኖርባችዋል። የወያኔ መንግስት የኦሮሞን ህዝብ በተለይም የተማረውን ክፍል የማጥፋት ፖሊሲ ዳግሜኛ ስለተጋለጠ የትም ማምለጥ ኣይቻልም። ከዚሁ ጋር ኣያይዤ ከኣሜሪካ ራዲዮ ጋር በተደረገዉ ቃለምልልስ ወቅት ዶክተር ሃይሉ ኣርኣያ በፍንፊኔ /ኣዲስ ኣባባ/ ኣራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ በወያኔ መንግስት የተወሰደውን ኣስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ላይ የምለው ይኖረኛል።

ዶክተር ኃይሉ ኣራኣያ ስለጉዳዩ በሰጡት ኣስተያየት “መንግስት የዘራውን እየለቀመ” ነው ያሉት። የኢሕኣዲግ መንግስት ምን ሆነና ነው የዘራውን ለቀመ የሚባለው? እሱ እኮ የኦሮሞ ህዝብ የተማሩና ጠንካራ የሃገር ተረካቢ ትውልድ እንዳየኖረው እያደረገ ስለሆነ ምን ተጎድቶ ነው የዘራውን ኣጨደ የሚባለው? ዶክተሩ ሌላ እንደምክንያት ያነሱት በብ ሄር መደራጀትን ነው። በብሄር የተደራጀው ኦሮሞ በቻ ነው? ኣማራም ሲዳማም ወላይታም ሁሉም በኢትዮዽያ የሚገኙ ህዝቦች ናቸው በብሄር የተደራጁት ታዲያ ለምን ግጭቱ በእነዚህ ሁሉ መካከል ኣልተፈጠረም?

ስለዚህ እንደ ተለመደው ለማንኛውም በኢትዮዽያ ውስጥ ለሚፈጠረው ሁሉ ተጠያቂው “የብሄር ፖለቲካ,” “የጎሳ ፖለቲካ” ወዘተ ብለው ለመኮነን ካልሆነ ኢሕኣዲግ ባልተጎዳበት የዘራውን ኣጨደ የሚያሰኝ ነገር የለም። ትክክለኛው መግለጫ ዶክተር መረራ ያሉት በኢሕኣዲግ ኣገዛዝ የሃገሪቱ “ዲሞክራሲ ኣልባ” መሆን ነው። ለዚህ ደግሞ የህዝቦችን በማንነታቸው ላይ ተመስርተው መደራጀትን “የኣንድነት” ጠላት ኣድርገው የሚኮንኑ ሃይሎችም ጭምር ተጠያቂ ናቸው። እነዚህ ወገኖች የህዝቦችን በፈለጉት መልክ መደራጀትን ቢደግፉና ቢያከብሩ ኖሮ የወያኔን መንግስት የከፋፍለህ ግዛ መንገድ በዘጉ ነበር። የህዝቦች በፈለጉት ኣይነት መደራጀትን መደገፍና ማክበር እራሱ ትልቁ የዲሞክራሲ መርህ መሆኑን ኣለመረዳታቸው በጣም ያስገርማል። ለግዛት ኣንድነት ሳይሆን ለህዝቦች ኣንድነት መሰረቱ ዲሞክራሲና ዲሞክራሲ ብቻ መሆኑን ካልተረዱና የህዝቦችን ነጻ ፍላጎት ካልተቀበሉ እኛ ለፍትሕ፣ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ነው የምንታገለው ማለት ኣይቻልም።

ሌሎችም ዶክተር ሃይሉ እንደምክንያት ያነሱት፣ እንደ በቂ ምግብ ኣለማግኝት፣ የትምህርት ጥራት፣ የመጨናነቅ ወዘተ ያሉትም በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ብቻ ደርሶ ግጭት ኣልፈጠረም። እነሱም ያንን ኣላነሱም። ዶክተሩ ካነሱኣቸው ውስጥ “የነጻነት ማጣት” ባሉት መቶ በመቶ እስማማለሁ። ዩኒቨርሲቲዎች የኣካዳሚ ነጻነታቸውን ኣጥተው የኣምባገነኖች ጉዳይ ኣስፈጻሚ ከሆኑ ረጅም ኣመታት ተቆጥረዋልና። ነጻ የተማሪዎች ማህበር፣ ነጻ የመምህራን ማህበርና በኣጠቃላይ በዩኒቨርሲቲዎች በነጻነት የማሰብ መብቶች ያለመኖር ተማሪዎቹ እንዳይወያዩና በመሃላቸው ያለውን ልዩነትና ኣንድነት እንዳይረዱ ማድረጉ ትልቁ ችግር መሆኑ ግልጽ ነው ዶክተር መረራ እንዳሉት። ለዚህ ዋናው ተጠያቂ የዲሞክራሲ ጠላት የሆነው ኣምባገነኑ የወያኔ መንግስት ሲሆን ለነጻነት፣ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ እንታገላለን የሚሉትም ተጠያቂነት ኣለባቸው። ምክንያቱም እነዚህ ሃይሎች ‘ልዩነት ያልሆኑ’ ልዩነቶቻቸውን ኣቻችለው በጋራ ቢሰሩ ኖሮ የወያኔ መሪዎች በህዝቦች ላይ ባልፈነጩ ነበር። ዋናው መፍትሄም የሃገሪቱን የወቅቱ ተጨባጭ የፖለቲካ ኣደረጃጀት ኣምኖ በመቀበል በዚያ ኣቅጣጫ ለሚፈለገው የህዝቦች ኣንድነት መስራት ብቻ ነው። ይህን ጊዜ ነው ተማሪዎችም ልዩነቶቻቸውን ኣቻችለው ኣንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ መምከር የሚቻለው። ኣባቶች ልዩነቶቻቸውን ማቻቻል ባልቻሉበት ልጆችን ተቻቻሉ ማለት ከጋሪው ፈረሱን ማስቀደም ከመሆን ኣያልፍም። ዶክተር መረራም በቃለምልልሳቸው ማጠቃለያ ጥሪ ያቀረቡት የድሞክራሲ ሃይሎች ነን የሚሉት ልዩነቶቻቸውን ለማቻቻል እንዲሰሩ ነው።በግልጽ የሚታወቀውን የሃገሪትዋን የፖለቲካ ችግር ለመፍታት መጣር ነው እንጂ ዶክተር ሃይሉ በማጠቃለያቸው እንዳሉት ተማሪዎችን ‘ግብረገብ’ በማስተማር ኣይደለም።

* በቀለ ከስውድን

No comments:

Post a Comment