የኢትዮጵያዉን ስደተኞች መከራ

April 05, 2013 | DW

ጩኸቱ ይቀጥላል። ከኢትዮጵያ ሰሜን ምሥራቅ፥ ወገኖቻቸዉን ለአደን ባሕር-አሳ-አዞ ገብረዉ ቀይ ባሕርን የተሻገሩ ኢትዮጵያዉያንን ስቃይ-ሰቆቃ እንስማ።የመን።ከሰነዓ እንጀምር።


የመን የሚገኙ ኢትዮጵያዉን ስደተኞች የሚደርስባቸዉ ግፍና በደል ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ዓለም አቀፉ የሥደተኞች መርጃ ድርጅት (IOM) አስታወቀ። ዓለም አቀፉ ድርጅት እንደሚለዉ በተለይ የመንን ከስዑዲ አረቢያ ጋር በሚያዋስነዉ አካባቢ የሠፈሩ ሥደተኞች ከምግብና መጠለያ ችግር ባለፍ በወረቦሎች እየታገቱ የሚደርስባቸዉ ግፍ ከሚነገረዉ በላይ ነዉ። በኢትዮጵያ የIOM የመገናኛ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ደምሰዉ ብዙወርቅ እንደሚሉት መሥሪያ ቤታቸዉ ሥደተኞቹን ለመርዳት ቢሞክርም በገንዘብ እጥረትና በስደተኞቹ ቁጥር መብዛት ምክንያት ተፈላጊዉን ርዳታ መስጠት አልቻለም።

ትናንት ሱዳን የገቡ የኢትዮጵያ በጣሙን ደግሞ የኤርትራ ስደተኞችን ሥቃይ ሰቆቃ ሰምተን ነበር። ወደ ሰሜን አፍሪቃ-እስከ ሊቢያ፥ ሽቅብ ወደ ሰሜን እስከ ሜድትራኒያን ማዶ እስከ ልታ ወይም ኢጣሊያ፥ ደግሞ በተቃራኒዉ ቁልቁል ወደ ደቡባዊ አፍሪቃ እስከ ታንዛኒያ፥ ማላዊ፥ ሞዛምቢክ ወይም ደቡብ አፍሪቃ ጥግ እሕ-ቢሉ የኢትዮጵያ፥ የኤርትራ፥ የሶማሌ ስደቶችን ስቃይ ሰቆቃ-እስኪያንገሸግሽዎት ይሰማሉ።

ጩኸቱ ይቀጥላል። ከኢትዮጵያ ሰሜን ምሥራቅ፥ ወገኖቻቸዉን ለአደን ባሕር-አሳ-አዞ ገብረዉ ቀይ ባሕርን የተሻገሩ ኢትዮጵያዉያንን ስቃይ-ሰቆቃ እንስማ። የመን ከሰነዓ እንጀምር።


ብዙ ጊዜ የተገለጠዉ ብዙ ችግር፥-የመኖሪያ ፍቃድ አያገኙም። ሥራ የላቸዉም። ሥራ ካገኙም አንዳድ አሰሪዎች ይደበ ቧቸዋል። ክፉዎቹ ይደፍሯቸዋል። ደሞዝ ሳይሰጡ የሚያብሯቸዉም ብዙ ናቸዉ። ሳዑዲ አረቢያ ጥግ ሐራጥ በምትባለዉ ከተማ ካሉት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ፥ የሰነአዎቹ ችግር-ሴትዋ ራሳዋቸዉ እንደሚሉት ቅንጦት ብጤ ነዉ።

ሴትዮዋ ከሩቅ ያዩ-የሰሙትን ነገሩን፥-እሱ ደግሞ እዚያዉ ነዉ። ሐራጥ።ይኸኛዉ ከኢትዮጵያ ከመሰደዱም በፊት ጋዜጠኛ ነበር። እዚያም ሔዶ የሙያ ልክፉቱ አለቀቀዉም። ጉዳተኞች አሉበት እየሔደ ሲችል እርዳታ፥ ይጠይቅላቸዋል። ሲያቅተዉ በደላቸዉን ለሌሎች ያሳዉቃል።አይቷል ሰምቷልም።


ግፉ ልክ የለዉም፥ ገፈኞቹ ግን ሰለቦቹ እንደመሰከሩ ከሩቅ ያለነዉ እንደምን ሰማዉ ወይም ዓለም አቀፉ መገናኛ ዘዴዎች እግረ-መንገዳቸዉን እንደሚነግሩን አይደለም።

ስደተኞቹ እንደሚሉት ካለሙት ሳዑዲ አረቢያ ወይም ሌሎች የፋርስ ባሕረ-ሠላጤ አካባቢ ሐገራት መግባት የማይማቻል ነገር ነዉ። እዚያዉ የመን መቆየትም የመደብደቢያ፥ መቆረጪያ፥ መደፈሪያ ቀንን መጠበቅ ነዉ።ወደ ሐገር የሚመልሳቸዉም የለም። የኢትዮጵያ መንግሥት ኤምባሲማ «አሳፋሪ» ይለዋል ጋዜጠኛዉ

በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የአይ ኦ ኤም የመገናኛ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ደምሰዉ ብዙ ወርቅ እንደሚሉት የስደተኛዉን ሥቃይ መከራ መስሪያ ቤታቸዉ ያዉቀዋል። ለመርዳትም ይፈልጋል፥ ይሞክራልም።ሁሉንም ችግረኛ ለመርዳት ግን ገንዘብ የለም።

ሥቃይ ሰቆቃዉ ቀጥሏል። መፍትሔዉ፥ ላሁኑ አይታወቅም።  

No comments:

Post a Comment