ግልገል ነፍጠኞችን ምንድነው የሚያንጫጫቸው?

February 03, 2015 | From Young Oromo intellectual Jawar Mohammed

ሰሞኑን አንድ አንድ የ OMN ጋዜጠኞች ከ አብዱላ ገመዳ ጋር ቁጭ ብለው የሚያሳይ ፎቶ በ ኢንተርኔት ከተሰራጨ በኋላ ትንሽ ቀዝቀዝ ብሎ የነበረው የግልገል ነፍጠኞፍ በሽታ ማለትም ኦሮሞፎቢያ እያገረሸባቸው ይመስላል። ጋዜጥኞቹ በምን ሁኔታ ከ ባለስልጣኑ ጋር እንደተጋናኙ በስፋት ገልጸዋል። ስብሰባውን እና የሚጠበቀውን የተቃውሞ ሰልፍ ለመዘገብ ወደ ስፍራው ተጓዙ። ሲደርሱ ፖሊሶች እነሱንና ሌላውንም ህዝብ አባረሩ። ካሜራ ይዘው መግባት አለመቻላቸውን ሲያውቁ እቃቸውን ትተው ተመሳሰለው ገቡ። በዚያ መልኩ መግባት የቻሉት እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ጋዜጠኞችን ጨምሮ 39 ኦሮሞዎች ባብዛኛው ለተቃውሞ የሄዱ ነበሩ። ስብሰባው ላይ ጋዜጠኞቹ ጠንካራ ጥያቄዎችን አቀረቡ። በተቻላችው አቅምም በስልክ መቅዳት ቻሉ። ስብሰባው ሲያልቅ በግል ለናነጋግራችሁ እንፈልጋለን ተባሉ። ከነዚህ ባለስልጣኖች ጋር ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ለቀናት ጥያቄ ሲያቀርቡ ነበር። እናም በግል እናናግራችሁ ሲባሉ ያ ሙከራቸው የተሳካ መሰላቸው እና ተከትለው ወደ ቀጣዩ ክፍል ገቡ። ነገር ግን እንደሰቡት አልሆን። ክፍሉ ለእራት የተዘጋጀ ነበር። ቃለመጥይቁን እንደማይፈቅዱ እና አብረው ቁጭ ብልው የሚለዋውጡትን ንግግር እንኳን መቅዳት እንደማይችሉ ተነገራቸው። ከ 20 ዳቂቃ የማግባባት ሙከራ በኋላ ጥለው ወጡ። ፎቶው የተነሳው ይህን የማግባባባት ጉትጎታ ሲያደርጉ ነው። በቃ ይህ ነው ታሪኩ።


ታዲያ የሚገርመው የግልገል ነፍጥኞቹ ጩሀት የባስበት ጋዜጠኖቹ በዚህ መልኩ ዝርዝር ዘገባ ካቀረቡ በሃላ መሆኑ ነው። ለመሆኑ እንዚህ ግልግለ ነፍጠኖች የሚቆጣጠሩት ሚዲያ አባዱላን ወይንም ሌላ ባለስልጣን ጋር ለ exclusive ቃለ መጠይቅ ቢጋበዙ እምቢ ይላሉን? እንተዋወቃለን እኮ. OMN አይደለም ከ ኦሮሞ ብሄር የፈለቀን ሰው ይቅር እና ኦሮሞ የሚለውን ቃል የሚጠየፉ፣ ማንነታችንን የሚያንቋሽሹ፣ የፖሊቲካ አመለካከታቸው እንደ አረጀ ፈረሰ የተንሸዋረረ የ neo-neftegna መሪዎችን እንኳን የጋዜጠኝነት ሙያ በሚጠይቀው መሰረት በክብር ለማስተናገድ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ይህንን መርህ ደግሞ ባለፉት 10 ወራት በተግባር አሳይቷል። የ ሰማያዊ ፓርቲን የተቃውሞ ሰፍል ቢጤ፤ በ 'አንድነትን' ቡድን ላይ ወያኔ የወሰደውን የማፍረስ ሴራ፤ የግንቦት ሰባትን የ ኤርትራ ድንፋታ በሚጋባ ሳያሳንሱ ሳያጋንኑ ዘግበዋል። ጋዜጠኘንነት ማለት የበሬ ወለደ breaking news እያራገቡ እንደሻፈደ አህያ ማናፋት አይደለም። ጋዜጠኝነት ህዝቡ ማወቅ ያለበትን ነገር፤ የት፣ እንዴት፣ መቼ፣ በማን እንደተፈጸመ መርምሮ verifiable fact ማቅረብ ነው። OMN በህዝብ መዋጮ የሚተዳደር የህዝብ (public) ሚዲያ ነው። የኦሮሞን ህዝብ እውነት (truth) በ እውነተኛ መንገድ ለማቅረብ ነው የተቋቋመው። ይህ ማለት ግን የሌላውን ህዝብም ሆነ ቡድን እውነታ (ቡድኑ ጠላትም እንኳ ቢሆን) የማፈን ፍላጎት የለውም።

በነገራችን ላይ ዛሬ የኦሮሞ ጋዜጠኖች ከአንድ የኦሮሞ ባለስልጣን ጋር ፎቶ ላይ ታዩ ብለው ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት ሰዎች የራሳቸውን ገመና መፈተሽ አለባቸው። የብአዴኖቹ እነ አዲሱ ለገሠ፤ ህላዊ ዮሰፍ፣ ጀነራል አበባው ታደሠ ከዛም አልፎ የወያኔ ቱባዎች እነ ስበሃት ነጋ፤ ጻድቃን ገብረትንሳይ፤ አባይ ጸሃየ፣ ሳሞራ ዩኑስ እዚህ ሀገር ሲመጡ የ አሜሪካን ምርጥ steak ከ blue label ጋር የሚጋበዙት ከ ድሮ የክፍል ጓደኞቻቸው ከ አሁኖቹ ነፍጥ-አልባ የ DC አርበኖች ጋር መሆኑን በተጨባጭ እናቃለን። ግማሹን በ አይኔ በብሌኗ አይቻለሁ። የዛሬን አይበልው እና አንድ ሰሞን ቤተኛ እስከመሆን ደርሰን እንደነበር አትርሱ ፡)
ታዲያ ዛሬ የኦሮሞ ጋዜጠኖች (ልብ በሉ የ ፖሊቲካ መሪዎች አይደሉም) ሙያዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ከ አባዱላ ጋር ቢገናኙ ይህን ሁሉ ጩሀት ምን ቀሰቀሰው? መልሱ ቀላለ ነው። ለግልገል ነፍጠኞች እና ወያኔዎች ከምንም እና ማንም በላይ የሚያስፈራ ነገር ቢኖር እርስ በርሳቸው ጠላቶች ናቸው ብለው የሚጥብቋቸው ኦሮሞዎች አብረው መታየት ነው። እንደነሱ ፍላጎት ኦሮሞ በቡድን ተከፋፍሎ ሁሌም አንዱ አንዱን እያብተለተለ፣ አንዱ የኦሮሞ ቡድን ከነሱ ጋር አብሮ ሌላ ቡድን ውስጥ ያሉ እህቶች እና ወንድሞቹን እየዘረጠጠ እራሱንም እያዋረደ ባዕዳንን እያስፈነደቀ ቅሌት ሲሸከም ነው። እነሱ ማየት የሚፈልጉት እና የለመዱት የኦሮሞ ልጆች በመኢሶን፣ እጭአት፣ ኦነግ፣ ኦህዴድ፣ ኦዲፍ፣ ኦፍሲ ... የ ዳዉድ ኢብሳ ኦነግ፣ የከማል ገልችሁ ኦነግ፣ የገላሳ ዲልቦ ኦነግ እንዲሁም የ ሌንጮ ለታ ቡድን ፣ የመረራ ጉዲና፣ የቡልቻ ደምቅሳ ተብሎ ተደርድሮ እየትኳረፈ፤ ከቻለም እየተታኮሰ ሲፋጭ ማየት ነው። እንደነሱ ፍላጎት አባዱላ አብዲ ፊጤን በታንክ ደምስሶ ሲሸልል ወይንም አብዲ ፊጤ አባዱላን በ አስቀያሚ ስድብ ዘርጥጦት ሲያዋርደው አይተው ሁለቱንም ለ mutual self destruction ማበረታታት ነው። እስቲ ልብ በሉ። VOA እና የጀርመን ራዲዮ አማርኛ ፕሮግራሞች የኦሮሞ ድርጅቶች ሲከፋፈሉ ተፎካካሪ መሪዎችን ጋብዘው ሲያነታርኩ እንጂ ተመልሰው ህብረት ሲመሰርቱ ዘግበው ሰምታችሁ ታቃላችሁ?

ግልገል ነፍጠኞች እና ወያኔዎች የኦሮሞን መከፋፈል፣ መነታረክ የሚፈልጉትም ያለ ምክንያት አይደለም። የተከፋፈለ እና እርስ በርሱ የሚናከስ ኦሮሞ እራሱን በራሱ እያዳከመ ለጠላቶቹ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል። እንደዚያ የተከፋፈለ ኦሮሞ ሲኖር፤ ባለጋራዎቹ በፖሊቲካ ጉዳዮች ላይ በጅምላ ከመደራደር ይልቅ በችርቻሮ አንዱን ወይም ሌላውን ቡድን ለማባበል እና ብሎም ለመግዛት ያመቻቸዋል። አንዱን ቡድን አቅርበው ሌላውን በጠላትነት ፈርጀው አያባሉ እሾህን በሾህ ያወጡታል። ለረጅም ዘመናትም ሲሆነ የቆየውም ይሄው ነው። ያ አለም ያደነቀው የ ኦሮሞ ራባ ዶሪ ጦር በ አቢሲኒያን ህይሎች ተሸንፎ ሃገሩ በባዕዳን ቅኝ አገዛዝ ስር የወደቀችው ዋናው ምክንያት ይህ ክፍፍል ነው። ከ ቅርብ ጊዜ ወዲህ በነታደሰ ብሩ፣ ኤሌሞ ቂልጡ፣ ዋቁ ጉቱ እና ሌሎች መስራችች የተጀመረው የ ኦሮሞ ብሔራዊ አንድነት ግንባታ ከ አበባ ወደ ፍሬ ተሸጋግሮ ለችርቻሮ ፖሊቲካን ምህዳር እያጠበበ ያለ አስደማሚ የኦሮሞ ብሄረተኘት እውን ወደመሆን እየተጠጋ ነው። ይህ እውነታ ነው ግልገል ነፍጠኖችን እና ወያኔዎችን እንቅልፍ ነስቶ የሚያቁነጠንጣቸው። አብደው ጨርቃቸው ጥለው ይሄዷታል እንጂ የኦሮሞ ልጆች አንድነታቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከሩ ወደ ነፃነት የሚያድርጉት ጉዞ ለሰከንድም አይገቱትም።

No comments:

Post a Comment