መክሸፍ እንደነ ጌች

March 01, 2014 Gadaa.com | በናኦድ፡ ዱጋ
Editor’s Note: the phrase, “መክሸፍ እንደ …,” was recently popularized by a Shoan Amhara elite with Ankober roots, Prof. Mesfin Woldemariam, who’s also the brainchild of the Neftegna supremacist organization called the Blue Party.
Writer Na’od Duga below uses the same phrase, “መክሸፍ እንደ …,” to criticize another Ankober-born Neftegna elite, Prof. Getachew Haile, for his hate propaganda on EthioMedia – which was directed at the Oromo nation.
Note to readers: Ankober was the home of murderer Menelik before he invaded Finfinne and the rest of Oromia, and the South. Thus, Ankober Amhara Neftegna’s were the most privileged by the regimes ousted by the peoples’ struggles in 1974 and 1991, and bitter by these popular defeats, remnants of The Old Regime currently hide behind “All-Amhara”/”All-Ethiopia” organizations to attack the Oromo nation using the ideology of Abba-Bahrey, who was also a resident in Shoa while writing his hate propaganda against the Oromo people in the 16th-century.

መክሸፍ እንደነ ጌች

ይድረስ ለ Prof. ጌታቸው ሀይሌ & Co.
ኦሮሞውን፣ ደቡቡን፣ ሙስሊሙን፣ አንዳንዴ ትግሬውንም ጨምራችሁ ትወርዱበታላችሁ። እናውቅልሃለን ትሉታላችሁ። አብሮአችሁ ያልዘመረውን፣ አጋጣሚ በለገሰቻችሁ ጡንቻ ደቆሳችሁት። ያለኛ ኢትዮጵያ ብላችሁ፣ ኢትዮጵያን አሳነሳችሁኣት። ሰዉን አእምሮውን አጥባችሁት፣ የናንተን ማንነት እንዲለብስ አለማችሁ። በከፊል ተሳካላችሁ። ዘመን ተለውጣ፣ እናንተም ፈረጠጣችሁ። ርዝራዡ ግን፣ እስከ አሁን ሰላም አሳጥቶን አለ።
ዕርቅና ሰላም፤ የሕይወት ቅመም” ብለህ ጥላቻን በውሸት ለውሰህ፣ ላቀረብከው ጽሁፍ ምስጋና እንደማትጠብቅ ገምታለሁ። “አንቱ” እንዳልልህ ማስመሰል ይሆንብኛል – ላንተ አይነቱ የአባ ባሕርይ ተቀጽላ አክብሮት የለኝምና። ስድብ ትቼ የ”መማር ማስተማር” ሂደቱን ያንተን ዘረኛ ጽሁፍ “ዲኮንስትራክት” [deconstruct] በማድረግ ላስጀምረው። ከተሳሳትኩ ታርመኛለህ።
መወራት ያለበት፣ ማን ማንን ይቅር ይበል አይመስለኝም። ያንተና የመሰሎችህ አስተሳሰብ ዞሮ ዞሮ ከ ቤተክርስትያኒቱ አያልፍምና ትንሽ መሰረትህን እንድትመረምረው፣ አንዳንድ ነገሮችን ልንገርህ። ከአለም ድሀ አገሮች ግንባር ቀደም አገር፣ እንግዲህ ይሄን ሁሉ ጉራ ከየት አመጣችው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። መልሱ ከባድ አይመስለኝም።
ሰሞኑን አንድ የመንግስት ባለስልጣን ተናገረ የተባለውን ሰምተሃል መቼም። አንድን ህዝብ በጅምላ መሳደብ ተገቢ አይደለም። ያሳዝናል። ቀጥሎ፣ ያንተ “ቅመም” ጽሁፍ ብቅ አለች። አማራው አለምነህ አማራውን ሲሳደብ፣ አንተንና መሰሎችህን ማለቱ ይሆን እንዴ እስክል ድረስ። አህያውን ፈርቶ ዳውላውን? የናንተ ጦስ ብዛቱ!
ውሸትን ስትግቱት የኖራችሁት ህዝብ በብዙ መልኩ የናንተ አይነት ሰዎች ውጤት ነው፤ ታሪክ ነው ብሎ የሚቀበለው፣ ለሌሎች ህዝቦች የሚኖረው እይታ፣ አለምን የሚመለከትበት መነጽር፣ ወዘተ። የናንተ አይነት ሰዎች ስል ባለስልጣናትን፣ ምሁራንን፣ የቤተክርስትያን (ወይም የመስጅድ) መሪዎች የመሳሰሉትን ማለቴ ነው። ሶሻል ሪያሊቲው [social realty] ላይ አሻራቸው በግልጽ የሚታይ ግለሰቦች። ምናባዊም ሊሆን ይችላሉ፤ እንደ አምላክ። ወይ ሰው ሰውን ለመቆጣጠር የፈጠራቸው፤ እንደ ምኒልክ ቀዳማዊ።
ይህን የምተይበው ከመሞትህ በፊት፣ እርጅና ያጠበበው አይንህ በእውቀት ብርሃን ይከፈታል፤ ስትተፋው ከኖርከው ጥላቻ ተጸጽተህ ትመለሳለህ፤ ከዛም አልፎ ያንተንና የመሰሎችህን ባዶ ኩራትና የትምክሀት ጠላ እየተጎነጩ ላደጉ ተተኪ “ጌታቸው ሀይሌዎች” የተሻለ መልእክት ታስተላልፋለህ ብዬ አይደለም። የጻፍከው ጽሁፍ የመሰሎችህን እውነተኛ ቀለም ስለሚያሳይ፣ ልክ ልክህን መንገር ተገቢ ነው። የናንተ ትእቢት ከወረቀት አልፎ፣ ሰው ሊያጫርስ ይችላልና ዝም መባል የለበትም። የዋሁ ህዝብ፣ ከናንተ “ምሁራን” በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚሰማውን ያለ አመክንዮ ሊቀበል ስለሚችል ማለት ነው።
ስልጣኔ ምን ማለት ነው? ስልጡን ማን ነው? ስልጣኔ የማን ነው? ዘመናዊነትስ? እንዲህ የምትንሰፈሰፍለት የኦርቶዶክስ ክርስትና መሰረቱ ምንድን ነው? ለህዝቡ ምን ፈየደለት? ወየት ያደርሰናል? ትንሽ እናውጋ እስኪ።
በክርስቶስ ዘመን የኖረው ፈላስፋ ሴኔካ “ሀይማኖት ለህዝቡ እውነት፤ ለጠቢቡ ውሸት፤ ለገዢው ጠቃሚ ነው” ይላል። የሀይማኖትን እውነትና ውሸት መሆን ስለማናውቅ ለገዢና ተገዢ ካለው ትርጉም ላይ እናተኩር። አንተን ከገዢው መድብሃለው። ያው ቤተ-ክህነቱ አይደል ከንጉሳዊያን ጋር ተባብሮ ህዝቡን የጨቆነው? ተገዢነትን፣ ስንፍናን፣ ድህነትን እንደጸጋ መቀበልን፣ ፍርሀትን፣ ላዳዲስ ሀሳቦች ዝግ መሆንን … ማን አስተማረው?
ያንተ የክርስትያኑ ማንነት እንግዲህ የአይሁድን ብሉይ ኪዳን በመንተራስ የክርስቶስን ውልደት፣ ስቅላትና ከሞት መነሳት በማመን ነው የተመሰረተው። በዚያ ላይ፣ የራስህን ተረት ጨመርክበት። እብሪትህ ከሚጨበጠው አለም ተነስቶ፣ መለኮታዊ ቡራኬን ከራስህ አገኘ። ማን ይቻልህ? ያው “ራስህ” ስልህ በእጅ አዙር ስታሾርህ የነበረችውን አሌክሳንድርያን አስባት – ከአራተኛው ምዕተ አመት እስክ ዛሬ ሀምሳ አመት ድረስ። ዝም ብለህ ባህርይን ከምታነበንብ ዞር ዞር ብለህ ታሪክ አንብብ። ሁሉም ነገር በግእዝ የተጻፈ ከመሰለህ ተሳስተሃል።
ከክርስቶስ ልደት 300 አመት በፊት፣ አንተ ያልሰለጠኑ የምትላቸው ኦሮሞዎች ሰማይ ሰማያትን እየተመለከቱ ከህንዳዊያን ቻይናዊያንና ከማያ ጋርሊወዳደር የሚችል ቀን መቁጠርያ ፈጥረው ነበር። አምላካቸውንም እንዳንተ ከሆረስ ከተበደሩ ከመበደር ይልቅ ራስዋን ተፈጥሮን አድርገው ነበር – ብዙም የሰው መልክ ሳይሰጥዋት። በሁኣላ ስፒኖዛንና አይንስታይንን የመሳሰሉ ልሂቃን ካራመዱት ፍልስፍና ጋር ይመሳሰላል።
(IQ ምናምን ብለህ የዘላበድከው ብዙ ወሬ አያስፈልገውም። ፈተና ይዘጋጅና፣ እንለካ።)
የፈለከውን ማመን ትችላለህ፤ አይመለከተኝም። ነገር የተበላሸው “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል አቢሲኒያንና ኦርቶዶክስ ክርስትናንን በማጋባት በተፈጠረ ጠባብነት ሰፊና ውብ ትርጉሙን ያጣ ጊዜ ነው። ታዋቂው ደራሲ ፊሊፕ ኬ. ዲክ ያለውን ላካፍልህ፤ “The basic tool for the manipulation of reality is the manipulation of words. If you can control the meaning of words, you can control the people who must use the words.” የቤተክርስትያን ባንዲራ ያለበስካት የባህር በር የሌላት የዛሬዋ “ኢትዮጵያ” አልነበረችም ኢትዮጵያ። ቃሉ የሚወክለውን ለራሳችሁ እንዲስማማ አድርጋችሁት ስለነበር ብዙሀኑን ለመቆጣጠር ተጠቀማችሁበት። በ “ቅድስት” ኢትዮጵያ ስም ስንት፣ በደል ተፈጸመ። አሁን “ይቅርታ ጠይቁን” የምትላቸው ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያዊ ነን ለማለት እስኪጸየፉ ድረስ ማለት ነው።
“ኢትዮጵያ” የሚለው ቃልና ዙርያውን ያለው እውነተኛ ታሪክ ከኛ ካሁኒትዋ ኢትዮጵያ ዜጎች አልፎ ለአፍሪካዊያንና ትውልደ አፍሪካዊያን ኩራት መሆን ይችላል። እነማርከስ ጋርቪና ዱ ቦይ የመሳሰሉት በሰፊው ጽፈውበታል።
ሀሳባቸው በናንተ አፈታሪክ ተነጠቀ እንጂ።
ራስተፈርያኖችን መመልከት ይቻላል። የሰው ልጅን እኩልነት ፍለጋ ሲሄዱ፣ መሰረቱ ውሸት የሆነ ርእዮተ አለም አጋጠማቸው። ሰመጡበት። ብለው ብለው፣ ጥቁርነታቸውን የሚክዱ በደም ኦሮሞ ሊባሉ የሚችሉትን የ “ይሁዳ አንበሳ” አጼ ያመልኩ ገቡ። የአጼው የተወዛገበ የማንነት እርከን የዘረጋችሁት ስርአት ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ ያሳየናል። ዘይገርም!
ሰሞኑን ያነበብኩት አንድ መጽሀፍ እንደውም አንተ ያሳነስካትን “ታላቋን ኢትዮጵያ” የኩሽ ስልጣኔ አድርጎ ደግመህ ደጋግመህ የምትቆጥረውን የሶስት ሺህ አመት ታሪክ ከስድስት ሺህ አመት በላይ አስረዝሞ ግብጽን አስቀድሞ አረብያን አስከትሎ፣ ባቢሎን፣ ህንድና ፋርስን የሚያዳርስ ታሪክ ይተርካል። አንተና መሰሎችህ ምናብ ውስጥ ያለችውን የ “ክርስትያን ደሴት” አቢሲንያ እንግዲህ በዚህ ዘመናትን ባስቆጠረ ታሪክ ውስጥ አንድ አጋጣሚ እንጂ የነገሮች ሁሉ መጀመርያና መደምደምያ እንዳልሆነች እወቅ። ከሶማሌዎች ጀምሮ እስከ አውሮፓ ያሉ ህዝቦች “የመጀመርያው” የግብጽ ስልጣኔ፣ የኛ ነው ሲሉ ይሰማል። ዞሮ ዞሮ እኔ ካንተ እሻላለሁ ነው ጨዋታው። (አለም ባንተ ህዝብና ቤተ-ክርስትያን ዙርያ እንደማትሽከረከር እያስታወስኩህ ነው።)
የምትገርመኝ ለንጉስ መገበርንና የፊውዳል ስርአትን እንደስልጣኔ እያየህ ራሱን አንተ “ማፊያ” ባልከው የገዳ [Gadaa] ዴሞክራሲና ውሸት ባልተሞጀረበት የእምነት መርሆች ያስተዳድር የነበረ ህዝብን ስትንቅ ነው። (የማታውቀው ከሆነ “ዋቄፈታ” ይባላል።)
አእምሮህ ትንሽ ሰፋ እንዲል ሂድና ፕሮፌሰር ላጲሶን ጠይቅ፤ ስለ ሳባና ሰለሞን አፈ ታሪክ በደንብ ያስረዱሀል። ኦሮሞዎች ሰው ሲገድሉ አየሁ፣ ያልክበት ዩትዩብ [YouTube] ላይ ጠቃሚ ነገሮችም አሉ። የጸጋዬ ገብረመድህንን ግጥሞች ተመልከት (ምሳሌ: “The Epic of Aesop” እና “Ilma Madhaa Abbaa Gadaa“)፤ የልዩነት ውበት፣ የአለም መስፋት፣ የኢትዮጵያ ምንነት ይገባሀል። እድሜ ከፈቀደልህ የፔትሪን መጽሀፍ አገላብጥ። በሽታህ ይለቅህ ይሆናል። ሰር ፍሊንደርስ ፔትሪ “The Making of Egypt” ላይ አንተ ከባህር መጡ የምትላቸው ኩሺቲክ ኦሮሞዎችን ከአስራ ሁለተኛው ስርወ መንግስት ጥቁር ስፊንክሶች ጋር ያመሳስላቸዋል። ያ ማለት እንግዲህ 1991-1759 B.C. መሆኑ ነው። 4ሺ አመት … ገና ብዙ የማናውቀው አለ።
ያው በአርኪዎሎጂና የኤትኖግራፊ ምርምር ላይ የተመሰረተ ስለሆነ እርግጥ ነው ብሎ ለመናገር ይከብዳል። ሆኖም፣ አንድ መነቁሴ ገዳም ቁጭ ብሎ ከሚፈበርከው ታሪክ የተሻለ ተአማኒነት አለው። ለነገሩ ይሄን ሁሉ የምትለው እውነትን የት መፈለግ እንዳለበህ ጠፍቶህ ሳይሆን፣ ማመን የምትፈልገውን የምታሳድድ የከሸፈ ምሁር ስለሆንክ ነው። ታሪክ ድንጋይ ላይ የተጻፈ አይምሰልህ። እውነት ስትገለጥና የመናገር ነጻነት ሲከበር፣ ትምህርት ሲስፋፋና ምርምር ሲካሄድ እንደ አዲስ ይተረካል። እንደ አዲስ ይነበባል። ነባሩን ባይሽረው አማራጭ ይሆናል።
(አላወራሁትም እንጂ ያው እስልምናም ካንተው ክርስትና አይብስም። ሁለቱም ለኔ ማርክስ እንዳለው ኦፒዬት [Opium] ናቸው። ፕሮቴስታንትነትንም ይጨምራል። ያንተን ቅዱስ፣ ሌላውን እርኩስ አታድርግ። ያስተዛዝበናል። ሁሉም የራሱ የሆኑ በጎና ጎጂ ልማዶች አሉት። እንዳንተ ሀይማኖተኛ የሆነውንም እንደኔ ያለውንም ሊያስማማን የሚችል ነገር ቢኖር “ራስህ ላይ እንዲደረግ የማትፈልገውን ሌላው ላይ አለማድረግ” ነው። ወርቃማው መርህ! ሌላው ተጨማሪ ይመስለኛል።)
ኦሮሞን አትፍራው። አትጥላው። ፍቅር ነው። ለማንነቱ ያንተ ቡራኬ የማያስፈልገው፣ ማስመሰል የማያውቅ፣ ኩሩ ህዝብ ነው። ያንተ አይነቱን ችሎ ኖሮዋል። (“ችለን እንጂ፣ ተችለን አናውቅም” አለ አንዱ።)
በል እንግዲህ … ብቻህን አለመሆንህ ያሳስበኛል። ተተኪዎችህ የጻፍከውን አንብበው፣ ዝም አሉ ማለት ይስማሙበታል ወይ ታሪክ አንተ እንደምትለው ብትጻፍ ደስ ይሰኛሉ ማለት ነው። ይቅርባችሁ። “ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ፣ አለያ ድንጋይ ነው ተብለህ ትወረወራለህ” ብዬ ልተርት። ይገባሃል ምን ማለት እንደሆነ።
ብዙ ወገኖቻችን በሞቱበት ትግል፣ እዚህ ደርሰናል። የብሄር ብሄረሰቦች ጥያቄ ቀሰ በቀስ ይመለሳል፤ ጅምሩ ጥሩ ነው ባይ ነኝ። አንተ የምትናፍቀው የፊውዳል ስርአት ላይመለስ ሄዶኣል። ያንተ አይነቱ በዛ እንጂ ይሄኔ ከብሄርና የሃይማኖት ፖለቲካ ወጥተን፣ ድህነትን ማሸነፍ ላይ እናተኩር ነበር።
የማታፍር ሰው ስለሆንክ ኦሮሞዎችና ሙስሊሞች፣ ይቅርታ ጠይቁን ብለሃል። ቃላቶቼ ጠንከር ካሉ አንባቢውን ይቅርታ ጠይቃለሁ። አንተ ይቅርታ መጠየቅ ማሰብ ሲገባህ ይሄኔ የምታስበው እንዴት አድርጌ ይሄ ልጅ የሚለውን ልካድ ነው – ተፈጥሮህ ክህደት ላይ የተመሰረተ ነውና።
(ባርቆብህ የተኮስከው የናንተን አስተሳሰብ በአጭሩ አቅርቦታል። የልብህን በመናገርህ፣ ሳላደንቅህ አላልፍም።)
መሰልጠን አይንን መግለጥ ነው። መሰልጠን ሰውን በሰውነቱ ማክበር ነው። መሰልጠን ስልጣኔን ከሁዋላ ቀርነት መለየት መቻል ነው።
ሰልጥን።
(ተጨማሪ: ላንተ አቢሲንያ ቅርጽ የሰጣት ከስዋ በፊት የነበሩ አንተ የምትንቃቸው ህዝቦች ስልጣኔ ሊሆን ይችላል። ደፍሬ “ነው” አልልህም። የማላውቀውን አውቃለሁ። ግን ጉራህን ያቀዘቅዝልህ ይሆናል። ከዚህ በታች ያሉትን ተመልከታቸው።)
ላሁን ይብቃ። ቸር እንሰንብት።
(ይህን መልእክት በኢሜይል ልልክልህ ፈልጌ አድራሻህን ላገኘው አልቻልኩም። ደርሶህ ካነበብከውና መልስ ካለህ ጻፍልኝ። “መማር ማስተማር” ይቀጥል።) 

No comments:

Post a Comment