የዶ/ር ኣቢይ ኣህመድ የቁልቁለት ሩጫ እንደቀጠለ ነዉ።

April 24, 2018 | Source: Face book Page of Tsegaye Hailu

ለፍርድ መቅረብ ያለበትን ወንጀለኛ የክብር ሜዳሊያ መሸለም ወንጀሉን መደገፍ ብቻ ሳይሆን ለኔም ምሳሌ ነህና እኔም ባንተ መንገድ እቀጥላለሁ እንደማለት ይወሰዳል። የዶ/ር ኣቢይ ኣህመድ የቁልቁለት ሩጫ እንደቀጠለ ነዉ።

ከኣቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ወንጀሎች መካከል ሊዘነጉ የማይገባቸዉ:-
***በኣቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የዉሸት የስልጣን ዘመን ከ5000 በላይ ንጹሃን ወገኖቻችን በወያኔ ታጣቂዎች ተገድለዋል። ይህንን ጭፍጨፋ ከፈጸሙትም ሆነ ካስፈጸሙት ዉስጥ ኣንድም ወንጀለኛ ለህግ ኣልቀረበም
***በኣቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የዉሸት የስልጣን ዘመን ከ700000 በላይ ሚስኪን ወገናችን በጉልበተኞቹ የትግራይ ጄነራል ነጋዴዎችና የኣብዲ ኢሌ ሸፍጥ ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል። ለዚህም ወንጀል ተጠያቂ የሆኑ ኣካላት ለፍርድ ኣልቀረቡም ብቻ ሳይሆን ሹመት ሽልማት እና ምስጋና ኣግኝተዋል እያገኙም ነዉ።
***በኣቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የዉሸት የስልጣን ዘመን መሬት የህዝብ ያለመሆኑ ቀርቶ የመንግስት ነዉ የተባለዉ እንኳን ወደ ቀልድ ተቀይሮ መሬት የወያኔ ነዉ የሚል ኣንቀጻ ህገ-መንግስቱ ዉስጥ ባይኖርም መሬት ላይ ያለዉ እዉነታ ግን ይህንን ሆኖዋል።
***በኣቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የዉሸት የስልጣን ዘመን ለመገመት የሚያዳግት የሃገሪቱ ወጣት ግፍ ኣንገፍግፎት ከዚህ የማይሻል የለም በማለት ከሃገሩ ተሰዶ የበረሃ ኣዉሬ የባህር ኣሳ እራት ሆኖዋል, እንዲሁም የጨካኞች ሰይፍ በልቶታል።
.............................
............................
...........................እና ሌሎችም
እንደዚህ ኣይነቱን ወንጀለኛ ነዉ እንግዲህ ዶ/ር ኣቢይ ጀግናዬ ነዉ የሚለዉ🤣🤣🤣
እኔ ከመጀመሪያዉ ጀምሮ ስጠይቀዉ ለነበረዉ ጥያቄ ኣጥጋቢ መልስ ኣግኝቻለሁ ሰዉየዉ ጠቅላይ ሚኒስተር ሳይሆን ተጥቅላይ ነዉ። ያዉ የበሰበሰዉን የወያኔ ኣጥፍቶ የመጥፋት ፖለቲካ በሌላ ሙድ ኣራማጅ ነዉ። ዋጋም የለሽ ብሬን መልሽ ኣለ ኣሉ ሰዉየዉ🤣🤣🤣🤣🤣🤣
ዶ/ር አብይ አህመድ ኣቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝን ብሄራዊ ጀግና ኣድርጎ ኣመስግኖ ማዳሊያ ሸልሞ የክብር ኣሸኛኘት ሲያደርግለት ማየት እጅግ በጣም የሚያሳዝን ከመሆኑም ባሻጋር በኣንድ ጎኑ ኣስቂኝም ነበር። ምክንያቱም ደግሞ ዶ/ሩ ስለ ኃ/ማሪያም ሲያወራ የሚጠቀማቸዉ የሙገሳ ቃላት በፍጹም ስለማን እንደሚያወራ ጭምር ግራ የሚያጋቡ ናቸዉ። የሚያወራዉ እሱ ራሱ ስለማን እያወራ እንደሆነ ያወቀ ኣይመስለኝም። የተወሰኑትን መርጬ ከፍት ለፊታቸዉ ደግሞ እዉነታዉን ኣስቀምጫለሁ:-
1. "ሃገሩን በማገልገል የሃገር ኣገልጋይነት ለትዉልድ ያስተማረ"------ እዉነታዉ ግን; ሃገሩን ሳይሆን ጥቂት የወያኔ ባለስልጣናትን ብቻ በማገልገል የክፋት ተባባሪ በመሆን ትዉልድን ለሆድ ኣዳሪነትን ያስተማረ

2. "ድንቅ መሪ"---- እዉነታዉ ግን; የክፉዎች ኣሽከርና ማፈሪያ የሆነ መሪ

3. "ክብር ኣይበዛበትም"----እዉነታዉ ግን; እረ የዉርደትም ደረጃ ካለ የተሻለ ዉርደትም ይበዛበታል

4. "ፈታኙን ጊዜ ያሻገረ"-----እዉነታዉ ግን; ከፈታኙ ጊዜ ሃገሪቱን ወደባሰ እና ወደ ተባባሰ ክፉ ፈተና ያስገባ፣ ያሻገረ ሳይሆን የበለጠ በዉድቀት ያሰመጠ

5. "ቆራጥ መሪ"------እዉነታዉ ግን; የያዘዉን ስልጣን ለኣንድ ቀን እንኳን በኣግባቡ ሳይጠቀም የ4ኛ ክፍል ጀኔራሎችን ትዕዛዝ ሲፈጽምና ሲያስፈጻም የነበረ ፈሪ

6. "እድገት እንዲቀጥል ያስቻለ"-----እዉነታዉ ግን; ዉድቀት እንዲቀጥል ያስቻለ

7. "ብልህ መሪ "-------እዉነታዉ ግን; በኣንድ ንግግሩም ሆነ ስራዉ ዉስጥ ብልህነት ያላሳየ መሪ

8. "ጀግና መሪ"------እዉነታዉ ግን; ደ/ጽዮንና መሰሎቹን ከኣምላኩ በላይ የሚፈራ መሪ

9. "እጁ ንጹህ የሆነ"-------እዉነታዉ ግን; እጆቹ ከ5000 በላይ ንጹሃን ወገኖቻችን ደም የተጨማለቀ

10. "ልብነት የሚጠየፍ"-------እዉነታዉ ግን; የሃገሪቱን ኣንጡራ ሃብት ሲዘረፉ ለነበሩት ከለላ በመሆን እና ባለመቃወም ሲያሰሪቅ የነበረ በመሆኑ ልባና የሌባ ተባባሪ ኣንድ በመሆናቸዉ እሱም የወጣለት ሌባ ነዉ

11. "የጦር መሪ የኢኮኖሚ መሪ"-------እዉነታዉ ግን; በቴሌቪዢን መስኮት ቀርቦ የተጻፈለትን ከማንበብ በስተቀር ምን እየተደረገና እየሆነ እንደነበረ እንኳን የማያዉቅ ግኡዝ

12. "ልጆቹን በሚያስደንቅ ሁኔታ ኣስተምሮ ለወግ ለማዕረግ ያበቃ"----እዉነታዉ ግን; የወገኖቻችንን ልጆች ግን በጠራራ ጸሃይ የጥይት እራት ያስደረገ, እናቶችን ኣባቶችን ኣያቶችን የልጆቻቸዉን የልጅ-ልጆቻቸዉን ወግ ማዕረገ ሳይሆን ቀብር እንዲያዩ ያደረግ
.....................
......................
....................... እና ሌሎችም
እዉነታዉ ይህ ሆኖ ሳለ ነዉ እንግዲህ ዶ/ር ኣቢይ ወንጀለኛን በዚህ መልኩ እያመሰገነ እያደነቀ ደግ ኣደረክ እያለ ያለዉ። እጅግ በጣም ያሳዝናል። ዶ/ር ኣቢይ ዶ/ር ኣቢይ እያላችሁ ደንኪራ ላይ የነበራችሁ ሁሉ እንግዲህ እርማችሁን ኣዉጡ። የመለስ ዜናዊ ራዕይ ይቀጥላል። ዶ/ር ኣቢያ ያን ለማስቀጠል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት ተቀን ይሰራሉ።

No comments:

Post a Comment